በማድመጥ መማር | Deutsche Welle

በድራማ መልክ የቀረበው ዝግጅት እያዝናና ስለጤና፡ ስለትምህርት፡ ስለማህበራዊ ኑሮ፡ ስለፖለቲካ እና ኤኮኖሚ ጉዳዮች ለአድማጮቹ ጠቃሚ መረጃዎችን ያቀርባል።

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 8«ያልታወቀው ወሰን»

ባለፈው ክፍል እምነት ለረጅም ጊዜ ከተማሪዎቿ ጋር ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት እንደገና ማስቀጠል ችላለች። ምን ያህሉ ተማሪዎች የችግሩ ሰለባ እንደነበሩም አታውቅም ነበር፡፡ ችግሩን መታገል እንዳለባት ስታስብ ጀምበሬን እንድታግዛት ጠየቀቻት፡፡ ራሂምም በሃሳባቸው ተስቦ ስኬታማ ዘመቻ ለማካሄድ ተቀላቅሏቸዋል፡፡ ቀጥሎ ምን ይከሰት ይሆን?

05-11
12:00

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 7«ተስፋ አለመቁረጥ»

እምነት ክፍል ውስጥ ከገጠማት ውድቀት ጋር ትግል ይዛለች ። ተማሪዎቿ እንደገና የእሷን ትኩረት ለማግኘት እየጣሩ ነው። ራሂም በማህበራዊ ሚድያ ከገባበት ሱሰኝነት ለመውጣት የሚያስችል ምክር ተቀብሏል፡፡ ጀምበሬ በምታደርገው ነገር ራሷን እየሆነች ነው ሶስቱ የወንድማማች ልጆች ላስቀመጡት የየግል ዕቅዳቸው ይታመኑ ይሆን?

05-04
11:59

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 6«ወድቆ መነሳት»

እምነት ባለፈው ጊዜ ከገጠማት ሱስ ለመላቀቅ ከሀኪም ባለሙያ ጋር ተገናኝታለች። ጀምበሬ በበኩሏ ኦንላይን ባቀረበችው ቪዲዮ ፍጹምነት ባለመርካቷ ከውስጣዊ ግፊቶቿ ጋር እየታገለች ነበር። ራሂምም በፍቅር ወጥመድ የገባ ይመስላል። ከሳምንት በኋላ የሶስቱ የወንድማማች ልጆች ታሪክ እንዴት ይቀጥላል?

04-27
11:59

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 5«እውነተኛ ማንነቴ የታለ?»

እምነት ከትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህርት ጋር የማስጠንቀቂያ ስብሰባ ነበራት። ራሂም ከባለሀብቶቹ የደረሰው አሳሳቢ ኢ-ሜይል በዓላማው ላይ እንዲያተኩር አድርጎታል። ጀምበሬ የአጎቶቿን ልጆች የፋሽን ሳምንት የማስጀመሪያ ዝግጅት ላይ በመጋበዝ ምሽታቸውን ብሩህ አድርጋለች። ግን እውነተኛ ማንነታቸውስ የታለ?

04-20
11:59

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 4«የመሮጫው መንገድ»

እምነት በእርግጥ ከዲጂታል ሱሰኝነት ጋር እየታገለች ልትሆን እንደምትችል ደርሰንበታል። ጀምበሬም ራሷን በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በምታያቸው ነገሮች በማነጻጸር ወጥመድ በመያዟ የነበራት በራስ መተማመን ወርዷል። ዥዋዥዌ ውስጥ የገባውን የእምነት ፤ ጀምበሬ እና ራሂምን ሕይወት እንዴት ይቀጥል ይሆን?

04-13
12:00

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 3«ማንቂያ»

እምነት በማስተማር ስራዋ ላይ ችግር ሊገጥማት እንደሚችል የተረዳች ይመስላል ። የራሂም ጅምር ህልምም አደጋ ላይ ነው። የጀምበሬ በራስ መተማመን ከምን ጊዜውም በላይ ወርዶ የታየበት ጊዜ ሆኗል። ለመሆኑ የወንድማማች ልጆቹ በእርግጥ በተናጥል የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች ይወጡት ይሆን?

04-06
12:00

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 2«ማለፍ»

ሃሳቧ ወደ ሌላ ቦታ እየተወሰደ የተቸገረችው እምነት ዳግም የተማሪዎቿን አመኔታ ታገኝ ይሆን ? ጀምበሬም ብትሆን በኢንተርኔት በምናብ የሳለችው ማንነት በቀጥታ በምታከናውነው ስራዎቿ ላይ ችግር ሊያመጣባት እንደሚችል እየታየ ነው። ህይወታቸውን እንዴት ሚዛናዊ ማድረግ ይችሉ ይሆን ?

03-30
12:00

«ከሱሰኝነት መመለስ»: ክፍል 1«ከእውነተኛው ዓለም ውጪ»

በዚህ “ከእውነተኛው ዓለም ውጪ” በሚለው ክፍል ሶስቱ የወንድማማች ልጆች በምናባዊ እና በገሃዱ ዓለም ለሕይወታቸው በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር ሲማሩ፤ የሚገጥማቸውን እንቅፋት እና ድል ቀርባችሁ እንድትመሰክሩ ተጋብዛችኋል። ምን ይገጥማቸው ይሆን?

03-23
11:29

የዲጂታል ግንዛቤ «ከሱሰኝነት መመለስ»ድራማ

ድራማው በሃያዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙት ሶስቱን የወንድማማች ልጆች በአንዲት አፍሪቃዊት ከተማ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያው እና ቴክኖሎጂው በየግል ሕይወታቸው እና በሞያቸው የሚያሳድርባቸውን የህይወት ውጣ ውረድ ለማሸነፍ የሚያደርጉት ጥረት ላይ ያተኩራል።

03-23
12:00

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 10 «ፍጻሜው»

እነጀምበሬ ራሳቸውን ለማስከበር መልሰው ግብግብ ገጥመዋል። ፍለጋቸው የት ያደርሳቸው ይሆን? በአሸናፊነት አጭበርባሪውን ማጋለጥ ይሳካላቸው ይሆን ወይስ አጭበርባሪው ሙልጭ አደርጎ ይዘርፋቸዋል?

03-16
11:59

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 9 «ግን እንዴት?»

እምነት ስልኳን ከተሰረቀች እና ጀምበሬ ብርቱ የስሜት ስብራት ከገጠማት በኋላ የሰርሳሪውን መኖሪያ ፈልጎ ማግኘት የመጀመሪያ እርምጃቸው ነበር። ፍለጋቸው በከተማው መሀል ወደሚገኝ የተገለለ መኖሪያ ቤት መርቷቸዋል። ነገር ግን አንዳች ተጨባጭ ነገር ከማግኘታቸው በፊት ግዙፍ አስፈሪ ውሻ አባሯቸዋል። ከዚያ ምን ተፈጠረ?

03-09
11:59

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 8«ሌላ መከራ»

ጀምበሬ፣ ራሒም እና እምነት የሰርሳሪውን ዱካ እየፈለጉ ነው። የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻቸውን ከተመሳሳይ ጥቃት ለመጠበቅ ፓስወርዶች ቀይረዋል። በጀመሩት ሥራ ምን ያህል ዘልቀው ይሆን? ጥቃት ፈጻሚው አሁንም በሕይወታቸው ጣልቃ እየገባ ነው ወይስ በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉት?

03-02
11:30

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 7«መልሶ ግብግብ»

ራሒም ላይ ያነጣጠረው አጭበርባሪ ሳይሳካለት ቀርቷል። አጭበርባሪው የጥቃት ስልቶቹን እና ፊቱን ለእኛ አድማጮች ገልጦልናል። እሱም ከጀምበሬ ጋር ለተወሰኑ ቀናት ግንኙነት ጀምሮ የነበረው አጎናፍር ነው። ጀምበሬ፣ እምነት እና ራሒም አጭበርባሪው ማን እንደሆነ እና ለምን እነሱ ላይ እንዳነጣጠረ ይደርሱበት ይሆን?

02-24
11:30

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 6 «ሰው አጥማጁ»

እምነት የቆጠበችውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በአጭበርባሪ ስትዘረፍ ጀምበሬ ከአባቷ ተለያይታለች። መጋቤ ኦንቾ አባቴ ብላ እንዳትጠራቸውም አውጀዋል። ጀምበሬ በጣም ተጎድታለች። እስካሁን ከዚህ የተረፈው ራሒም ብቻ ነው! በዚህ ይዘልቅ ይሆን?

02-17
11:30

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 4 «ወረራው»

እምነት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ስልኳ ተሰርቆ ተደናግጣ ነበር። ጀምበሬ በአንጻሩ የተሻለ ዕድል ገጥሟታል። ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለች። ሕይወት ጥሩ ይመስላል። ይኼ ዕድል ይዘልቅ ይሆን?

02-03
12:00

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 3 «ከሰዎች ሽሽት»

ጀምበሬ በማህበራዊ ሚዲያ 50,000 ተከታዮች በማፍራቷ ዘመዳሞቹ በጣም ተደስተዋል። ጀምበሬም በኦን ላይን ከተዋወቀችው ሰው መለያየቷ ከፈጠረባት ስሜት ያገገመች ትመስላለች። እርሱ ግን መለያየታቸውን እንዴት ተቀብሎት ይሆን?

01-27
11:30

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 2 «እንደ ዳክዬ ከጮኸ»

ከራሒም እና እምነት ጋር አንድ ላይ አብራ የምትኖረው እና በማህበራዊ ሚዲያ በምታገኘው ገቢ ኑሮዋን የምትመራው ጀምበሬ እና የአጎናፍር የፍቅር ግንኙነት ሳይጀመር በኢንዙና ከተማ በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ ያበቃ ይመስላል። በእርግጥ አብቅቶለት ይሆን?

01-20
11:59

«የአጭበርባሪው በቀል»: ክፍል 1«የመጨረሻው መጀመሪያ»

ጀምበሬ፣ እምነት እና ራሒም የወንድማማች ልጆች ቢሆኑም በባህሪያቸው እንደ ቀን እና ጭለማ የተለያዩ ናቸው። የዛሬውን ክፍል የምንጀምረው ከኢንዙና ከተማ ዳርቻ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ይሆናል።

01-13
10:59

Recommend Channels