SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

" እንኳን ለደመራ እና መስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ። " - መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት

መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የደመራ እና የመስቀል በአል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ አንድምታ አስረድተዋል ።

09-26
13:30

"የኤሌክትሪክ መኪናዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት መሠረተ ልማትን ለመሥራት ያስገድዳል፤ ወደ ፈጠራ ይመራል። የኤሌክትሪክ ስኩተርና ብስክሌትም አሥፈላጊ ናቸው"ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ

ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ የኤሌክትሪክ መኪና፣ ስኩተርና ብስክሌት ለኢትዮጵያ ያለውን ጠቀሜታ ከጀርመንና ቻይና ተሞክሮ ጋር አያይዘው ያስረዳሉ።

09-26
23:17

"የኤሌክትሪክ መኪናዎች ለመንዳት ምቹና ለአካባቢያዊ አየር ብክለት ቅነሳ ጠቀሜታ ቢኖራቸውም፤ ጉዳትም አላቸው" ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ

ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ ከነዳጅና ናፍጣ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መኪና ሽግግርን ፋይዳዎች በንፅፅሮሽ አንስተው ያስረዳሉ።

09-26
12:14

ኢሬቻ መልካ በሜልበርን - አውስትራሊያ እሑድ ዕለት ሊከበር ነው

የኢሬቻ ክብረ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ኦቦ አብደታ ሆማ እና ኦቦ በንቲ ኦሊቃ፤ እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 በ Wilson Botanic Park Berwick ተከብሮ ስለሚውለው የኢሬቻ ክብረ በዓል ሥነ ሥርዓትና ሂደት ይናገራሉ። የአብረን እንታደም የጥሪ ግብዣም ያቀርባሉ።

09-25
08:55

“ የተቀበልኳቸው ታላላቅ ሽልማቶች እና እውቅናዎች ተጨማሪ ሀላፊናትን መሸከም እና ጠንክሬ መስራት እንዳለብኝ የሚያስታውሱ ናቸው። ” - አርቲስት ሮፍናን

አባቴ በእኔ ስኬት ውስጥ ታላቅ ስፍራ አለው ፤ ዩኒቨርሳል ሙዚቃ ያቀረበልኝን ውል ስፈርም በእነሱ ቅድመ ሁኔታ ስይሆን በእኔ ምርጫ የተሻለ ውል እንድፈርም የረዳኝ የአባቴን ምክር እና የሕይወት ፍልስፍና መስማቴ እና መከተሌ ነው ፤ ይለናል ሁለገቡ አርቲስት ድምጻዊ ፤ ገጣሚ ፤ አቀናባሪ ፤ ዲጄ እንዲሁም ድምጻዊ ሮፍናን ኒሪ ሙዘይን ነው ።

09-25
28:57

"ደሲ ለእግዚአብሔር ቃልና ለፍቅር የተረታች ናት፤ በሕልፈቷ ድንጋጤ ውስጥ ነው ያለሁት፤ ያለ እሷ እንዴት እንደምኖር አላውቅም" የፓስተር ደሲ ባለቤት አቶ ዓይናለም ካሱ

የመንፈሳዊ ሕይወትና የበጎ አድራጎት አገልጋይዋ ፓስተር ደሲ ባይሳ ከእዚህ ዓለም በሕልፈት ተሰናብተዋል። "አታልቅስ፤ ነገ ይነጋል" ነበር የመጨረሻ ቃሏ ያሉትን ታላቅ ወንድማቸውን ተክሉ ባይሳ አክሎ፤ ቤተስብና ወዳጆች ጥልቅ ሐዘናቸውን ይገልጣሉ። የፓስተር ደሲ የቀብር ሥነ ሥርዓት እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 ከቀኑ 2:00 pm በ Bulla Cemetery Lane, Bulla ይፈፀማል።

09-25
23:55

“ራሴን ማድመጤ የተሻለ ሙዚቃን ይዤ እንድመጣ ረድቶኛል ፤ በራሴ መንገድ የመጣሁበት ሙዚቃ ፍሬውን ሳይ እድለኛ ነኝ እንድል ያደርገኛ -አርቲስት ሮፍናን

የሙዚቀኛ ውጤት የሚታየው በሚዚቀኛው ጥረት ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ የአስተሳሰብ አቅጣጫ ነው ። አገር ሰላም ሲሆን ማህበረሰብ ሲራጋጋ የኪነጥበብ ባለሙያዎችም ጥሩ ስራን ይዘን መቅረብ እንችላላን፤ የሚለን የሙዚቃ ስራውን በአውስትራሊያ እያሳየ ያለው ሁለገቡ አርቲስት ድምጻዊ ፤ ገጣሚ ፤ አቀናባሪ ፤ ዲጄ እንዲሁም ድምጻዊ ሮፍናን ኒሪ ሙዘይን ነው ።

09-24
29:45

- አንቶኒ አልበኒዚ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጋር በጥቅምት ወር ሊገናኙ ቀጥሮ ተቆረጠ

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጋዛ የእስራኤልን ወረራን ተቃወሙ

09-24
06:09

ዜና -አውስትራሊያዊቷ የከፍታ ዘላይ ኒኮላ ኦላሳርገን የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነች

እስራኤል የፍርስጤማውያንን ነጻ አገር የመሆን ጥያቄ መቼውንም ቢሆን እውቅናን አልሰጥም አለች፤

09-22
06:26

አገርኛ ሪፖርት - " ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ

" ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ

09-21
13:04

"ነቢይ አይደለሁም፤ ነቢይ እንዳልባል እንጂ ሁለቱም [ኢትዮጵያና ኤርትራ] ተለያይተው የሚኖሩ አይመስልም" ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ

በሕይወት ዘመናቸው "ኤርትራውያን ጀግናዎች ናቸው፤ ጥሩ ተዋጊዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ስር ወድቀዋል። "አንድነት ኢትዮጵያ" ብለው የሔዱ ናቸው" ያሉን የቀድሞው የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ፣ የብሔራዊ ውትድርና መምሪያ ኃላፊና የ "ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር" መጽሐፍ ደራሲ ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ተለይተዋል። ዝክረ መታሰቢያ ይሆናቸውም ዘንድ ቀደም ሲል በወርኃ ኖቬምበር 2014 ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ ደግመን አቅርበናል።

09-16
23:21

"ባሕላችን ለትውልድ እንዲቀጥል ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው መጥተው ስለ ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንዲያስረዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን" ወ/ት ገነት ማስረሻ

ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 በ Kensington Town Hall በማኅበሩ አስተባባሪነት ስለሚከበረው የ2018 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ይገልጣሉ።

09-16
13:25

አውስትራሊያን አክሎ 42 ሀገራት በኢትዮጵያ የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ባለበት መቆሙና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለተመድ አስታወቁ

እስከ አንድ ወር ጊዜ ይወስድ የነበረውን አዲስ የንግድ ምዝገባና ዕድሳት አሠራርን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል በመቀየር በሁለት ቀናት መጨረስ የሚያስችል ሥርዓት ይፋ ተደረገ

09-16
09:31

"የእኛ ዕድር ከዘርና ሃይማኖት ነፃ የሆነ ነው፤ ኑ ተደጋግፈን ማኅበራዊ ሕይወታችንን እናጎልበት፤ መልካም አዲስ ዓመት" የኢትዮ-አውስትራሊያ አንድነት መረዳጃ ዕድር

የኢትዮ - አውስትራሊያ አንድነት ዕድር ሰብሳቢ አቶ መስቀሉ ደሴ፣ ፀሐፊ ብሩክ ይማ እና የበዓል አስተባባሪ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ይልማ፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2018 እና የመስቀል በዓል በጣምራ ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰብ አባላት ጋር በፐርዝ ከተማ Koondoola Community Centre ለማክበር ስላሰናዱት የበዓል ዝግጅት ፕሮግራም ይናገራሉ። የአንድነት ጥሪም ያቀርባሉ።

09-15
11:12

የጥምር ዜግነት ጉዳይ በአጀንዳነት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀረበ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሔደው ጦርነት ሳቢያ በኢትዮጵያ ላይ ጥለውት የነበረውን የተለያዩ ዕቀባዎችን የያዘው ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ፤ በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ፀንቶ እንዲቆይ ተወሰነ

09-14
12:29

"ኢትዮጵያ ውስጥ የሁሉንም ክልልሎች ይሁንታ ለማግኘትና ዲሞክራሲም ሥር እንዲሰድ ለማድረግ ፕሬዚደንታዊ ሥርዓት ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም

ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ ስለምን የሶስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ የምርምር ፅሁፋቸውን ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ አውጥተው "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ስያሜ ለመፅሐፍነት ለማብቃት እንደወደዱ ያነሳሉ፤ ጭብጦቹንም ነቅሰው ይናገራሉ።

09-13
25:02

"የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚታየው የሀገር ቤት ነፀብራቅ ነው፤ ሀገር ቤት ያለው ሁኔታ እየሰከነ ሲሄድ የዳያስፖራውም እንደዚያ ይሆናል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም

የ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ መፅሐፋቸው ውስጥ ያሠፈሯቸውን አንኳር ምክረ ሃሳቦች ፋይዳ ነቅሰው ያስገነዝባሉ።

09-12
23:44

"የኢኮኖሚ ዕድገት ኢትዮጵያዊነት እንዲለመልም ያደርጋል፤ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት የሚያስገኘውን ጥቅም እንዲያውቅ ማድረግ ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም

ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ለሕትመት ስላበቁት መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ይናገራሉ።

09-12
15:05

2018 - አዲስ ዓመት፣ አውደ ዓመት፣ ዕንቁጣጣሽ

የ"ክብረ በዓላት፤ ሃይማኖትና ባሕል" መፅሐፍ ደራሲ መላኩ ጌታቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘመን ቅመራና ባሕላዊ አከባበር ያስረዳል።

09-11
18:22

Recommend Channels