እናትHood | EnatHood

EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile from http://enathood.com እናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል። ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ http://enathood.com ጦማር ነው።

ጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Healthy & non toxic living

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ ጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ተወያይተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ወይም ለቤተሰብ አካፍሉት።

06-13
01:16:14

የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ለራሳችን እና ለልጆቻችን ከሳይበር ደህንነት ባለሙያ ከሁስኒ አወል ጋር

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ከሆነው ሁስኒ አወል ጋር የራሳችን እና የልጆቻችንን የሳይበር ደህንነት እንዴት እንደምንጠብቅ ተነጋግረናል። ጠቃሚ መረጃዎች እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። ሁስኒ አወል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ነው። በአሁን ጊዜ ለToyota Financial Services በአማካሪነት እየሰራ ይገኛል። በኢትዮጵያ በግል እና የመንግስት የሳይበር ደህንነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለማህበረሰባችን በሙያው አገልግሎት ይሰጣል። #amharic #ethiopia #ethiopian #cybersecurity #enat #enathood

05-31
40:32

ከAyla’s የልጆች መጫወቻ እና መማሪያ አዘጋጅ ሳራ ሱከር Ayla’s Kids Learning Tools with Sara Suker #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናት

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ከሳራ ሱከር ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋና ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ ስለምታዘጋጃቸው ነገሮች ፣ ስለ ቢዝነስ እና ሌሎችም ነገሮች ተነጋግረናል። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሳራ የሁለት ልጆች እናት ናት። በቅርቡ የሙሉ ጊዜ ስራዋን በቤት ከልጆችዋ ጋር ለመሆን ወስና በቤት ቤተሰቧን እየተንከባከበች ትገኛለች። እንዲሁም ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ የሚሆኑ የተለያዮ በእጇ የምታዘጋጃቸውን ነገሮች ለገበያ ታቀርባለች። ስለገጠሟት ተግዳሮቶች ፣ ከእናትነት ልምዷ ፣ እና ሌሎችም ነገሮችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ!! Instagram : aylas_playthingz TikTok : Ayla's play thingz Phone no. 0966922080 Store location: Gurd shola, Holy City Center building, Ground floor G-08 #enathood #እናትhood #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናት #habesha #ethiopian #amharic #smallbusinessowner

05-14
40:32

ከሆስፒታል ዉጪ ለመውለድ ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ፤ ለምን? ከህይወቴ ታደሰ ጋር (MPH)

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በ ማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወልዳለች። እንኳን ደስ አለሽ እያልን በተከታታይ ስላካፈለችው ልምድ እናመሰግናታለን። ህይወቴ በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ​⁠ ታካፍላለች። በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሶስት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።

05-08
48:14

ወሊድ በአሜሪካ ከሆስፒታል ውጪ ፣ እናትነት ፣ ኑሮ በተለያየ አገር እና ጉዞ ከህይወቴ ታደሰ ጋር (ክፍል 1)

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ​⁠ ጋር ስለ ሶስተኛ እርግዝናዋ እንዴት ለወሊድ እየተዘጋጀች እንዳለች ፣ እናትነት ፣ በተለያዩ አገራትና ባህል ልጆችን ማሳደግ ፣ ወሊድ በሆስፒታል እና በማዋለጃ ማዕከል (birthing center) እና የመሳሰሉትን ነገሮች ተጨዋውተናል። መልካም ቆይታ። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች። ህይወቴ በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት። #ethiopian #habesha #amharic #ኢትዮጵያ #birth #childbirth #pregnancy

05-01
51:33

ኦቲዝምና ተመሳሳይ ኑሮሎጂክ መዛባትን የሚረዳ አመጋገብ / A diet that helps with Autism and related disorder

Our latest podcast opens the world of autism motherhood, where challenges meet triumphs, especially when raising a child with autism. Let’s discover together Sel Seyoum’s book on how a healing diet program tailored for autism can be a game-changer, offering crucial support and day to day management. From modern cities to remote corners of countries, families with children in the spectrum and related disorders find help and guidance in this dedicated book on nutrition, navigating the unique path of autism with strength and resilience. Buy “Autism Lifestyle” handbook on Amazon 👉🏽 https://a.co/d/f3roRxl 👉🏽 Sel’s Instagram : [https://www.instagram.com/selseyoum](https://www.instagram.com/selseyoum?utm_source=ig_web_button_share_sheet&igsh=ZDNlZDc0MzIxNw==)

04-24
01:10:29

የጥቁር እናት ነኝ ፀሀፊ እና ገጣሚ መሰረት ክንፈ ጋር የተደረገ ቆይታ - ስለ ኦቲዝም #autismawareness #enathood

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከመሰረት ክንፈ ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፥ ልዮ ፍላጎት ያለውን ልጅዋን ስታሳድግ የሚገጥማትን የለት ተለት ኑሮ ፥ ስለመፅሀፏ “የጥቁር እናት ነኝ” ፥ ስለምትሰራው የበጎ አድራጎት ስራ እና ሌሎችም ተጨዋውተናል። መሰረት ክንፈ “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ ፀሀፊ እና ገጣሚ ስትሆን የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናት። የመጀመሪያ ልጇ ኦትስቲክ ወይም ልዮ ፍላጎት ያለሁ በመሆኑ የገጠማትን ውጣ ውረድ ፥ የህይወት እይታዋን እና ትዝታዎችዋን በግጥም አስውባ በማቅረብ ትታወቃለች። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሃፍ ሽያጭ ለበጎ አድራጎት በማዋል በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቸረጉ እናቶችና ልጆችን እየረዳች ለብዙዎች መትረፍ ችላለች። መልካም ቆይታ። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ Amazon ላይ ይገኛል። 👉🏽 https://a.co/d/13Pp8Ys #ethiopia #amharic #ethiopian #autism #እናት #ኢትዮጵያ #habesha

04-09
01:29:07

ስለ ኦቲዝም ከሊያ ስዮም ከ Reaching Families ኘሬዝዳንት ጋር / Autism with Leah Seyum

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሊያ ስዩም የ Reaching Families Advocacy and Support Group መስራችና ኘሬዝዳንት ጋር ስለ ኦቲዝም (ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች) ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል። ሊያ የግል የእናትነት ጉዞዋን እንዲሁም እየመራች ያለችው የበጎ አድራጎት ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩ ስራዎች እና ማህበረሰባችን ስለ ኦቲዝም ማወቅ ያለበትን ሁሉ ከሙያ ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ✨ሊያ ስዩም የአራት ልጆች እናት ስትሆን ሁለቱ ልጆችዋ ኦትስቲክ ወይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ናቸው። በዚህም የተነሳ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን እና ወላጆችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርታ ዳላስ ቴክሳስን ጨምሮ በሌሎች ትላልቅ የአሜሪካ ግዛት ከተሞች ያሉ ኢትዮጵያን እና ኤርትራውያን ወገኖች በመደገፍ እና ድርጅቱን በኘሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ትገኛለች። #autismawareness #enathood Reaching Families Advocacy and Support Group Website 👉🏾 https://reachfamilies.org/ Facebook 👉🏾 https://www.facebook.com/groups/454918007982318/ YouTube 👉🏾 https://youtube.com/channel/UCPOeeQv6d9qvXNJ2Gl0_94Q

04-02
01:21:35

ስለ GAPS አመጋገብ እና በቤት ውስጥ ልጆችን ትምህርት ማስተማር ከሜላት ማሞ ጋር (MPH) ክፍል 2 - Gut & Psychology Syndrome

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ካለፈው የቀጠለ ዉይይት ከሜላት ማሞ ጋር ስለ GAPS አመጋገብና ልጆችን በቤት ውስጥ ስለማስተማር ተጨዋውተናል። ሜላት በተከታታይ ሁለት ክፍሎች የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሐሳብና አስተያየታችሁን ላኩልን። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች። ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!

03-17
31:07

ስለ GAPS አመጋገብ ፣ እናትነት እና ኑሮ በአቡዳቢ ከሜላት ማሞ (MPH, licensed ASCP)

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሜላት ማሞ ጋር ስለ እናትነት ፣ በቤት ውስጥ ሙሉ ጊዜ መሆንና ቤተሰብን መንከባከብ ፣ እና ስለ ኑሮ በአቡዳቢ ተጨዋውተናል። በሰፊው የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (**Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።** ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች። ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!

02-20
01:08:24

የቆዳ ውበት አጠባበቅ ፣ እራስን መንከባከብ እና እናትነት ከHanSim Skin ባለቤት ምልጃዬ ስሜ ጋር Skincare, Self-care, & Motherhood

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከምልጃዬ ስሜ የሃንሲም የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች - HanSim Skin መስራች እና ባለቤት ጋር የፊትና የሰውነታችን ቆዳ እንዴት መንከባከብ እንደምንችል ተወያይተናል። በተጨማሪም እራስን መጠበቅ እና እናትነት እንዴት አብሮ ማስኬድ ይቻላል የሚሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። የቢዝነስ ስራዎችዋን ከቤተሰብ ሃላፊነት ጋር እንዴት እንደምታስኬድ የግል ልምዷን ጨምራ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። የ HanSim ምርቶችን ለማግኘት:- HanSim Online Store 👉🏾 https://hansimskin.com/ በአዲስ አበባ የሚገኙ መሸጫና አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ:- 1. የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች መሸጫ :- ሌበኔዝ ህንፃ Lebenze Tower ጋዜቦ አደባባይ 1ኛ ፎቅ 2. Hansim Salon and Spa ሙሉ የፀጉር የውበት ሳሎን እና የቆዳ እንክብካቤ አገልግሎት :- ሆሊ ሲቲ ሴንተር Holy City Center 2ኛ ፎቅ ጉርድ ሾላ በስልክ ቁጥር 0931888855 ይደውሉ።

12-07
01:01:05

ፍጹም ተፈጥሮአዊ ወሊድ በዉሃ ውስጥ ፤ የሶስተኛ ልጃችን የወሊድ ታሪክ - Super Natural Water Birth

የዚህ ክፍል የእናትHood ፓድካስት ስለ ሶስተኛ ልጄ የወሊድ ታሪክ የተመለከተ ነው። የወለድኩት በወሊድ ማእከል/birthing center ውስጥ ያለ ምንም መድሀኒት ፣ ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ከሚድዋይፎች እገዛ ጋር ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ሰላም የሰፈነበት ወሊድ በዉሀ ዉስጥ ተሳክቶልኛል። ቪዲዮን መመልከት ከፈለጋችሁ በYouTube ታገኙታላችሁ።

11-15
12:20

የወሊድን ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ Childbirth with Epidural Anesthesia vs without

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የወሊድ ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ (Epidural Anesthesia) ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ በሚል በሁለቱም መንገድ ያለኝ ልምድ አካፍያለሁ። የመጀመሪያ ልጄን በኢፒዱራል አንስቴዚያ ስወልድ ያጋጠመኝን ፤ ሁለተኛ ልጄን ያለምንም መድሀኒት ስወልድ የነበረውን ሁኔታ በንፅፅር እና ሶስተኛ ለመውለድ እንዴት እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ጨምሮ ተያያዝ ነገሮችን አንስቻለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም ጊዜ!! 👉🏾  Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia with Dr. Betelehem M. Asnake, MD – ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ 👉🏾  The Mama Natural Week-by-Week Guide to Pregnancy and Childbirth 👉🏾  Christian Hypo Birthing

09-30
16:49

ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ከዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር - Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል አንስቲዚኦሎጂስት ከሆነችው ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ/Epidural Anesthesia ማለትም በአብዛኛው ጊዜ በወሊድ እና በቀዶ ጥገና ጊዜ ስለሚሰጠው የማደንዘዣ መድሀኒት ተወያይተናል። ሙያዊ ልምዷን ጨምራ በኢፒዶራል አንስቴዚያ ዙሪያ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስና ማብራሪያ ሰጥታናለች። መልካም ቆይታ። Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologist and anesthesia global health director at the University of California Los Angeles. 👉🏾 Dr. Betelehem M. Asnake, MD - https://www.uclahealth.org/providers/betelehem-asnake She is  also a founder and manager of Mulu Mentor, which helps underrepresented and disadvantaged pre-medical students navigate the medical school application process through targeted mentorship. 👉🏾 Mulu Mentor - https://www.mulumentor.com/

09-15
01:09:47

በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት - Breastfeeding during Pregnancy and Tandem Nursing

በሶስት አመት የጡት ማጥባት ጉዞዬ ውስጥ ያደረግኩት በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት ብዙ ጥያቄና አስተያየት ያስተናገድኩበት ነው። ሳይንስ የሚለውን እና የራሴን ልምድ በዚህ ክፍል አካፍያለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። 💫 ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። 🌟 የቀደሙ የጡት ማጥባት ዉይይቶች 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለልጆች https://youtu.be/WodjPq3RHJE?si=Pw9CGJajEzNrfeCs 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለእናቶች https://youtu.be/TVHwglULAD4?si=oKG_ePx44sxwLHQb 👉🏾 የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች https://youtu.be/YXb-DU9u2hM

09-02
28:03

የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች ከብርቱካን አሊ (CRNA, DNP) - Breast Milk Pumping Best Practice

የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በተከታታይ የጡት ማጥባት ዉይይቶችን እያደረግን በመሆኑ ከአድማጮች የተነሱ ስለ ጡት ወተት ማለብ እና አቆይቶ መጠቀም ጥያቄዎችን ከብርቱካን አሊ ጋር በመወያየት ከልምድና ከሙያዋ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ብርቱካን የሶስት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ Certified Registered Nurse Anesthetist, (CRNA DNP) ማለትም ነርስ እና የማደንዘዣ ወይም የሰመመን መድሀኒት ሰጪ ናት። 🌟 በውይይታችን የተጠቀሱ ጡት ወተት ማለቢያ እና ማስቀመጫ - Medela Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ https://www.medela.us/breastfeeding/products/breast-pumps - Spectra Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ - [https://www.spectrababyusa.com](https://www.spectrababyusa.com/) - Elvie Hand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - https://www.elvie.com/en-us/shop/elvie-pump - WillowHand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - [https://onewillow.com](https://onewillow.com/) - Mason Jar 4 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG - Mason Jar 8 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG - Pack It Ice Bag / የበረዶ ቦርሳ - https://amzn.to/3KXtJXE - Breast Milk Warmer / የጡት ወተት ማሞቂያ - https://amzn.to/3Ebcfn0

08-27
01:00:14

የእናት ጡት ወተት ጥቅም ለልጆች ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Benefits of Breast Milk for Children

የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ የእናት ጡት ወተት ለልጆች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። እናም ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። በተጨማሪም በህይወቴ የYouTube channel ላይ ጡት ማጥባት ለእናቶች ያለውን ጥቅም። ተወያይተናል። በጣም ጥሩ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንደተመለከቱት እጋብዛችሁአለሁ። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። 💫ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።

08-13
01:16:07

የእናቶች ታሪክ በአለም ዙሪያ - ረቂቅ አዕምሮ ከዳላስ (Mother's Stories Around the World)

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ረቂቅ አዕምሮ የእናትነት ጉዞዋ አካፍላናለች። እናትነት ለሷ ምን ማለት እንደሆነ ፣ የዕለት ተለት ስኬትና ተግዳሮቶችን ጨምሮ እና ኑሮ በዳላስ ቴክሳስ ምን እንደሚመስል አጫውታናለች። መልካም ቆይታ። ረቂቅ አዕምሮ የአንድ ቆንጆ ሴት ልጅ እናት ናት። ከባለቤቷ እና ከልጇ ጋር በቴክሳስ ዳላስ ትኖራለች። ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጇን እና ቤተሰቧን ትንከባከባለች።

07-28
01:21:48

ልጆች ተኮር አመጋገብ (Baby - Led Weaning) ከጊፍቲ ባዮ ጋር የተደረገ ቆይታ

በዛሬው የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከጊፍቲ ባዮ ጋር ቆይታ ይኖረናል። ዉይይታችን የህፃናት ልጆች አመጋገብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ህፃናት ልጆች በተለይም ከስድስት ወር በኃላ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናስጀምራለን? ምን አይነት የአመጋገብ ዘዴዎች አሉ? ፣ እንዲሁም እንዴት ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ እንችላለን? እና ህፃናት እራሳቸውን መመገብ እንዲችሉ እንዴት መርዳት እንምንችል ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን እናነሳለን።

05-23
01:06:14

እናትHood ፖድካስት - እንኳን ደህና መጣችሁ!! Welcome to EnatHood!!

እናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል። ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ enathood.com ጦማር ነው። EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile from enathood.com.

05-05
03:14

Recommend Channels