DiscoverContinental Drift
Continental Drift

Continental Drift

Author: Eden Teshome

Subscribed: 0Played: 0
Share

Description

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.
55 Episodes
Reverse
በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያ ቡና ዘርፍ ከአውሮፓ ህብረት አዳዲስ ደንቦች እና ከምርት መገኛ (traceability) መስፈርቶች አንጻር ያለውን እውነታ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ እና ሉዓላዊነት ጉዳዮችን በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የቡናሮማ ቡና ኤክስፖርተር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቤል አየለ እንዲሁም የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሌክቸረር እንዳለ ንጉሴ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት በማርኬቲንግ እና በፈጠራ ስራዎች ውስጥ እየጫወተው ያለው ሚና እጅግ እየጨመረ መጥቷል። ቴክኖሎጂ ዜግነት ባይኖረውም፣ የየሀገራቱን ማህበራዊና ባህላዊ አውድ የተረዱ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት እና ከደቡብ-ደቡብ አጋሮች ጋር መተባበር ለአፍሪካ እና ለኢትዮጵያ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ ጠቀሜታ አለው።"ወደ ቴክኖሎጂ ሲመጣ ቴክኖሎጂ ዜግነት የለውም። ነገር ግን የየሀገራቱን የተለያዩ አውዶች የተረዱ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕቀፎችን የሚያለሙ አገራት ሁልጊዜ የላቀ ዕድል ይኖራቸዋል። አሁን የደቡብ-ደቡብ አጋርነት አገራትን ስንመለከት፣ ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ ጋር በባህል ረገድ ያላቸው መመሳሰል የላቀ ነው። እናም ይህ መመሳሰል የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ ብልጫ ሊሆን ይችላል።" — መቅደላ መኩሪያ የኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንትበዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን የማርኬቲንግ ስራዎችን፣ ዳታ ሉዓላዊነትን እና የደቡብ-ደቡብ አጋርነትን ፋይዳ እንቃኛለን። ለዚህም የኢትዮጵያ ግብይት ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከመክደላ መኩሪያ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።
«ቆሻሻን ሁልጊዜ ሰብስበን የምንጥለው ነገር ብቻ አድርገን ማየት የለብንም... ቆሻሻን በአገር ውስጥ ሰብስበን የምናቀነባብርበት እና ዋጋ የምንሰጥበት ስርአት ከገነባን፣ የንጽህና አጠባበቅ ችግሮችን ከመቅረፍ ባለፈ ንግድን፣ የሥራ እድሎችን እና እውነተኛ የኢኮኖሚ እሴትን መፍጠር እንችላለን።» ሲሉ በርናርድ ሙሳባ፣ የጃርኮ ኢነርጂ ሶሉሽንስ መስራች እና የቴክኖሎጂ ፈጣሪበስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው የ ኮንቲኔንታል ድሪፍት ፕሮግራማችን ፣ የአካባቢ ፈጠራዎች፣ ዘመናዊ የኦርጋኒክ ማቀነባበሪያ መንገዶች እና የተዋሃዱ የዋጋ ሰንሰለቶች ቆሻሻን እንዴት ወደ ሥራ፣ ኃይል እና ኢንዱስትሪ እንደሚቀይሩ አእና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ በምን መልኩ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆኑ እንቃኛለን።በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉውን ቆይታ በማዳመጥ አፍሪካ ለዘላቂ ልማት የራሷን መንገድ እንዴት እየገነባች እንደሆነ ይረዱ
የአፍሪካ ሀገራት የማዕድን ሃብታቸውን በጥሬው ከማስወጣት ባለፈ በአገር ውስጥ እሴት ጨምሮ ማቀነባበር እና የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነትን መቀነስ ለኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸው ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ክልል ያስመረቀችው ብሔራዊ የከበሩ ብረቶች ማጣሪያ ፋብሪካ ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር፣ የተሻለ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ቀጣናዊ የንግድ ማዕከል ለመሆን ትልቅ ምዕራፍ ነው።"የአፍሪካ ሀገራት ገንዘባቸውን ለመደገፍ ወርቃቸውን ሸጠው የአሜሪካ ዶላር ከሚገዙ—እንደ ጋና እና ናይጄሪያ ልምድ—የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች፣ ማለቴ የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች ሁሉ፣ ጋና እያደረገችው እንዳለው ሁሉ የሀገራቸውን ምንዛሪ ጠንካራ መሠረት ለማስያዝ የወርቅ ሀብታቸውን በቀጥታ በሪዘርቭነት መያዝ ይኖርባቸዋል።" ሲሉ አለም አቀፍ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ዴኒስ ፐርሲቫል ኩአይኮኢ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን አዲስ የከበሩ ብረቶች ማጣሪያ ፋብሪካ፣ የወርቅ እሴት መጨመር እና የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች የወርቅ ሪዘርቭ ፖሊሲ ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ያላቸውን ፋይዳ እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ከሆኑት ከዴኒስ ፐርሲቫል ኩአይኮኢ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ።
«የሀገራትን የብድር ምዘና ፍትሃዊነትና ገለልተኝነት ማሻሻል በራሱ በአሁኑ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ብቻ ለአፍሪካ በየዓመቱ ከ3 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር ማዳን ያስችላል። የመንግሥት ልማት ድርጅቶችንና የግል ኢንቨስትመንቶችን ስንጨምር ደግሞ ይህ ዓመታዊ ቁጠባ ከ10 እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር ሊበልጥ ይችላል።» ሲሉ የ ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚካኤል አዲሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን አፍሪካ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ያቋቋመችውን የአፍሪካ የብድር ምዘና ተቋም በተመለከተ በሰፊው እንቃኛለን ፡፡ የዚህ ተቋም መቋቋም ለአፍሪካ ኢኮኖሚ የሚኖረውን ፋይዳም በሰፊው ለመዳሰስ ከፈርስት  አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አነጋግረናቸዋል፡፡ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ
loading
Comments