DiscoverTurning Africa Forward
Turning Africa Forward

Turning Africa Forward

Author: በርናባስ ተስፋዬ

Subscribed: 0Played: 0
Share

Description

Turning Africa Forward - ከቴክኖሎጂ እና አስተዳደር እስከ ባህል፣ ዲፕሎማሲ እና ከዚያም ባለፈ፤ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ ለማደግ የምታደርገውን ጽኑ ጉዞ የሚመሩ ምልከታዎችን በዝርዝር እንዳስሳለን።
36 Episodes
Reverse
በዛሬው ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ የመስቀል በዓል መንፈሳዊና ማህበራዊ ትርጉም፣ ሀገር በቀል የእርቅና የፍትህ ስርዓቶች፣ በዩኔስኮ የተመዘገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ፋይዳና እንክብካቤ፣ እንዲሁም እነዚህን ባህላዊ ሀብቶች ለደቡብ-ደቡብ የቱሪዝም ዲፕሎማሲ እና ለአህጉራዊ የእውቀት ሽግግር ማዋል በሚቻልበት ስትራቴጂ ላይ ከፎክሎር ተመራማሪዋ ዶክተር ፍሬሕይወት ባዩ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፖድካስት ክፍላችን፤ የቻይና እና ሩሲያ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ አጋርነት እያሳየ ያለውን ፈጣን እድገት፣ የምዕራባውያን ማዕቀቦች ውጤት አልባ መሆን፣ አፍሪካ ከእርዳታ ወጥታ ጥሬ ዕቃዎቿ ላይ እሴት በመጨመር እና ከቀረጥ ነፃ የንግድ እድሎችን በመጠቀም የምታገኘውን የኢኮኖሚ ነፃነት፣ በዶላር የበላይነት ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን እና የBRICS አዲሱን የልማት ባንክ መጠቀም፣ እንዲሁም ከቻይናና ሩሲያ በሚደረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር የአፍሪካን የዳታ ሉዓላዊነት የማረጋገጥና የኢትዮጵያ AI ተቋም ክፍለ-አህጉራዊ የማዕከልነት ሚና ላይ ከምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው ቶላ ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ትንተና አጠቃለን ይዘንላችሁ ቀርበናል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፖድካስት ክፍላችን፤ አፍሪካ ከዓለም አቀፉ የዳታ ማዕከል አቅም ከ1 በመቶ ያነሰ ድርሻ ብቻ መያዟ የሚያስከትለውን የዲጂታል ጥገኝነት ስጋት፣ የሀገር ውስጥ የግል ባለሀብቶችን በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ላይ የማሳተፍ አስፈላጊነትን፣ የህዝብ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል በመቀየር ለሀገር በቀል AI ሞዴሎች ግብአት የሚሆን ዳታ ማዘጋጀት፣ ከሩሲያና ከሌሎች የግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር በሚደረግ ስትራቴጂካዊ ትብብር የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊና ቴክኒካዊ እንቅስቃሴ ላይ ከዶ/ር ዋለልኝ ተዋበ ጋር ያደረግነውን ሰፊ ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል።
''አሜሪካ አብዛኛውን ጊዜ ከአፍሪካ ወይም ከደቡብ ዓለም የሚመጡ ውሳኔዎችን እና ሃሳቦችን በመቃወም የምትታወቅ ሀገር ነች። የደቡብ ዓለም ድምፅ እየተሰማ በሄደ ቁጥር የምዕራባውያን የበላይነት እየተዋጠ የአፍሪካ ተፅዕኖ እያደገ እንደሚሄድ ስለሚታወቅ፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሃሳቡ መልካም ሆነ አልሆነ አሜሪካ የመቃወም ልማድ አላት፤'' ሲሉ የፖለቲካ እና አስተዳደር ምሁሩ ጂሬኛ ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በቶጎ አነሳሽነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቀረበው ረቂቅ ውሳኔ ላይ የተመዘገበውን የ164–1 ታሪካዊ የድምፅ ውሳኔ፣ የአሜሪካን በብቸኝነት ተነጥላ መቅረት፣ የሜርኬተር ካርታ ያደረሰውን ስነ-ልቦናዊ ተፅዕኖ፣ እንዲሁም አፍሪካ በትክክለኛው የእኩል ምድር ሞዴል በኩል የመልክዓ-ምድራዊ ሉዓላዊነቷን የምታረጋግጥበትን ስትራቴጂዎች ከምሁር ጂሬኛ ታደሰ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡
 ''በጦርነትና በወረራ ከተዘረፉ ቅርሶች በንግድ መልክ ገንዘብ ለመስበስብ የሚደረግ ጥረት በምንም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው የሞራል ውድቀት ነው። ቅርሶቻችንን በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለን የምንገዛበት ሳይሆን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት አዲስ የትግል ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፤'' ሲሉ የታሪክ ተመራማሪና አንትሮፖሎጂስቱ አሉላ ፓንክኸርስት(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።​በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፖድካስት ክፍላችን፤ ሞስኮ ለአፍሪካ ታሪካዊ ፍትህና የቅርሶች መመለስ ያሳየችውን ድጋፍ፣ 500,000 የሚሆኑ የአፍሪካ የጥበብ ሀብቶች በውጭ ሀገራት መበተናቸውን፣ እና በ1868 በመቅደላ ከተዘረፉት መካከል በቅርቡ በ250,000 ዩሮ አቡዳቢ ውስጥ ለጨረታ የቀረበውን የ18ኛው ክፍለ ዘመን የጎንደር ወንጌል ያለ ክፍያ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ የህግና የዲፕሎማሲ ትግል ከአሉላ ፓንክኸርስት(ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል።​ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡
loading
Comments