Discoverማሕደረ ዜና
ማሕደረ ዜና
Claim Ownership

ማሕደረ ዜና

Author: DW

Subscribed: 3Played: 62
Share

Description

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ
153 Episodes
Reverse
የኢራን ትምሕርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመድሐኒት ፋብሪካዎች፣ ድልድዮች፣ ዩኒቨርስቲዎች ሳይቀሩ ወድመዋል።የእስራኤልና የመካከለኛዉ ምሥራቅ የአረብ ሐገራት በርካታ የኃይልና የሰላማዊ ተቋማት ተመትተዋል።ከሁሉም በላይ ምትክ የሌለዉ ከአራት ሺሕ በላይ ህይወት ጠፍቷል።በአንዳዶች ግምት በትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አንድም ጠፍቷል ሁለትም ከስሯል።ትራምፕም ግን ነገ ማክሰኞ የኢራን የመሰረተ ልማት ተቋማት የሚፈራርሱበት ቀን እንደሆነ አዉጀዋል።ባለፈዉ ሳምንት ለኢራኖች የሚገባዉ «የድጋይ ዘመን ነዉ» ያሉት ትራምፕ ትናንት ኢራኖችን «እብድ፣ ዲቃሎች» በማለትም ባደባባይ ተሳድበዋል።ያበደዉ ማን ይሆን?
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሣምንት አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት መቼ እንደሚቆም ሲጠየቁ “እስከ አጥንቴ ዘልቆ ሲሰማኝ” የሚል መልስ ሰጥተዋል። መልሳቸው የጦርነቱን መቋጫ ለሚናፍቁ ማስተማመኛ የሚሰጥ አይደለም። ተንታኞች 24ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ጦርነት የሚቆምበት ጊዜ እና ሁኔታ እጅግ ውስብስብ እንደሆነ ሥጋት አላቸው።
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግሥት ኃይለማርያም የናደዉ ዕዝ በ1987 (እጎአ መሆኑን አይዘንጉ) ግድም አፍአበት ላይ የገጠመዉን ሽንፈት ጠላት «አካቢዉን ከበቦ ሲያበቃ የዕዙን ጭንቅላት በጠበጠዉ» ዓይነት ብለዉ ባጭሩ ገልፀዉት ነበር።የእስራኤልና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የካቲት 28 ጧት የኢራንን የፖለቲካ፣ የጦርና የስለላ እናትን ቆርጦ ቢጥልም ፋርሶች እንደታሰበዉ «ያልተበጠበጡበት» ሁለተኛዉ ምክንያት የጠላታቸዉን የዉጊያ ሥልት ብዙ አጥንተዉ በቅርብ አመታት ኢራቅ፣ አፍቃኒስታንና ሊቢያ ላይ ከሆነዉ ተምረዉ የነኬይን ዘመናይ ሥልት በነ አፄ ምኒልክ ጥንታዊ ሥልት ለመመከት በመዘጋጀታቸዉ ነዉ።
እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን መደብደብ የጀመሩት ቴሕራን ላይ የኢራን መሪዎችን፣ ሚናብ ዉስጥ ሕፃናት ሴት ተማሪዎችን በመግደል ነዉ።መሪዎቹን ከነሚስት ልጆቻቸዉ መግደል ለቴል አቪቭ ዋሽግተን መሪዎች ራሳቸዉ ደጋግመዉ እንዳሉት ጀግንነት ነዉ።የሚናብ-ኢራን ሴት ተማሪ-አስተማሪዎችን መግደል ግን ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የቴሕራኖች ሥራ እንጂ በዓለም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጦራቸዉ ስሕተት ዓይደለም።
ሳዳም ሁሴይ፣ ኦስማ ቢን ላደን፣ ሙዓመር ቃዛፊ፣ ዑስማኢል ሐንያሕ፣ ሐሰን ነስረላሕ ሌሎችም ሲገደሉ ዓለም ከአምባገነኖች፣ከጨቋኞች እና ካሸባሪዎች መላቀቋን የቴል አቪቭ-ዋሽግተን-ለንደን-ብራስልስ መሪዎች ለዓለም አዉጀዉ ነበር።ዓለም ግን ዘንድሮም ሰላም አታዉቅም።አምና ጥር ለሁለተኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስን የፕሬዝደትነት ሥልጣን የያዙት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ፕሬዝደንት መሆናቸዉን ሲደሰኩሩ የልዕለ ኃያሊቱ ሐገር መሪዎች የጦርነትን አትራፊነት ብቻ ሳይሆን አስከፊነትቱን የተረዱ መስለዉ ነበር
ዩክሬንን የሚደግፉት የምዕራባዉያን መንግሥታትና ተቋማት እንደሚሉት የሩሲያ ዕቅድ ኪቪን ባጭር ጊዜ ምናልባትም በሶስት ቀናት ዉስጥ ተቆጣጥሮ ዜለንስኪና ተባባሪዎቻቸዉን አንቆ ወደ ሞስኮ ለመዉሰድ ነበር።ፑቲን ግን ዘመቻዉ ልዩ፣ ዩክሬንን በኃይል የመግዛት ዕቅድም እንደሌላቸዉ አስታዉቀዉ ነበር።የጦርነቱ ዕቅድ ምዕራባዉያኑ እንደገመቱትም ሆነ ፑቲን እንዳሉት እስካሁን አሸናፊና ተሸናፊ አልተለየም።
የጀርመኑ መራሔ መንግሥት የአሜሪካ ወዳጆቻችን በቀጥታ እንዲረዱት በማለት ለጉባኤተኞች በእንግሊዘኛ ጭምር ያደረጉት ንግግር አዉሮጶች በትራምፕ አስዳደር እርምጃና መርሕ ከመስጋት አልፈዉ መናደድ፣ መቆጣታቸዉን የሚያስረዳ ነዉ።የፈረንሳይና የሌሎች የአዉሮጳ መንግሥታት መሪዎችና ተወካዮችም የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደርን በተደጋጋሚ ተችተዋል።አዉሮጳ የራስዋን የመከላከያ ኃይል ማጠናከር እንደሚገባት አሳስበዋልም።
ሮሞች፣ቱርኮች፣ፖርቱጋሎች፣ አረቦች፣ አዉሮጶች፣ሐበሾች፣ ግብፆች፣ ሶቭየት ሕብረቶች፣ ኩባዎች፣ አሜሪካኖች በየዘመናቸዉ ዘምተዉ ገድለዉ ሞተዉበታል።የዚያን ምድር ሕዝብ ደም አፋሰዉበታል።በቅርቡ ደግሞ የመካከለኛዉ ምሥራቅና የእስያ ኃያል ቱጃር መንግሥታት እየተራኮቱበት ነዉ።የአፍሪቃ ቀንድ።የጎቲንገን ዩኒቨርስቲ ባልደረባ ዶክተር ማርኩስ ፊርግል ሆነ እንደሚሉት የአፍሪቃ ቀንድ የአዲስ ቅርምትና ማዕከል ሆኗል።
ባለፉት ጥቂት አመታት የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች በወሰዱት እርምጃ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከልነቱ የተሽመደመደዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዲፕሎማቶችም የዋሽግተንና የቴሕራን መሪዎች ጦርነት ከመግጠም እንዲታቀቡ አደራ ብለዋል።በለንደን ስኩል ኦፍ ኤኮኖሚክስ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ፋዉዝ ጀርጀስ እንደሚሉት የዲፖሎማሲ ጥረት እየከሰመ፣ የጦርነቱ አይቀሬነት እየደመቀ ነዉ።
የምዕራብ አዉሮጳ መንግሥታት የእስራኤን አለመቃወማቸዉን ሲያስታዉቁ፣ ትራምፕ እስራኤልን ደግፈዉ ኢራንን ደበደቡ።ኢራንን የኑክሌር ተቋማት ሙሉ በሙሉ አወደምን አሉም።12 ቀናት ያስቆጠረዉ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት በተለይ ኢራንና እስራኤል ዉስጥ የሰዉ ሕይወት ከማጥፋቱ በተጨማሪ ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ኪሳራ አስከትሏል።ዩናይትድ ስቴትስም ለ18 ሰዓታት ድብደባ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር አዉጥታለች።የ12ቀናቱ ድብደባማ ሆነ ትራምፕ ያወ,ጁት ድል የእስራኤል፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን መሪዎች ለተጨማሪ ጦርነት ከመዛዛት፣ በጦር ኃይል ከመፋጠጥ አለማዳኑ እንጂ እንቆቅልሹ።ፍጥጫዉ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።
በማግሥቱ ቅዳሜ የሞቃዲሾ መንግሥትን የሚደግፉ ወይም የእስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን እርምጃ ከሚቃወሙት መካከል የቱርክ፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የሱዳንና የጅቡቲ አምባሳደሮችና ፖለቲከኞች ላስ አኖድ ገቡ።የዲፕሎማቶቹና የፖለቲከኞቹ ጉብኝት አዲስ በተመረጡት የሰሜን ምሥራቅ ግዛት ፕሬዝደንት አብዲቃድር አሕመድ አዊ-ዓሊ (ፊርዲሕዬ) በዓለ-ሲመት ላይ ለመገኘት እንደሆነ ተነግሯል።ትክክለኛ መልዕክቱ ግን እስራኤል ከድፍን ዓለም ተሽቀዳድማ፣ የዓለም ሕግን ጥሳ፣ የሶማሊያን ሉዓላዊነት አፍርሳ፣ ለሶማሊላንድ ዕዉቅና መስጠቷን ከቃላት በላይ በድርጊት ለመቃወም ነዉ
ኢራን ዳግም በተጣለባት ማዕቀብ መገበያያ ገንዘቧ ሲላሽቅ በተፈጠረ ኢኮኖሚያዊ ጫና የተቀሰቀሰ ተቃውሞ ሦስተኛ ሣምንቱን አስቆጥሯል። እስካሁን ከ530 በላይ ተዋሚዎች እና የጸጥታ አስከባሪዎች መገደላቸውን አክቲቪስቶች ገልጸዋል። ኢራን ለተቃውሞዎች እንግዳ ባትሆንም ጂዖ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል መሪዎች የሰጧቸው አስተያየቶች የአሁኑን አሳሳቢ አድርገውታል።
የቡድን 20 ጉባኤ ሲጠናቀቅ በሱዳን፣ ኮንጎ፣ በእስራኤል በጉልበት በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶችና በዩክሬን “ፍትኃዊ፣ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ሰላም” እንዲወርድ እንደሚሠሩ መሪዎቹ ቃል ገብተዋል። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደው ጉባኤ የደቡብ አፍሪካ እና የአሜሪካ ውዝግብ ተጭኖታል። ጉባኤው ሲጠናቀቅ አሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝደንትነቱን አልተረከበችም።
አንዳዶቹ ፎቶ ግራፎች ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዉስጥ የተነሱ መሆናቸዉ ቢረጋገጥም የነጮችን የበላይነት ለማስከበር ቆርጠዉ የተነሱት ዶናልድ ትራምፕ ግን ነጭ ደቡብ አፍሪቃዉያን ወደ አሜሪካ እንዲሰደዱ ፈቀደዋል።አሜሪካ ጥግ የምትገኘዉን የጃማይካ ስደተኛን ሳይቀር ከአሜሪካ ወደ አፍሪቃ ያስግዛሉ።መሰደድ የማይፈልጉትን የደቡብ አፍሪቃ ነጭ ዜጎችን ወደ አሜሪካ ይጋብዛሉ።ከአፍሪቃ ጋር የንግድ ግንኙነትን ማጠናቀር እሻለሁ ይላሉ፤ ደቡብ አፍሪቃን በዘረኝነት ያወግዛሉ።
loading
Comments 
loading