Discoverዜና መጽሔት
ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Author: DW

Subscribed: 4Played: 428
Share

Description

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
686 Episodes
Reverse
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ -ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ፣ሴቶችን በጅምላ የመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መክሰሱ ፣ -ነገ ስለሚጀመረው የመራጮች ምዝገባ የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች፣ -በኢትዮጵያ በኬንያና በሶማሊያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለድርቅ መጋለጣቸው -ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የ"አንድ ቀን ውድድር" እንደምታዘጋጅ መገለጹ
የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን 41 ሐገሮች በኢትዮጵያ ያለውን የመናገር ነጻነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሞሽን በአርሲ ስለተገደሉ ዜጎች ያወጣውን መግለጫ፤ ከራያ አላማጣ፣ ኮረምና ኦፍላ ዛታ የተፈናቀሉ ወገኖች የዕርዳታ ጥሪ፤ በምዕራባዊ የሐገሪቱ ክፍል ከመደበኛ በላይ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው የነዳጅ ዕጥረት እንዲሁም የድሬደዋ ስታድየም - የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ጋር የሚያደርገውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንዲያስተናግድ መወሰኑ" የተሰኙትን ጉዳዮች ያስቃኘናል
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ያገረሸው ጸጥታ ችግር፤ በአማራ ክልል የሚካሄደው ውጊያ ወጣቶች ላይ ያስከተለው ተጽዕኖ፤ ምርጫ ቦርድ በ5 የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ለቀረበበት ክስ ለፍርድ ቤት ምላሽ ማቅረቡ፤ የሱዳን መከላከያ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ክስ አንድምታ
በዛሬው የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ ለታቀደዉ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማሕበራት ድርጅቶችን ዝግጅቶች የሚቃኙ ሁለት ዘገባዎችን ፣ የአድዋ ድል 130ኛ ዓመት ዝክር በፓሪስ የሚመለከት ዘገባ የእስራኤልና የአሜሪካ ድብደባና የኢራን አፀፋን የሚመለከት አጭር ቃለ መጠይቅም ተካቷል።
130ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በድሉ መታሰቢያ ማዕከል ተከብሯል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን የጅምላ እልቂት አውግዛለች፣  አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራንን አጸፋንና አውሮጳን እንዲሁም ጦርነቱ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በቀጥታ ሊጎዳ ይችላሉ መባሉ
በዛሬው የዜና መጽሔት "በንጹሓን ላይ የሚሰነዘር" ያለው ጥቃት "እያደር ከብዷል" ሲል ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መግለጫ ማዉጣቱ፣ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና ሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ወረዳዎች፣ በተለይም በኤፍራታ ግድም እና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የተከሰተ ግጭት ፣ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በኦሮምያ ክልል ስለመጭዉ ምርጫ ምን አስተያየት አላቸዉ ነዋሪዎችን አነጋግረናል። አሜሪካ በኢራን ላይ ልትፈጸም የምትችለው ጥቃት የምሽቱ ዜና መጽሔት የያዘዉ ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።
በዛሬው መጽሔታችን አምስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ብሔራዊ ምርጫ በ5 የምርጫ ክልሎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" መታዘዙ፤ ክራይሲስ ግሩፕ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ውዝግብ ያቀረበው ምክረ-ሀሳብ፤ 2025 በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ "ሰፊ እሥራቶች፣ አፈናዎች እና ትንኮሳዎች የተጋረጡበት" ነበር መባሉl ፤ «የምግብ ድጋፍ ተነፈግን» ያሉ ተፈናቃዮች ለከፋ ስቃይ ተዳርገናል ማለታቸው ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።
-የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንት ፍቃዱን የሰረዘበት አዲስ ስታንዳርድ ሥራዉን አለማቋረጡን አስታወቀ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ትናንት ባሰራጨዉ ደብዳቤ የአዲስ ስታንዳርድ የምሥክር ወረቀት መሰረዙን አሰታዉቆ ነበር።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ያደረጉት ዓመታዊ የመርሕ ንግግር በአብዛኛዉ ሐሰትን ከዕዉነት የቀየጠ መሆኑን አጥኚዎችና ተንታኞች አስታወቁ።ትራምፕ በኢራን ላይ የሰነዘሩት ዛቻም ከቴሕራን ጠንካራ አፀፋ ገጥሞታል። --በግሪጎሪያኑ አምና 2025፣ 129 ጋዜጠኞች መገደላቸዉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ CPJ አስታወቁ።አብዛኞቹን ጋዜጠኞች የገደለችዉ እስራኤል ናት።
ዜና መጽሔት የአፍሪካ ቀንድ ለውጭ ኃይላት ፍላጎት ማስፈፀሚያነት ያለው ተጋላጭነት ፤ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት በኢትዮጵያ ሠፋ ወይስ ጠበበ ?፤ ለተሻለ ሁኔታ ወደ አረብ ሃገር የሚሰደዱ የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ እንዲሁም በአዉሮጳ አባል ሃገራት ተቃዉሞ የታገደዉ ለዩክሬይን ይሰጣል የተባለዉ ብድር ፤የተሰኙ ዘገባዎችን ያስተነትናል።
የምሽቱ ስርጭታችን በዜና መጽሔት ጥንቅሩ --ከጦርነት ሥጋት ያልተላቀቀው ኢትዮጵያን፣ ሱዳንን እና ኤርትራን የሚያዋስነው አካባቢ --እየሰፋ የመጣው የምንዛሪ ቢሮዎች እና የባንኮች ልዩነት -- እናት ፓርቲ "ለኢትዮጵያ" ወደተባለው የፓርቲዎች ቅንጅት መመለሱ ተገለጠ -- የተማሪዎች ምገባ በአማራ ክልል-- እንዲሁም --ነዳጅን ከመደበኛ ዋጋ የመሸጥ ፈተና -- ፤የተሰኙ ዘገባዎችን በስፋት ያስተነትናል።
ዜና መጽሔት ፤ -የየካቲት 12 ሰማዕታት ፍትሕ እንዲያገኙ የሚጠይቀው ዓለም አቀፍ ዘመቻ -የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የምዕራብ ኦሮሚያ ጉብኝት -የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል አጀንዳዎችን አዲስ አበባ ላይ ለማሰባሰብ መወሰኑን ማስታወቁ -“የጦርነት ድባብ” እና የኦነግ ማሳሰቢያ- በአማራ ክልል ያለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት - ከሶማሊያ እና ሳውዲ አረቢያ ወታደራዊ ስምምነት ጀርባ ያለው ምንድን ነው በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ቀርበዋል።
በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። የቱርክዬ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት፤ በሕወኃትና በፊደራል መንግስት ዳግም ግጭት እንዳይቀሰቀስ የነዋሪዎች ሥጋት፤ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ወጪ የድሬደዋ የፍሳሽ ማስወገጃ እና ማጣርያ ፕሮጀክት፤ ደቡብ ወሎ ዞን ከ276 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት አልተመለሱም፤ እንዲሁም ቱሪዝም እያበበ ነው የተባለለት አዲሱ የጎርጎሳውያን ዓመትና የኢትዮጵያ ድርሻ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። ሳምንታዊዎቹ ከኤኮኖሚው ዓለም እንዲሁም ሣይንስና ቴክኖሎጂም ተዘጋጅተዋል ።
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣ ወታደራዊ ንቅናቄ በሰሜን ኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአቪሽን ፀጥታ ላይ ያደረገዉን ዉይይት። የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 6 ወራት ከ41 ኩንታል በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱን አስታዉቋል።አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ 15 ሰዎች መገደላቸዉ ተዘግቧል።የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) በክክሉ ፀጥታና የኑሮ ዉድነት ላይ ያደረገዉ ዉይይት ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ። ዜና መፅሔቱ ደቡብ ወሎ ዞን 276 ሺሕ ተማሪዎች ትምሕርት ማቋረጣቸዉን ይቃኛል። ሳምንታዊ ጤናና አካባቢ ምዕራብ ሸዋ ዉስጥ ምንነቱ በዉል ያልታወቀ አዉሬ ያደረሰዉን ጥቃት ይዳስሳል።
-ባለ ጉዳይ የበዛበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና፤ --በአፍሪቃ በቀጠሉ የፀጥታ ችግሮችና በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎች በማሳለፍ የተጠናቀቀዉ 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ፤ --የምርጫ ዝግጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል --በደቡብ ኢትዮጵየ ክልል በየዞኖቹ የተዘረጉ ህገ ወጥ ኬላዎች እና ተግዳሮቶቻቸዉ
በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎች በትንታኔ ይቀርባሉ ። ለጸጥታ ቅድሚያ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ፤ ሕዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ ለአፍሪቃ ህብረት የላከው ደብዳቤ እና አንድምታው ፤ በደብረታቦር ከተማ የተከሰተው የጸጥታ አለመረጋጋት እና የነዋሪው አስተያየት ፤ የኢትዮጵያውያን ሕብረትና የሽግግር ቅድመ ሁኔታ ላይ የተደረገ ምክክር እና አንድምታው፤ የአውሮጳ መሪዎች ከኤኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ የያዙት መንገድ የተመለከቱ ዘገባዎች ይደመጣሉ ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዙ 19 ማሻሻያዎች አድርጓል። የሳዑዲ ማረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የኢትዮፕያ ጉብኝት እና አንድምታው ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ተፈናቅለው ለሁለት ዓመታት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ተጠልለው ከቆዩ ተፈናቃዮች መካከል ከ1,200 በላይ የሚሆኑት ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ገልጸዋል።
የዕለቱ መጽሔታችን ሶስት ርዕሰ ጉዳዮችን በቅደም ተከተል ያስደምጣል። የሱዳን የርስ በርስ ግጭት፤ አፍጦ የመጣው ጣልቃ ገብነት እና ጂኦፖለቲካው፤ ቆቦ ዙሪያ የሰፈሩ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ ሳያገኙ ሁለት ሳምንት እንዳለፋቸው መናገራቸው፤ የአብን የፖርላማ ተመራጮች ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ የወሰዱት አቋም በሚሉ ርዕሶች የተሰናዱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ክስ ዛሬ ሰኞ “ሐሰት” በማለት አጣጥሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ የድንበር አካባቢ ከዚህ ቀደም ከተቆጣጠሩት “የበለጠ ዘልቀው” እንደገቡ ገልጸው ነበር። በጉዳዩ ላይ የተንታኞች እና የፓለቲከኞች አስተያየቶች የተካተቱባቸው ዘገባዎች ለዛሬ ተዘጋጅተዋል። የአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 625,000 የሥራ ዕድሎች በክልሉ እንደተፈጠሩ አስታውቋል። ይህን የተመለከተው ዘገባ በዜና መጽሔት ከሚቀርቡት መካከል ነው።
loading
Comments