DiscoverDW | Amharic - News
DW | Amharic - News
Claim Ownership

DW | Amharic - News

Author:

Subscribed: 53Played: 3,507
Share

Description

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
2531 Episodes
Reverse
የራስ ምታት ህመም ለብዙዎች እንግዳ ካልሆኑ ህመሞች አንዱ ነው። ግን የራስ ምታት ህመም ምንድነው? እራሱን የቻለ ህመም ወይንስ የሌላ በሽታ ምልክት?
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሴት የበላይ ኃላፊ ተሾመለት። ተቋሙን ለአንድ ዓመት ገደማ የመሩት ዶክተር ሳምሶን መኮንን በፈቃዳቸው ሥልጣን መልቀቃቸው ተነግሯል።
«በግብርና ምርት ውጤቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ቢስተዋልም እንደዘይት የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶች ዋጋ ግን አይቀመስም»“ ይላሉ የሀዋሳ ከተማ የበዓል ሸማቾች።
ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ነው። በዋዜማው በአዲስ አበባ ከተማም ይሁን በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ከፍተኛ የበዓል ግብይት ይከናወናል።
በላሊበላ ከተማ በገና በዓል ዋዜማ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁስ የእርድ እንስሳቶች በጎብኝዎች እየተሸመቱ ነው። በተለያም ባህላዊ ቁሳቁስ ከፍተኛ ሽያጭ አለው። የገናን በዓል ለማክበር የመጡ እንግዶችም በአካባቢዉ ማኅበረሰብ መስተንግዶ እየተደረገላቸው ነው።
ቬንዙዌላዉያን ባለፈው ቅዳሜ ጠዋት ከእንቅልፋቸው እንደነቁ ፕሬዚዳንታቸው በአሜሪካ ወታደሮች ታግተው መወሰዳቸውን ሲሰሙ ምን ተሰምቷቸው ይኾን? ይህ ቬንዙዌላዉያንን ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ዓለም ዓይን እና ጆሮን ለማመን የሚቸግር ዱብ ዕዳ ነው የሆነው። ቬንዙዌላን የምታክል ሀገርስ እንደምን መሪዋ እንደ አንድ ተራ ነገር ተንጠልጥሎ ሊወሰድባት ቻለ?
በመላው ዓለም በተልየም በአፍሪካውያን ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና በሞሮኮ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የስፖርቱን አፍቃሪ ቀልብ እንደገዛ ነው። የምድብ ማጣሪያ ውድድሩ ተጠናቆ እየተካሄደ ባለው የጥሎ ማለፍ ወድድር ዛሪ ሰኞ እና ነገ ማክሰኞ በሚካሄዱ አራት ጨዋታዎች ለዋንጫው ግብግብ የሚገጥሙት ቡድኖች የሚለዩበት ይሆናል።
ከሦስት ዐሥርተ ዓመታት በላይ የዘለቀው ጥበቃ አሁን ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስፋ የፈነጠቀላት መስሏል። እስራኤል ለሶማሌ ላንድ የሉአላዊ ሀገርነት እውቅና ስትሰጥ የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገር ሆናለች።
ከ5ሺህ በላይ ይሆናሉ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ድንገት ወደሀገራቸው እንዲሚመለሱ ተነግሯቸዋል። ኢትዮጵያውንንም ተጠቃሚ ያደርግ የነበረው ቋሚ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሚያስገኘው የDV መርሃ-ግብር መቋረጡ ተነግሯል። እነዚህ ስደተኞችን የሚያዋክቡ አሰራሮች ወደ አውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራትና ብሪታንያም ጭምር የመዛመታቸው አዝማሚያ ያሰጋል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት የዓለም የፕረስ ነጻነትን ቀን የማስተናገድ እጋጣሚ ሰምሮላት በነበረው ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀን የነጻነት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱ መነገር ከጀመረ ውሎ አደረ።
«ቂም ይዘን እዚህ አንመጣም፡፡ በጸጥታ እና በተለያዩ ጉድለቶቻቸው በዚህ የአንድነታችን በዓል ላይ ለመምጣት አስበው መምጣት ያልቻሉትን በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ሁሉ ሞልቶ እንዲመጡ ፈጣሪ ይርዳቸው ነው የምለው»
የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ሰው እንደ አቅሙ ተደስቶ ለማለፍ ጥረት የሚያደርግበት፣ ላለፈው ዘመን ለአምላኩ ምስጋና ለመጪው አዲስ ዘመን ደግሞ ለሰዎች ሁሉ ደግ እና በጎ ሕይወት እንዲገጥም መልካም ምኞት የሚቀርብበትም ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን እንደ አቅም ሥጋ እና የፍስግ ምግቦች ተነጥለው የሚቀሩ አይደሉም።
2017 ዓ.ም "ግጭቶቻችንን በውይይት እና በድርድር ፈትተን፤ የዘመናት ስብራቶቻችንን በምክክርና በሽግግር ፍትሕ ጠግነን፤ በብዙ ነገሮች ራሳችንን ችለን" የምንለወጠበት እንዲሆን ምኞቴ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ። የሃይማኖት መሪዎችም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የሰላም እና የአንድነት ጥሪ አቅርበዋል።
ባንኮች ሐዋላ ለሚላክላቸው ደንበኞች እስከ 17 በመቶ የሚደርስ የአዲስ ዓመት ስጦታ ቃል ገብተዋል። የአንዳንዶቹ ባንኮች ስጦታ ከመደበኛው የዶላር ምንዛሪ ሲደመር በተለምዶ ጥቁር ከሚባለው የጎንዮሽ ገበያ የሚያቀራርባቸው ነው። የኢትዮጵያ 31 ባንኮች ሐዋላ ለሚልኩ የ100 ቢሊዮን ብድር ማዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ይፋ አድርገዋል
አሮጌ አመት ተሸኝቶ አዲስ ዓመት ሲተካ አዳዲስ ዕቅዶችን መንደፍ የተለመደ ነገር ነው።ለመሆኑ ሰዎች አዲስ ዓመትን እንደ አዲስ ጅምር የሚቆጥሩት ለምንድን ነው? በአዲስ ዓመትስ ለምን አዲስ ዕቅድ ያወጣሉ? ስለ አዲስ አመት ዕቅድስ ሳይንስ ምን ይላል?
ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከጥቂት አገራት በስተቀር አብዛኛውን የዓለም ክፍል ተዘዋውረው በመጎብኘት ሀገራቸውን ያስተዋወቁ መሪ ናቸው።በዘመናቸው ካሳኳቸው የውጭ ሀገራት ግንኙነቶች ከጀርመን ጋር የመሰረቱት ጥብቅ ወዳጅነት አንዱ ነው።ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን እንደሚሉት ይህ ወዳጅነት የተመሰረተው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነበር።
የመገጣጠሚያ ላይ እብጠትና ብግነት ወይም ከባድ ህመም የሪህ ህመም እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። በእርግጥ ሪህ ህመም ምንድነው? መንስኤው ይታወቃል? ሪህ በሽታ በዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች እንዴት ይገለጻል?
ዓለም በሱዳን እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የሰው ልጅ ሰቆቃ፤ እልቂትና ስደት፤ ያገር ውድመትና ጥፋት ዐይኑን ገልጦ እንዲያይና እንዲታደግ አሁንም ጥሪ ቀርቦለታል።
በአማራ ክልል አዲሱን ዓመት ተመልክቶ ምርቶች ወደ ገበያው የደረሱ ቢሆንም በሁሉም በሚባል ደረጃ በምርቶች የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል ። የክልሉ መንግስት በበኩሉ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ዐሳውቋል ።
በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ ተጠርቷል የተባለው የመጓጓዣ እና ግብይት እንቅስቃሴ እቀባ በተጓዦች ላይ ስጋት ቢያጭርም እንቅስቃሴዎችን ግን ሙሉ ለሙሉ አለመግታቱን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለዶቼ ቬለ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ ።
loading
Comments