DiscoverSBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Claim Ownership

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Author: SBS

Subscribed: 129Played: 8,653
Share

Description

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
633 Episodes
Reverse
ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ ከነዳጅና ናፍጣ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መኪና ሽግግርን ፋይዳዎች በንፅፅሮሽ አንስተው ያስረዳሉ።
የኢሬቻ ክብረ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ኦቦ አብደታ ሆማ እና ኦቦ በንቲ ኦሊቃ፤ እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 በ Wilson Botanic Park Berwick ተከብሮ ስለሚውለው የኢሬቻ ክብረ በዓል ሥነ ሥርዓትና ሂደት ይናገራሉ። የአብረን እንታደም የጥሪ ግብዣም ያቀርባሉ።
አባቴ በእኔ ስኬት ውስጥ ታላቅ ስፍራ አለው ፤ ዩኒቨርሳል ሙዚቃ ያቀረበልኝን ውል ስፈርም በእነሱ ቅድመ ሁኔታ ስይሆን በእኔ ምርጫ የተሻለ ውል እንድፈርም የረዳኝ የአባቴን ምክር እና የሕይወት ፍልስፍና መስማቴ እና መከተሌ ነው ፤ ይለናል ሁለገቡ አርቲስት ድምጻዊ ፤ ገጣሚ ፤ አቀናባሪ ፤ ዲጄ እንዲሁም ድምጻዊ ሮፍናን ኒሪ ሙዘይን ነው ።
የመንፈሳዊ ሕይወትና የበጎ አድራጎት አገልጋይዋ ፓስተር ደሲ ባይሳ ከእዚህ ዓለም በሕልፈት ተሰናብተዋል። "አታልቅስ፤ ነገ ይነጋል" ነበር የመጨረሻ ቃሏ ያሉትን ታላቅ ወንድማቸውን ተክሉ ባይሳ አክሎ፤ ቤተስብና ወዳጆች ጥልቅ ሐዘናቸውን ይገልጣሉ። የፓስተር ደሲ የቀብር ሥነ ሥርዓት እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 ከቀኑ 2:00 pm በ Bulla Cemetery Lane, Bulla ይፈፀማል።
የሙዚቀኛ ውጤት የሚታየው በሚዚቀኛው ጥረት ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ የአስተሳሰብ አቅጣጫ ነው ። አገር ሰላም ሲሆን ማህበረሰብ ሲራጋጋ የኪነጥበብ ባለሙያዎችም ጥሩ ስራን ይዘን መቅረብ እንችላላን፤ የሚለን የሙዚቃ ስራውን በአውስትራሊያ እያሳየ ያለው ሁለገቡ አርቲስት ድምጻዊ ፤ ገጣሚ ፤ አቀናባሪ ፤ ዲጄ እንዲሁም ድምጻዊ ሮፍናን ኒሪ ሙዘይን ነው ።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጋዛ የእስራኤልን ወረራን ተቃወሙ
የኢትዮጵያውያን 2018 አዲስ ዓመት አከባበር በኬንሲንግተን ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሜልበርን አውስትራሊያ።
እስራኤል የፍርስጤማውያንን ነጻ አገር የመሆን ጥያቄ መቼውንም ቢሆን እውቅናን አልሰጥም አለች፤
" ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ
በሕይወት ዘመናቸው "ኤርትራውያን ጀግናዎች ናቸው፤ ጥሩ ተዋጊዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ስር ወድቀዋል። "አንድነት ኢትዮጵያ" ብለው የሔዱ ናቸው" ያሉን የቀድሞው የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ፣ የብሔራዊ ውትድርና መምሪያ ኃላፊና የ "ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር" መጽሐፍ ደራሲ ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ተለይተዋል። ዝክረ መታሰቢያ ይሆናቸውም ዘንድ ቀደም ሲል በወርኃ ኖቬምበር 2014 ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ ደግመን አቅርበናል።
ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 በ Kensington Town Hall በማኅበሩ አስተባባሪነት ስለሚከበረው የ2018 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ይገልጣሉ።
እስከ አንድ ወር ጊዜ ይወስድ የነበረውን አዲስ የንግድ ምዝገባና ዕድሳት አሠራርን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል በመቀየር በሁለት ቀናት መጨረስ የሚያስችል ሥርዓት ይፋ ተደረገ
የኢትዮ - አውስትራሊያ አንድነት ዕድር ሰብሳቢ አቶ መስቀሉ ደሴ፣ ፀሐፊ ብሩክ ይማ እና የበዓል አስተባባሪ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ይልማ፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2018 እና የመስቀል በዓል በጣምራ ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰብ አባላት ጋር በፐርዝ ከተማ Koondoola Community Centre ለማክበር ስላሰናዱት የበዓል ዝግጅት ፕሮግራም ይናገራሉ። የአንድነት ጥሪም ያቀርባሉ።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሔደው ጦርነት ሳቢያ በኢትዮጵያ ላይ ጥለውት የነበረውን የተለያዩ ዕቀባዎችን የያዘው ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ፤ በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ፀንቶ እንዲቆይ ተወሰነ
ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ ስለምን የሶስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ የምርምር ፅሁፋቸውን ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ አውጥተው "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ስያሜ ለመፅሐፍነት ለማብቃት እንደወደዱ ያነሳሉ፤ ጭብጦቹንም ነቅሰው ይናገራሉ።
የ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ መፅሐፋቸው ውስጥ ያሠፈሯቸውን አንኳር ምክረ ሃሳቦች ፋይዳ ነቅሰው ያስገነዝባሉ።
ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ለሕትመት ስላበቁት መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ይናገራሉ።
የ"ክብረ በዓላት፤ ሃይማኖትና ባሕል" መፅሐፍ ደራሲ መላኩ ጌታቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘመን ቅመራና ባሕላዊ አከባበር ያስረዳል።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋብት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
loading
Comments