DiscoverእናትHood | EnatHood
እናትHood | EnatHood
Claim Ownership

እናትHood | EnatHood

Author: Hana Haile

Subscribed: 1Played: 0
Share

Description

EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile from http://enathood.com

እናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል። ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ http://enathood.com ጦማር ነው።
21 Episodes
Reverse
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ ጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ተወያይተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ወይም ለቤተሰብ አካፍሉት።
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በ ማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወልዳለች። እንኳን ደስ አለሽ እያልን በተከታታይ ስላካፈለችው ልምድ እናመሰግናታለን። ህይወቴ በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ​⁠ ታካፍላለች። በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሶስት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ​⁠ ጋር ስለ ሶስተኛ እርግዝናዋ እንዴት ለወሊድ እየተዘጋጀች እንዳለች ፣ እናትነት ፣ በተለያዩ አገራትና ባህል ልጆችን ማሳደግ ፣ ወሊድ በሆስፒታል እና በማዋለጃ ማዕከል (birthing center) እና የመሳሰሉትን ነገሮች ተጨዋውተናል። መልካም ቆይታ። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች። ህይወቴ በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት። #ethiopian #habesha #amharic #ኢትዮጵያ #birth #childbirth #pregnancy
Our latest podcast opens the world of autism motherhood, where challenges meet triumphs, especially when raising a child with autism. Let’s discover together Sel Seyoum’s book on how a healing diet program tailored for autism can be a game-changer, offering crucial support and day to day management. From modern cities to remote corners of countries, families with children in the spectrum and related disorders find help and guidance in this dedicated book on nutrition, navigating the unique path of autism with strength and resilience. Buy “Autism Lifestyle” handbook on Amazon 👉🏽 https://a.co/d/f3roRxl 👉🏽 Sel’s Instagram : [https://www.instagram.com/selseyoum](https://www.instagram.com/selseyoum?utm_source=ig_web_button_share_sheet&igsh=ZDNlZDc0MzIxNw==)
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከመሰረት ክንፈ ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፥ ልዮ ፍላጎት ያለውን ልጅዋን ስታሳድግ የሚገጥማትን የለት ተለት ኑሮ ፥ ስለመፅሀፏ “የጥቁር እናት ነኝ” ፥ ስለምትሰራው የበጎ አድራጎት ስራ እና ሌሎችም ተጨዋውተናል። መሰረት ክንፈ “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ ፀሀፊ እና ገጣሚ ስትሆን የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናት። የመጀመሪያ ልጇ ኦትስቲክ ወይም ልዮ ፍላጎት ያለሁ በመሆኑ የገጠማትን ውጣ ውረድ ፥ የህይወት እይታዋን እና ትዝታዎችዋን በግጥም አስውባ በማቅረብ ትታወቃለች። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሃፍ ሽያጭ ለበጎ አድራጎት በማዋል በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቸረጉ እናቶችና ልጆችን እየረዳች ለብዙዎች መትረፍ ችላለች። መልካም ቆይታ። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ Amazon ላይ ይገኛል። 👉🏽 https://a.co/d/13Pp8Ys #ethiopia #amharic #ethiopian #autism #እናት #ኢትዮጵያ #habesha
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሊያ ስዩም የ Reaching Families Advocacy and Support Group መስራችና ኘሬዝዳንት ጋር ስለ ኦቲዝም (ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች) ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል። ሊያ የግል የእናትነት ጉዞዋን እንዲሁም እየመራች ያለችው የበጎ አድራጎት ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩ ስራዎች እና ማህበረሰባችን ስለ ኦቲዝም ማወቅ ያለበትን ሁሉ ከሙያ ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ✨ሊያ ስዩም የአራት ልጆች እናት ስትሆን ሁለቱ ልጆችዋ ኦትስቲክ ወይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ናቸው። በዚህም የተነሳ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን እና ወላጆችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርታ ዳላስ ቴክሳስን ጨምሮ በሌሎች ትላልቅ የአሜሪካ ግዛት ከተሞች ያሉ ኢትዮጵያን እና ኤርትራውያን ወገኖች በመደገፍ እና ድርጅቱን በኘሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ትገኛለች። #autismawareness #enathood Reaching Families Advocacy and Support Group Website 👉🏾 https://reachfamilies.org/ Facebook 👉🏾 https://www.facebook.com/groups/454918007982318/ YouTube 👉🏾 https://youtube.com/channel/UCPOeeQv6d9qvXNJ2Gl0_94Q
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ካለፈው የቀጠለ ዉይይት ከሜላት ማሞ ጋር ስለ GAPS አመጋገብና ልጆችን በቤት ውስጥ ስለማስተማር ተጨዋውተናል። ሜላት በተከታታይ ሁለት ክፍሎች የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሐሳብና አስተያየታችሁን ላኩልን። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች። ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሜላት ማሞ ጋር ስለ እናትነት ፣ በቤት ውስጥ ሙሉ ጊዜ መሆንና ቤተሰብን መንከባከብ ፣ እና ስለ ኑሮ በአቡዳቢ ተጨዋውተናል። በሰፊው የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (**Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።** ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ!! ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት። በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች። ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከምልጃዬ ስሜ የሃንሲም የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች - HanSim Skin መስራች እና ባለቤት ጋር የፊትና የሰውነታችን ቆዳ እንዴት መንከባከብ እንደምንችል ተወያይተናል። በተጨማሪም እራስን መጠበቅ እና እናትነት እንዴት አብሮ ማስኬድ ይቻላል የሚሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። የቢዝነስ ስራዎችዋን ከቤተሰብ ሃላፊነት ጋር እንዴት እንደምታስኬድ የግል ልምዷን ጨምራ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። የ HanSim ምርቶችን ለማግኘት:- HanSim Online Store 👉🏾 https://hansimskin.com/ በአዲስ አበባ የሚገኙ መሸጫና አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ:- 1. የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች መሸጫ :- ሌበኔዝ ህንፃ Lebenze Tower ጋዜቦ አደባባይ 1ኛ ፎቅ 2. Hansim Salon and Spa ሙሉ የፀጉር የውበት ሳሎን እና የቆዳ እንክብካቤ አገልግሎት :- ሆሊ ሲቲ ሴንተር Holy City Center 2ኛ ፎቅ ጉርድ ሾላ በስልክ ቁጥር 0931888855 ይደውሉ።
የዚህ ክፍል የእናትHood ፓድካስት ስለ ሶስተኛ ልጄ የወሊድ ታሪክ የተመለከተ ነው። የወለድኩት በወሊድ ማእከል/birthing center ውስጥ ያለ ምንም መድሀኒት ፣ ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ከሚድዋይፎች እገዛ ጋር ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ሰላም የሰፈነበት ወሊድ በዉሀ ዉስጥ ተሳክቶልኛል። ቪዲዮን መመልከት ከፈለጋችሁ በYouTube ታገኙታላችሁ።
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የወሊድ ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ (Epidural Anesthesia) ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ በሚል በሁለቱም መንገድ ያለኝ ልምድ አካፍያለሁ። የመጀመሪያ ልጄን በኢፒዱራል አንስቴዚያ ስወልድ ያጋጠመኝን ፤ ሁለተኛ ልጄን ያለምንም መድሀኒት ስወልድ የነበረውን ሁኔታ በንፅፅር እና ሶስተኛ ለመውለድ እንዴት እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ጨምሮ ተያያዝ ነገሮችን አንስቻለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም ጊዜ!! 👉🏾  Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia with Dr. Betelehem M. Asnake, MD – ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ 👉🏾  The Mama Natural Week-by-Week Guide to Pregnancy and Childbirth 👉🏾  Christian Hypo Birthing
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል አንስቲዚኦሎጂስት ከሆነችው ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ/Epidural Anesthesia ማለትም በአብዛኛው ጊዜ በወሊድ እና በቀዶ ጥገና ጊዜ ስለሚሰጠው የማደንዘዣ መድሀኒት ተወያይተናል። ሙያዊ ልምዷን ጨምራ በኢፒዶራል አንስቴዚያ ዙሪያ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስና ማብራሪያ ሰጥታናለች። መልካም ቆይታ። Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologist and anesthesia global health director at the University of California Los Angeles. 👉🏾 Dr. Betelehem M. Asnake, MD - https://www.uclahealth.org/providers/betelehem-asnake She is  also a founder and manager of Mulu Mentor, which helps underrepresented and disadvantaged pre-medical students navigate the medical school application process through targeted mentorship. 👉🏾 Mulu Mentor - https://www.mulumentor.com/
በሶስት አመት የጡት ማጥባት ጉዞዬ ውስጥ ያደረግኩት በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት ብዙ ጥያቄና አስተያየት ያስተናገድኩበት ነው። ሳይንስ የሚለውን እና የራሴን ልምድ በዚህ ክፍል አካፍያለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። 💫 ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። 🌟 የቀደሙ የጡት ማጥባት ዉይይቶች 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለልጆች https://youtu.be/WodjPq3RHJE?si=Pw9CGJajEzNrfeCs 👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለእናቶች https://youtu.be/TVHwglULAD4?si=oKG_ePx44sxwLHQb 👉🏾 የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች https://youtu.be/YXb-DU9u2hM
የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በተከታታይ የጡት ማጥባት ዉይይቶችን እያደረግን በመሆኑ ከአድማጮች የተነሱ ስለ ጡት ወተት ማለብ እና አቆይቶ መጠቀም ጥያቄዎችን ከብርቱካን አሊ ጋር በመወያየት ከልምድና ከሙያዋ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ብርቱካን የሶስት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ Certified Registered Nurse Anesthetist, (CRNA DNP) ማለትም ነርስ እና የማደንዘዣ ወይም የሰመመን መድሀኒት ሰጪ ናት። 🌟 በውይይታችን የተጠቀሱ ጡት ወተት ማለቢያ እና ማስቀመጫ - Medela Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ https://www.medela.us/breastfeeding/products/breast-pumps - Spectra Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ - [https://www.spectrababyusa.com](https://www.spectrababyusa.com/) - Elvie Hand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - https://www.elvie.com/en-us/shop/elvie-pump - WillowHand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - [https://onewillow.com](https://onewillow.com/) - Mason Jar 4 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG - Mason Jar 8 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG - Pack It Ice Bag / የበረዶ ቦርሳ - https://amzn.to/3KXtJXE - Breast Milk Warmer / የጡት ወተት ማሞቂያ - https://amzn.to/3Ebcfn0
የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ የእናት ጡት ወተት ለልጆች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። እናም ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። በተጨማሪም በህይወቴ የYouTube channel ላይ ጡት ማጥባት ለእናቶች ያለውን ጥቅም። ተወያይተናል። በጣም ጥሩ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንደተመለከቱት እጋብዛችሁአለሁ። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። 💫ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ረቂቅ አዕምሮ የእናትነት ጉዞዋ አካፍላናለች። እናትነት ለሷ ምን ማለት እንደሆነ ፣ የዕለት ተለት ስኬትና ተግዳሮቶችን ጨምሮ እና ኑሮ በዳላስ ቴክሳስ ምን እንደሚመስል አጫውታናለች። መልካም ቆይታ። ረቂቅ አዕምሮ የአንድ ቆንጆ ሴት ልጅ እናት ናት። ከባለቤቷ እና ከልጇ ጋር በቴክሳስ ዳላስ ትኖራለች። ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጇን እና ቤተሰቧን ትንከባከባለች።
በዛሬው የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከጊፍቲ ባዮ ጋር ቆይታ ይኖረናል። ዉይይታችን የህፃናት ልጆች አመጋገብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ህፃናት ልጆች በተለይም ከስድስት ወር በኃላ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናስጀምራለን? ምን አይነት የአመጋገብ ዘዴዎች አሉ? ፣ እንዲሁም እንዴት ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ እንችላለን? እና ህፃናት እራሳቸውን መመገብ እንዲችሉ እንዴት መርዳት እንምንችል ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን እናነሳለን።
እናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው። እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል። ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ enathood.com ጦማር ነው። EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for. It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices. It is brought to you by Hana Haile from enathood.com.
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከቤተልሔም ፀጋዬ ጋር በቤት ውስጥ ልጆችን በሙሉ ሰዓት ማስተማር ፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ መሆን እና ልጆችን ከስክሪን (ከቲቪ እና ከስልክ) ነፃ አድርጎ ስለማሳደግ ተነጋግረናል። ቤተልሔም ብዙ ጠቃሚና አነቃቂ መረጃዎችን ከወላጅነት ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ቤተልሔም የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ልጆችዋን በሙሉ ጊዜ በቤትዋ ት/ቤት ሳትልክ ታስተምራለች። ልጆችዋ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከዛም ጋር በተገናኘ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማርያ የርቀት (በዙም) የምታስተምርበት ፋኖስ የሚባል ማስተማርያ አላት። በተጨማሪም ቤተልሔም የልጆች መማርያ መፅሀፍትንም ታዘጋጃለች። ከፋኖስ ድህረ ገፅ እነዚህን የአማርኛ መማርያ መፅሀፋትና ሌሎች መርጃ መሳሪያዎች ታገኛላችሁ። ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ። 👉🏾 https://www.myfanos.com/
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከረድኤት እንዳለው ጋር ስለ ሚድዋይፈሪ (Midwifery) አገልግሎት ተወያይተናል። ለሴቶች እና እናቶች የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲሁም በእርግዝና እና ወሊድ ጊዜ የሚድዋይፍ (Midwife) የሚሰጡትን እገዛ ጨምሮ ሌሎችም መረጃዎች አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ረድኤት እንዳለው በኢትዮጵያ የምትኖር ሚድዋይፍ (Clinical midwife, Msc) ናት። በአቻሞ ዩንቨርስቲ አስተማሪ ናት። እማ ዛሬ (Ema Zaire) በሚባል የYoutube channel ስለእናቶች እና የልጆች ጤና ጠቃሚ መረጃዎችን ታካፍላለች። እዚህ ጋር ልታገኙት ትችላላችሁ 👉🏾 https://youtube.com/@emazare6315
loading
Comments 
Download from Google Play
Download from App Store