ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ

የደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ያየለበት የቡድን 20 ጉባኤ

የቡድን 20 ጉባኤ ሲጠናቀቅ በሱዳን፣ ኮንጎ፣ በእስራኤል በጉልበት በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶችና በዩክሬን “ፍትኃዊ፣ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ሰላም” እንዲወርድ እንደሚሠሩ መሪዎቹ ቃል ገብተዋል። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደው ጉባኤ የደቡብ አፍሪካ እና የአሜሪካ ውዝግብ ተጭኖታል። ጉባኤው ሲጠናቀቅ አሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝደንትነቱን አልተረከበችም።

11-24
13:30

ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ተቃራኒ የአፍሪቃ መርሕ

አንዳዶቹ ፎቶ ግራፎች ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዉስጥ የተነሱ መሆናቸዉ ቢረጋገጥም የነጮችን የበላይነት ለማስከበር ቆርጠዉ የተነሱት ዶናልድ ትራምፕ ግን ነጭ ደቡብ አፍሪቃዉያን ወደ አሜሪካ እንዲሰደዱ ፈቀደዋል።አሜሪካ ጥግ የምትገኘዉን የጃማይካ ስደተኛን ሳይቀር ከአሜሪካ ወደ አፍሪቃ ያስግዛሉ።መሰደድ የማይፈልጉትን የደቡብ አፍሪቃ ነጭ ዜጎችን ወደ አሜሪካ ይጋብዛሉ።ከአፍሪቃ ጋር የንግድ ግንኙነትን ማጠናቀር እሻለሁ ይላሉ፤ ደቡብ አፍሪቃን በዘረኝነት ያወግዛሉ።

11-17
13:48

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ምድር ሌላ ጦርነት እየተደገሰለት ይሆን?

ኢትዮጵያ በየሥፍራዉ ከሚደረጉ ግጭቶች በተጨማሪ የኑሮ ዉድነት፣ ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ደሕንነት እጦት፣ እገታና ግድያን የመሳሰሉ የሕግና ሥርዓት መጓደሎች አቃርጠዉ እንደያዟት ነዉ።ትግራይን ጨምሮ ከአራት ሚሊዮን የሚበልጥ ተፈናቃይ በየመጠለያ ጣቢያዉ እንደሰፈረ ነዉ።የኤርትራ ሁኔታም ከኢትዮጵያ የባሰ እንጂ ያነሰ አይደለም።በዚሕ ላይ አካባቢዉ ሌላ ጦርነት ይችል ይሆን?

11-10
13:02

የማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

ፓሪስ፥የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ያስተዋወቀ መድረክ ተከናወነ፣ ዴንሐግ፥ በሰዎች ማዘዋወር የተጠረጠረ ኤርትራዊ ላይ ኔዘርላንድስ ውስጥ ክስ ተከፈተ፣ ካርቱም፥ የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ለዕርቅ አወንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን የትራምፕ ረዳት ተናገሩ፣ ዳርኤሰላም፥ ፖሊስ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች የሚረብሹ ምስሎች እንዳይጋሩ አስጠነቀቀ፣ ቤርሊን፥ ጀርመን በሚቀጥለው የጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2026 ለዩክሬይን የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለማሳደግ ወሰነች

11-04
10:35

ማሕደረ ዜና፣ ኤል ፋሻር-የሱዳን እልቂት አዲስ ምዕራፍ

የካይሮና የአቡዳቢ ገዢዎች የመንንን ለመደብደብ ጥብቅ ወዳጅ ነበሩ።ቀጠር በማዕቀብ ለመቅጣት ተባባሪ ነበሩ።የቀድሞዉን የሶሪያ መሪ በሽር አል አሰድን ለማስወገድ ተመሳጣሪ ነበሩ።ሱዳንና ሊቢያ ጦርነት ላይ ተቃራኒ ኃይላትን ይደግፋሉ።ሱዳንም የቀድሞ ወዳጆች የገጠሙት-ወዳጆችን ያቃረነ ጦርነት ማዕከል እንደሆነች ቀጥላለች።

11-03
17:35

ማሕደረ ዜና፣ የASEAN ጉባኤ፣ የትራምፕ ጉብኝትና የሲኖ-አሜሪካ ድርድር

ቤጂንጎች ሲያመሩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ «የንግድ ጦርነት ቀላል ነዉ አልኩ እንጂ---ከቻይና ጋር ማለቴ አልነበረም» ማለታቸዉ ተዘገበ።ዘ-ኤኮኖሚስት የተሰኘዉ መፅሔት ደግሞ በቀደም «ቻይና በትራምፕ ዱላ አሜሪካናንን ደበደበች» አለ።የሁለቱ ሐገራት የንግድና የኤኮኖሚ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ለ5ኛ ዙር እየተደ,ራደሩ ነዉ።የቻይና ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጉዮ ጂያኩን ዛሬ እንዳሉት ዉይይቱ የሰከነና መግባባት የታየበት ነዉ።

10-27
13:39

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ሶማሊላንድ ጥልፍልፍ

የኢሮ ጉብኝት ባለፈዉ ሐሙስ ሲጠናቀቅ የበርበራ ወደብን የሚገነባዉ፣ DP ወርልድ የተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ፣ መርከቦች ከርበራ ወደብ ጀበል ዓሊ ወደተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወደብ እና በተቃራኒዉ መጓዝ መጀመራቸዉን አስታዉቋል። በኢትዮጵያ-ሶማሊያና ሶማሊላንድ መሪዎች ጉብኝት፣ ዉይይት፣ የፖለቲካ ጥልፍልፉ የአቡዳቢና የካይሮ ገዢዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም ጫና ማድረጋቸዉ የተሠወረ አይደለም።ይሁንና የሶማሊላንድ ዲፕሎማቶች በግል እንዳሉት ኢሮ የመሩት የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በኩል የቀረበለትን የሶማሊያ ፕሬዝደንትን ሥልት አልተቀበለዉም።ጉብኝቱም ባጭሩ ተጠናቅቋል።ምናልባት እስከሚቀጥለዉ ጊዜ።

10-20
13:30

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ኢትዮጵያ ዘንድሮ የሕዳሴ ግድብን አስመርቃለች።፣የካሉብ ጋዝ ማምረቻና የማደባሪያ ፋብሪካን የመሠረት ድንጋይ ጥላለች።አማራ ክልል ከፋኖ፣ ኦሮሚያ ክልል ከኦነሠ ወይም OLA ጋር የሚደረገዉ ዉጊያ አሸናፊና ተሸናፊ ሳይለይበት እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያ ምናልባትም የኤርትራ ክረምት ግን አብቅቷል።ዓየሩ ለወታደራዊ ንቅናቄ ይመቻል።እና ይዋጉ ይሆን?

10-13
14:15

ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል መጠቃት፣ የጋዛ ጦርነትና ድርድር 2ኛ ዓመት

ሕዝባቸዉ በየአደባባዩ የሚያደርገዉ ግፊት የጠናባቸዉ የምዕራብ አዉሮጳ መሪዎች እየተግተለተሉ ለፍልስጤሞች የመንግሥትነት እዉቅና ሰጡ።ኔታንያሁ በሚጭሩት ጦርነት ዘለዉ በመግባት ወይም ለኔታንያሁ መንግስት ፍፁም ድጋፍ በመስጠታቸዉ ምክንያት አረብ-ሙስሊም እየራቃቸዉ፣ ሕዝብ እየተከፋባቸዉ፣ ከተቀረዉ ዓለምም እየተነጠሉ የመጡት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥብቅ ወዳጃቸዉን ኔታንያሁን በቅርቡ «በቃሕ» አሉሏቸዉ።ወይም ያሉ መሰሉ።

10-06
14:09

ማሕደረ ዜና፣ ዓለም መሪዎች እየተግባቡ ይሆን ወይስ ግራ እያጋቡ

ሰዉዬዉ ከመቸኮላቸዉ የተነሰ በእስራኤል ላይ የሚለዉን በኢራን ላይ የተቃጣ አደጋ ብለዉት ነበር።ቸኩለዉ አሉት።ፈጥነዉ አረሙት።ኔታንያሁ እስራኤል ከመጥፋት አደጋ፣ ዓለምም ከመገደል ሥጋት ድኗል ቢሉም የለንድን፣ የፓሪስና የበርሊን መሪዎች አልተቀበሉትም። እንደ አሜሪካ ሁሉ የእስራኤል የቅርብ ወዳጆች፣ የኢራን ጠላቶች ፈረንሳይ፣ ብሪታንያና ጀርመን የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያሰደረዉ ሥጋት አልተወገደም ይላሉ።ወይም የኔታንያሁን ማረጋገጪያ አላመኑትም።በሶስቱ ሐገራት ግፊት የተሰየመዉ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኢራን ላይ ዳግም ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል።

09-29
13:53

ማሕደረ ዜና፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ80 ዓመት አዛዉንት ወይስ ጨቅላ?

ዓለም ከአንድ ሐገር የአዉቶሚክ ሥጋት ወደ ዘጠኝ ሐገራት የኑክሌር ሥጋትና ፍጥጫ ያደገችበት 80 ዓመት የሰላም ዘመን ነበር ማለት ይቻል ይሆን? አንዳድ ጥናቶች እንደጠቆሙት የጋራ ማሕበር ከተመሠረተ ከ1945 ወዲሕ ዓለም ከ300 በላይ ከባድ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።በአብዛኞቹ ጦርነቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች፣ የዓለም ልዕለ ኃያላን መንግሥታት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተካፍለወል።----ዛሬም ከሱዳን እስከ ጋዛ፣ ከዩክሬን እስከ ኮንጎ ዴምክራቲክ ሪፐብሊክ ዓለም ሰላም የላትም

09-22
15:08

ማሕደረ ዜና፣ ዝክረ-2017 ዓበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች

2017 ኤርትራን፣ ሶማሊላንድን፣ ሶማሊያንና ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር አስማማም-አጣላ፣ ቱርክን ለሽምግልና ጋበዘም-ጣልቃ አስገባ፣ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ እስከ አዲስ አበባ ኢትዮጵያዉያንን አስደሰተም-አስከፋ ሰበብ ምክንያቱ ሁለትም-አንድም ነዉ ወደብና ግድብ።ዉኃ።በ2017 የኮሪደር ልማትን አዲስ አበባ ላይ ክፉኛ የተፈተነዉ ጎርፍ ነዉ።-ዉኃ፣ወለጋና ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በትንሹ 10 ሰዎችን የገደለዉ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ላይ ሺዎችን ያፈናቀለዉ፣ ደቡብ ወሎ ዉስጥ የተፈናቃዮችን መጠለያ ጣቢያ ያጠፈዉ ጎርፍ ነዉ-ዉኃ።ሥደተኞችን የበላዉ-ባሕር ነዉ።ዉኃ።

09-15
14:50

የኦሮሚያ የጸጥታ ኹኔታ እና የአዲሱ ዓመት መባቻ

ዓመታትን ያስቆጠረው የትጥቅ ትግል አሁንም ድረስ መቋጫ አላገኘም ። አንዴ ውጥረት እያነገሰ ሌላ ጊዜ ረገብ እያለ የቀጠለው የታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ አካላት ግጭት ለማህበረሰቡ ሌላ ስጋት ካስከተለ ሰነበተ ። ዕገታ ፤ የዘፈቀደ ግድያ እና ዘረፋ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው ።

09-08
14:11

ማሕደረ ዜና፣የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫዉ ይታወቅ ይሆን?

ኢትዮጵያ ከሉሲ ግኝት እስከ አክሱም ሐዉልቶች፣ ዋልያን ከመሰሉ-እንስሳት እስከ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ከሶፍ ዑመር ዋሻ-እስከ ሐረር ግንብ፣ ከአድዋ እስከ ካራማራ ድል የሚደርሱ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የጀግንነት ታሪኮች ባለቤት መሆንዋ አያከራክርም።የዚያኑ ያክል የርስበርስ ጦርነት፣ የጎሳ ጥቃትና የፖለቲካ ዉዝግብ ኢትዮጵያን ቁል ዉል እየደፈቋት ነዉ።የድሕነት፣የበሽታና የረሐብ አስከፊነት ከተጠቀሰ የኢትዮጵያዉያን ቁጥር የአሐዞች ማድመቂያ ነዉ።የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣የስደተኞች ብዛትና ሞት ከተዘረዘረ ኢትዮጵያና ዜጎችዋን ማለፍ አይቻልም።ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታና ዘረፋም ከኢትዮጵያ «መለያዎች» እየተካተቱ ነዉ

08-25
13:43

ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት፣የጉባኤ ጋጋታና የዲፕሎማሲዉ ዉጣ ዉረድ

3 ዓመት ከመንፈቅ።ጦርነቱ አንዳዶች እንደገመቱት ከሁለቱም ወገን በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ወታደር አልቆበታል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሠላማዊ ሰዉ ተገድሏል።ቆስሏል።ተፈናቅሏልም።በብዙ መቶ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟል።ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ ከመቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስክሰዋል።ያሸነፈም፣ የተሸነፈም የለም።የጦርነቱ መሠረታዊ ምክንያት ምንም ሆነ ምን ከግዛት ይገባኛል ያለፈ ሰበብ አልቀረበበትም።ተጨማሪ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እንዳይጠፋ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈዉ ቅዳሜ አንዳሉት ተፋላሚዎች ሰጥቶ ለመቀበል ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል።

08-18
14:11

ማሕደረ ዜና፤ የጋዛ እልቂት፣ የእስራኤል አዲስ ዕቅድና የገጠመዉ ተቃዉሞ

በእስራኤልና በጠላቶችዋ አፀፋ ጥቃት ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ፣ ቤይሩት፣ ሐይፋ፣ ቴሕራን፣ ብዙ ሺሕ ሕዝብ አልቋል።የጋዛ ለብቻዉ ነዉ።የግዛቲቱ የጤና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ከ60ሺሕ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።ረሐብ የፈጀዉ ሰዉ ቁጥርም ወደ ሁለት መቶ ተቃርቧል።ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል።እስራኤልም ወደ 800 የሚሆኑ ወታደሮች ተገድለዋባታል።22 ወራት።ከዚሕ ሁሉ እልቂት፣ስደት፣ረሐብ፣ ስቃይ-ሰቆቃ፣ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ዕቅድ ከግብ አልደረሰም።

08-11
13:08

ማሕደረ ዜና፣ ሒሮሺማ-የመጀመሪያዋ የአዉቶሚክ ቦምብ ሰለባ 80ኛ ዓመት

«ያየነዉን ማመን በጣም ከባድ ነበር።» አሉ ኮሎኔል ቲቤትስ ኋላ።«አንዱ ባልደረባችን «የፈጣሪ ያለሕ» ሲል ሰማሁት» አከሉ ኮሎኔሉ።እነሱ የሚጥበረብር አስደንጋጭ ብልጭታ፣ ሰቅጣጭ-ድምፅ፣ ሐምራዊ፣ሰማያዊ ነጭ ቀለም ያለዉ ወፍራም፣ እምቅ፣ ጢሱን ሰንጥቀዉ ወደ መጡበት ተፈተለኩ።መሬት ላይ ለነበሩት ግን የዕልቂት እቶን በር ተበረገደ።አፍንጫ የሚሰነፍጥ ቅርናት፣ጆሮን የሚሰቀጥጥ የሰቆቃ ጩኸት፣ ከተቀመጡት አስፈንጥሮ የሚያንሳፍፍ ንዝረት፣ ትንፋሽ የሚያሳጣ ወበቅ---ዕልቂት።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሐሪስ ኤስ ትሩማን እንዳሉት ግን ለዩናይትድ ስቴትስና ለተባባሪዎቿ ታላቅ የታላቅ ድል የመጀመሪያ ምዕራፍ ነዉ

08-04
13:06

Recommend Channels