Discover
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Author: SBS
Subscribed: 132Played: 9,231Subscribe
Share
© Copyright 2025, Special Broadcasting Services
Description
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
783 Episodes
Reverse
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 31 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ በአየር መንገዶች የማስፈፀም አቅም ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነ
ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ከእዚህ ዓለም በሞት ስለ ተለዩት የሁለት መንታ ሴት ልጆች አባት አቶ ሩፋኤል ተሰማ፤ መልካም ሰብዕና እና ትውስታዎችን ነቅሰው የቅርብ ወዳጆችና የትግል አጋሮች በስንብት ቃሎቻቸው ይዘክራሉ።
አቶ በፈቃዱ ወለሎ፤የ Bef Homes Australia መሥራችና ባለቤት፤ ድርጅታቸው በምዕራብ አውስትራሊያ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ስለሚሰጣቸው አግልግሎቶች ይናገራሉ። የመኖሪያና ሙዋዕለ ንዋይ ቤት ግዢና ሽያጭ መንገዶችን ያመላክታሉ።
አውስትራሊያ ለመቅረት ጥገኝነት ከጠየቁት ሁለት ተጨማሪ የኢራን የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ውስጥ አንደኛይቱ ሃሳቧን ቀይራ ወደ ኢራን ልትመለስ ነው።
እያደገ የመጣውን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ራሱን በቻለ ተቋም ለማስተዳደር መታቀዱ ተገለጠ
ዴቪድ ሊትልፕራውድ ከናሽናልስ ፓርቲ መሪነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ
41 ሀገራት የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች የተመለከተ ማሳሰቢያ ሰጡ
የፖለቲካ አንቂ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ቀስቃሽ፣ የቀድሞው የዲሞክራት ፓርቲ የሁለት ዙር ዕጩ ፕሬዚደንት ጄሲ ጃክሰን የወጣቶች ኮሚቴ ሰብሳቢና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ የሐረወርቅ ጋሻው፤ ፌብሪዋሪ 17 ቀን 2026 ከእዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ጄሲ ጃክሰን ፕሬዚደንታዊ የምርጫ ዘመቻ ወቅት ስላበረከቷቸው አስተዋፅዖዎች አንስተው ይናገራሉ። የጃክሰንን ሰብዓዊ ገፅታም ይዘክራሉ።
Learn useful English for talking about small wins at work. Practise phrases for celebrating achievements, staying motivated, and making progress step by step. - በሥራ ቦታ ስለ አነስተኛ የአሸናፊነት ውጤት ለመናገር ጠቃሚ እንግሊዝኛን ይማሩ። ስኬቶችን የማክበር፣ በከፍተኛ ተነሳሽነት መዝለቅንና ደረጃ በደረጃ ዕድገት የማስየትን ቃለ ሐረጎች ይለማመዱ።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ኢራን ጦርነት ከሳምንታት ዐልፎ ለተራዘመ ጊዜያት ሊዘልቅ እንደሚችል አመላከቱ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ዓለም ያሉ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትን ለማገልገል የሚያስችሉትን አዳዲስ አሠራሮች ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታወቀ
ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ በተባባሪ ደራሲነት ለሕትመት ስላበቁት "The Many Lives of Tesfa Seyon: An Ethiopian Intellectual in Early Modern Rome" መፅሐፋቸው አንኳር ይዘቶች ያስረዳሉ።
ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ በተባባሪ ደራሲነት ለሕትመት ስላበቁት "The Many Lives of Tesfa Seyon: An Ethiopian Intellectual in Early Modern Rome" መፅሐፋቸው አንኳር ይዘቶች ያስረዳሉ።
የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አዘጋጅነት ሜልበርን ከተማ ውስጥ ተከብሮ ስለዋለው የ130ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ትሩፋቶች አንስተው ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ትምህርትን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለመስጠት ወጠነች
ሥነ ግጥም በጃዝ አዳዲስ ገጣሚያንን አካትቶ በሜልበርን - አውስትራሊያ አሰልሶ ተካሔደ።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንትና ተዋናይ ጌታሁን ይርጉ፤ ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 28 / የካቲት 21 በሜልበርን ከተማ - አውስትራሊያ 21 Yardley St, Maidstone ከ4:00 pm - 6:00 pm ስለሚከበረው 130ኛው የአድዋ ክብረ በዓል መሰናዶና ዝግጅቶች ይናገራሉ። ማኅበረሰባዊ ጥሪም ያቀርባሉ።
በአውስትራሊያ፣ በኒውዚላንድ፣ በፊጂ፣ በፓፕዋ ኒው ጊኒ እና በሰሎሞን ደሴቶች የኢፌዴሪ ጥብቅ አምባሳደር አንዋር ሙክታር፤ 130ኛውን የአድዋ ድል አስመልክተው የክብረ በዓሉን ታላቅነትና ልዩ ብሔራዊ መገለጫነት ያመላክታሉ። የሀገራዊ አንድነትና ትብብር ጥሪም ያቀርባሉ።
ኢትዮጵያ ኃይሏን የምትገነባው በቀጠናው ሽብር እንዳይፈጠር ለመከላከል እንደሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመላከቱ
ግጥም - ጌትነት እንየው *** ድምፅ - ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና























