ፀሀይ. ፀሀይ አስፈሪውን ጨለማ ፈርታ ሳትወጣ አትቀርም ጨልማውን እየገፈፈች እየገፈፈች ስፍራውን ትሞላዋለች እንጂ ዛሬ ጨለማ ነው ብላ ጎጆዋ ውስጥ አትደበቅም ምድር እንኳን ጀርባዋን ብትሰጣት ፀሀይ በራሷ እና በሌሎች አለማት ፊት እየበራች ነው ፀሀይ የዝናብ ናዳ አያጨልማትም በኛ ሰማይ ሲዳምን ፀሀይ በራሷ አለም መውጣቷ አይቀርም ፀሀይ ምድርን ታበራታለች እንጂ ምድር እንዳዘዘቻት አትሆንም ለራሷ ደምቃ ውበቷንና ብርሃኗን ታንበሸብሸናለች እንጂ እርሷ አይበርዳትም ፀሀይ ሁልጊዜ ከደመናው በላይ ናት በተራሮች ከፍታ አትሰወርም ምድር ብትዳምን ፀሀይ ጨልማ ጠፍታ አይደለም የምድር ፊት በዳመና ተሸፍኖ እንጂ ፀሀይ ስትወጣ የፍጥረት ፊት ይደምቃል ውበት አብቦ ይፈካል በድፍረት ይወገዳል ሃዘን በደስታ ይተካል ፀሀይ ስትወጣ አይን ይከፈታል ተስፋ ይታደሳል::
October Month podcast is here as promised . I hope you enjoy it ladies.
Sparkle means bright light that shines for short time. In Amharic ብልጭታ. በፍጥነት በርቶ የሚጠፋ ደማቅ ብርሃን ነው:: ሰላም ለእናንተ ይሁን እህቶቼ እንዴት ናችሁ?ደስ እያለኝ ብልጭታ ፖድካስት እና መፅሄት ወይም Sparkle podcast and magazine ይዤልን ቀርቤያለሁ:: ባብዛኛው ሴት እህቶቼን እራሴንም ጨምሮ በማበርታት ላይ ያተኩራል:: በተለይ በትምህርት ሴት ልጅ እንድትጎብዝ መምከር እና ማበረታታት ደስታዬን ያበዛዋል:: እስቲ እንግዲህ በወር አንዴ ቡናችንን ወይም ሻያችንን ወይም ውሃችንን ይዘን ዘና እያልን ዝግጅታችንን አብረን እንቋደስ:: ወርሃዊ መጽሄታችን እነሆ፡ https://www.flipsnack.com/5CAFBAFF8D6/
Sparkle means bright light that shines for short time. In Amharic ብልጭታ. በፍጥነት በርቶ የሚጠፋ ደማቅ ብርሃን ነው:: ሰላም ለእናንተ ይሁን እህቶቼ እንዴት ናችሁ?ደስ እያለኝ ብልጭታ መፅሄት ወይም Sparkle magazine ይዤልን ቀርቤያለሁ:: ባብዛኛው ሴት እህቶቼን እራሴንም ጨምሮ በማበርታት ላይ ያተኩራል:: በተለይ በትምህርት ሴት ልጅ እንድትጎብዝ መምከር እና ማበረታታት ደስታዬን ያበዛዋል:: እስቲ እንግዲህ በወር አንዴ ቡናችንን ወይም ሻያችንን ወይም ውሃችንን ይዘን ዘና እያልን ዝግጅታችንን አብረን እንቋደስ::
ቀና ስትል ወደ መስቀሉ ታየዋለህ ያንተን ዋጋ የተከፈለልህን በሙሉ ህይወትህ ውድ መሆንዋን የታመመላት መኖሩን የፈወሳት በቁስሉ
በጨዋታ ከተሞላ ከመልካም የቤተሰብ ግዜ ባለፈ: ከዜና ማድመጥ ባለፈ: ከመጨነቅ ባለፈ: ከማረፍ ባለፈ: ከቤት መቆየት ባለፈ: ደግሞ ወለል ብሎ ወደ ተከፈተው ሰማይ: ወደ እግዚአብሄር ማደርያ ወደማይዘጋጋው በር እንግባ:: መፍትሄ ያለው በዚህኛው በር ነው:: በሰማዩ በር::
Beyond the quality time we spend with our family, beyond listening to news, beyond panicking, beyond taking good rest, beyond staying home safe, let’s enter to heaven that is open wide. Let’s get in to the Almighty’s place where it’s always open. The solution is in this door. The door of heaven.
እግዚአብሄርን እንታመን:: ምርምሩም ይቀጥል:: ሳይንሱም ይበርታ:: እግዚአብሄርን ግን ሁልጊዜ እናስቀድም::
It’s time to surrender! To the Almighty. Come to God through Jesus! He is merciful.
Faith መ. ኢያሱ 1:5-9 በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። 6 ለአባቶቻቸው፡— እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወርሳለህና ጽና፥ አይዞህ። 7 ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። 8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። 9 በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?
Hi , young moms and young ladies,we have poems songs, women’s place, kids time , family prayer and student girl empowerment session. I also share my books and women ahead of me that I am utilizing.