Discoverየዓለም ዜና
የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Author: DW

Subscribed: 7Played: 362
Share

Description

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
856 Episodes
Reverse
የሶማሊያ ፌድራል መንግሥት እና የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ከማባባስ እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ አሳሰቡ። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን የሚያካሒዱት ውጊያ የሚቆምበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የቀጠናው ቁልፍ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በፓኪስታን ተሰበሰቡ። ጦርነቱ ዓለም አቀፍ ሕግ እንደሚጥስ ቡንደስታግ ተብሎ የሚጠራው የጀርመን ምክር ቤት የምርምር አገልግሎት ይፋ ያደረገው ሪፖርት አሳየ። በአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና ፖሊሲዎቻቸውን ለመቃወም በተለያዩ ከተሞች በተካሔዱ ሰልፎች ቢያንስ 8 ሚሊዮን ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሎ እንደሚገመት አዘጋጆቹ አስታወቁ።
• የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ያስከተለው ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለከፋ እንግልት እያጋለጠ ነው ተባለ። • በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በተጠረጠሩ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት ባለቤቶች ላይ ክስ ተመሰረተ። • በኢራን የሚደገፉ የየመኑ ሁቲ አማፂያን በእስራኤል ላይ የሚሳይል ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቁ። • በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተዘገበ። • በሜድትራንያን ባህር ላይ በአነስተኛ የፕላስቲክ ጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 22ቱ በግሪክ የባሕር ጠረፍ መሞታቸው ተሰማ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል "አስቻይ ኹኔታ እስኪፈጠር" የክልሉን አጀንዳ የማሰባሰብ እና የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታን በአዲስ አበባ ለማካሄድ መገደዱን አስታወq።። ኮሚሽኑ እንዳለው ምክክሩ ከመጋቢት 23 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ለአፍሪቃ ሀገራት የተላኩ የኮሌራ መከላከያ መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች በኢራን ጦርነት ምክንያት ወደሚፈለጉበት ሀገራት መድረስ አለመቻላቸው ተዘገበ። መድኃኒቶቹ ች ዱባይ በሚገኝ መጋዘን ተከማችተው እንደሚገኙተገልጿል ። ዛሬ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ለማለፍ የሞከሩ ሁለት እቃ ጫኝ የቻይና መርከቦች በሰርጡ ሳያልፉ ተመልሰዋል።
በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ አንድ የስደተኞች ጀልባ በመስጠሙ 9 ሲሞቱ 45ቱ እስከአሁን ደብዛቸውን ማግኘት እንዳልተቻል ፤ የኢራን እስላማዊ ዘብ የባሕር ሃይል አዛዥ በእስራኤል መገደላቸውን ተሰማ። የየመን ሁቲ አማጽያን ከኢራን ጎን እንደሚቆሙና አስፈላጊ ከሆነም በቀይባሕር ባብ አልመንደብ የሚተላለፉ መርከቦችን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አስታወቁ። ሩስያ በደቡባዊ የኦዴሳ ግዛት በምትገኘው አንዲት የወደብ ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት በመፈጸም በሐይል መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አደረሰች ተባለ።
አ.አ፥ ከምርጭ ራሳችንን እስከማግለል ርምጃ ልንወስድ እንችላለን" - የ4 ፓርቲዎች ቅንጅት፤ ካርቱም፥ የሱዳን ድንበር ከተማ ኩርሙክ አስተዳዳሪ ከተማዪቱ በፈጥኖ ደራሽ ለመያዟ ኢትዮጵያ እጇ አለበት አሉ፤ አ.አ፥ 922 ባሕር ስደተኞች በበቀይ ባሕር ያለቁበት 2025 ዓመት ከምንጊዜውም በላይ ገዳዩ ተባለ፤ ራባት፥ ሞሮኮ የአይ ኤስ አሸባሪዎች የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከስፑን ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለጠች፤ ቴሕራን፥ ኢራን «ዩናይትድ ስቴትስ የምትደራደረው ከገዛ ራሷ ጋር ነው» አለች፤ ትሪፖሊ፥ የሊቢያ የባሕር በር ጠባቂዎች ጠባቂዎች ጉዳት የደረሰባት የሩስያ ነዳጅ ጫኝ መርከብን አሸሹ
የትግራይ ቴሌቪዥን የዜና ክፍል ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ዮሐንስ ብርሃነ ኢ- ሕገመንግሥታዊ "አፈና እና እሥር" እንደተፈፀመበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ገለፀ። በለፉት 3 ወራት ግድም በሱዳን በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ከ500 በላይ ሱዳናውያን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥ ካልከፈተች በሃይል መሰረተ ልማቶቿ ብርቱ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ የሰጡትን የ2 ቀናት ቀነ ገደብ ወደ 5 ቀናት መራዘሙን ከገለጹ በሰአታት ጊዜ ውስጥ በኢራን ሁለት የሃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተሰማ።
• በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬኒያ ሲሻገሩ ደረስኩባቸው ያላቸውን 48 ኤርትራዊያንን በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ አስታወቀ ፡፡ • የናይጄሪያው ግዙፉ የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ነዳጅ መላክ መጀመሩን አስታወቀ። • ማሊ በነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎቿ ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማስቆም በደረሰችው ስምምነት በርካታ ጂሃዲስቶችን ከእስር ለቀቀች። • የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወሳኙን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ለአለም አቀፍ የንግድ መርከቦች እንድትከፍት ያስቀመጡትን የጊዜ ገደብ ለአምስት ቀናት ማራዘማቸውን አስታወቁ።
• በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ 13 ሕፃናትን ጨምሮ በትንሹ 64 ሰዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። • ኢራን በእስራኤል የበረሃ ከተሞች ላይ በፈጸመችው የሚሳኤል ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች ቆሰሉ ። • በቃጣር በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን የቃጣር እና የቱርክ ባለስልጣናት አስታወቁ። • ቱርክ፣ እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ሰላማዊ ዕልባት እንዲያገኝ ጥረት እያደረገች መሆኑ ተሰማ።
ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እና የኬንያ መዲና ናይሮቢን ጨምሮ በአስራ ሁለት ከተሞች የአደጋ እና ሰብአዊ ድጋፍ ምላሽ ቀጠናዊ ማዕከላት ልታቋቁም ነው። ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል በኢራን ኢስፋሃን ግዛት የሚገኘው የናታንዝ የኒኩሊየር ማብለያ ጣቢያ ላይ በድጋሚ ጥቃት መፈጸማቸውን የኢራን መገናኛ ብዙሃን አስታወቁ። እስራኤል በሶሪያ ጦር ካምፕ የፈጸመችው ጥቃት ሳውዲ አረቢያ «ወረራ» ስትል አወገዘችው።
1447 ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፊጥር በዓል ዛሬ አዲስ አበን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ በእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሯል። የእስራኤል ጦር ዛሬ ጠዋት በቴህራን ባካሄደው ድብደባ የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ ቃል አቀባይ መግደሉን አስታወቀ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ታላቋ ብሪታንያን አስጠነቀቁ። የፈረንሳይ የባሕር ሐይል አባላት የሩስያ ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን የሐገሪቱ ፕረዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤክስ ገጻቸው ገልጸዋል።
አአ፥በሰው ሠራሽ አስተውሎት ወይም 'AI' የተሠሩ ምስሎች ሚና በኢትዮ ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት፤ አ.አ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ወቅታዊው የነዳጅ እትረት ማጓጓዣ ስርዓቱ ላይ ተግዳሮት ፈጥሯል፤ ንጃሜና፥ ከሱዳን የተሰነዘረ የሰው አልባ ጥቃት ጎረቤት ቻድ ውስጥ 17 ሰው ገደለ፤ ላሙ፥ በኢራን ጦርነት የተነሳ በሺህዎች የሚቆጠሩ ፖርሼ ተሽከርካሪዎች ኬኒያ ተራገፉ፤ ብራስልስ፥ በአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ላይ የተገኙት የተመድ ዋና ጸሐፊ የኢራን ጦርነት እንዲያበቃ ጥሪ አስተላለፉ፤ ቴሕራን፥ ኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ ላይ መርከቦችን ለማስከፈል እያጤንኩ ነው አለች
የመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስ እንዲለቀቁ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ ዛሬ ውድቅ አደረገው። የተከ የእስራኤል ጦር ኃይል የኢራንን የስለላ ጉዳይ ሚንስትር ኢስማኢል ኻቲብን መግደሉን አስታወቀ። ኢራን ግድያዉን አላረጋገጠችም። የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና እሥራኤል በኢራን ላይ ስለከፈቱት ጦርነት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጀርመን አማክራ ቢሆን ኖሮ፣ እርምጃው እንዳይወሰድ እንመክራቸው ነበር ሲሉ አስታወቁ። ሜርስ እንዳሉት ዋሽንግተን ስለጦርነቱ ጀርመንን አላማከረችም።
• የደቡብ ሱዳን ጦር እና በአማጽያን መካከል የተቀሰቀሰውን አዲስ ግጭት ሽሽት ከ100 ሺ በላይ የአኮቦ ከተማ ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አስታወቀ። • የሶማሊያዋ የጁባላንድ ግዛት አስተዳደር ከሞቃዲሾው ፌዴራላዊ መንግስት ጋር ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት እና ትብብር ማቋረጡን አስታወቀ። • በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ በደረሰ ተከታታይ የአጥፍቶ መጥፋት የቦምብ ጥቃት በትንሹ 23 ሰዎች ተገደሉ። • እስራኤል ከፍተኛውን የኢራን የደህንነት ባለስልጣን አሊ ላሪጃኒን መግደሏን አስታወቀች።
በኢትዮጵያ “ነዳጅን በቁጠባ እና ለመሰረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም” እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀዘናቸውን ለኢትዮጵያ ገለፁ። ኬንያ ፤ ሩሲያ የኬንያ ዜጎችን ለውትድርና መመልመሏን ለማቆም ተስማማች። ኢራን በኳታር እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ ጥቃት ሰነዘረች። ትራምፕ „የኔቶ አባል ሀገራት አሜሪካን ካላገዙ የኔቶ የወደፊት እጣ ፈንታ ጥሩ አይሆንም” አሉ።
የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ ላይ ያደረገውን ጭማሪ ተከትሎ በአዲስ አበባ የሕዝብ መጓጓዣ ከ5 እስከ 20 ብር የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ። የሩሲያ ጦር በዩክሬን በመካሔድ ላይ ለሚገኘው ጦርነት ኬንያውያንን በግዳጅ ከመመልመል እንዲታቀብ ግፊት ለማድረግ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ወደ ሞስኮ አቀኑ። በኮንጎ ሪፐብሊክ ዜጎች ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን የገጠሙትን ጦርነት የቀሰቀሱ መሪዎች ውጊያውን እንዲያስቆሙ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ሊዎ 14ኛ ጥሪ አቀረቡ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በባርሴሎና እና በሴዑል የተካሔዱ የማራቶን የሩጫ ውድድሮችን አሸነፉ።
በታንዛኒያ ኃይቅ ላይ ጀልባቸው ተገልብጦ ሰባት የጤና ባለሙያዎች ህይወት አለፈ።የዩጋንዳ ተቃዋሚ መሪ ቦቢ ዋይን ከሀገር መውጣታቸውን አስታወቁ።አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በእስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ እየነፈሰ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ኻመኔይና ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለመያዝ 10 ሚሊዮን ወሮታ እከፍላለሁ አለች። በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳት ደረሰበት።ሰሜን ኮሪያ አስር የሚጠጉ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች
ጋሞ፥ በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ለ3 ቀናት የሚቆይ ክልላዊ የሐዘን ቀን ታወጀ፤ አስመራ፥ ኤርትራ ውስጥ ያለ ክስ ለ15 ዓመታት የታሰረ ካርቱኒስት መፈታቱ ተገለጠ ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በጊዜያዊነት የሩስያ ድፍድፍ ነዳጅ እገዳን አነሳች፤ ኪዬቭ፥ የሩስያ ነዳጅ እገዳ በከፊል መነሳት ተቃውሞና ድጋፍ፤ ካቡል፥ ፓኪስታን የአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና የድንበር ከተሞችን በቦንብ ደበደበች፤ ዋሽንግተን፥ የታይዋን ምክር ቤት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነትን አጸደቀ፤
ዐርእስተ ዜና አሜሪካን የጠረዘቻቸው 4 ተጨማሪ ሰዎች ኤስዋቲኒ ተቀበለች ተጠራዦች ሁለቱ ከሶማሊያ አንድ ከታንዛኒያ ሌላ አንድ ደግሞ ከሱዳን መሆናቸው ተገልጿል። አዲሱ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻማኒ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጡት መግለጫ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መዘጋት እንደ ማነቃቂያ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ተናገሩ፤ ኢራን ጎረቤቶቿን የባህረ ሰላጤው አገራትን ማጥቃቷን እንደምትቀጥልም አስታወቁ ቱርክና ጀርመን የኢራን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ተስማሙ። ጀርመን አውሮጳውያንና የባህረ ሰላጤው አገራት የኢራንን ጦርነት ለማስቆም በጋራ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ ጥሪ አቀረበች።
-ደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ ዞን ዉስጥ በደረሰ የመሬት መደርመስና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 64 ሰዎች ሞቱ።ሌሎች በርካታ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።---ሱዳን ዉስጥ ለቀስተኞችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አነስተኛ የጭነት መኪና (ፒክ አፕ) በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) ተመትታ 40 ሰዎች ተገደሉ።በሌላ የሰ,ዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃት 17 ሰዎች ተገድለዋል።አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎች ናቸዉ።---እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራን አፀፋ የዓለምን ምጣኔ ሐብት እያዉገረገረዉ ነዉ።ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ መንግስታትና የኃይማኖት መሪዎች የሚያደርጉት ጥሪና ፀሎት እንደቀጠለ ነዉ።ጦርነቱም አላባራም።
loading
Comments