DiscoverAfrican Heights Show
African Heights Show

African Heights Show

Author: ወሰንሰገድ አሰፋ እና ዐቢይ ሀብታሙ

Subscribed: 0Played: 0
Share

Description

ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።
19 Episodes
Reverse
“የሆሊውድ ተጽእኖ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው፤ ጉዳቱ ያመዝናል ግን ቢሆንም ጠቃሚነቱም ደግሞ የሚካድ አይደለም። [...] ምዕራባውያን በአብዛኛው ፊልሞቻቸው ላይ የበላይነታቸውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ […] በተቃራኒው ደግሞ የአፍሪካን ኋላቀርነት እና አስከፊ ገጽታ ለመገንባት ይሞክራሉ፤ ይህም ትውልዱ ራሱን እና ሀገሩን የሚያይበትን መንገድ የተበላሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡” ሲል አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ፣ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ግጭት ጉዳዮች ተመራማሪ እና መምህር አሌክሳንደር ኃይማኖት(ዶ/ር) አፍሪካ ከጥሬ እቃ አቅራቢነት እሴትን ወደ መጨመር እንዴት ልትሸጋገር እንደምትችል ሀሳባቸውን የሚያጋሩን ሲሆን፤  በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የፊልም እና ቲያትር ባለሙያ ከሆነው ከአርቲስት ቢኒያም ወርቁ ጋር በመሆን የምእራብያውያን የፊልም እና ሌሎች የጥበብ ስራዎች ቀሪውን ዓለም የሚቃኙበት እና የሚያቀርቡበት መንገድ እንዴት ባለ መልኩ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንዳለ፣ አፍሪካ እና አፍሪካውያን ስለእራሳቸው ስላላቸው አመለካከት ላይ በተለይ የሆሊውድ የፊልም ኢንደስትሪ ያደረሰው አሉታዊ ጫና እንዲሁም የአፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የስነጥበብ ባለሙያዎች ይህን የባህል ወረራ እንዴት ባለ መልኩ መመከት እንደሚችሉ በሰፊው ቃኝተነዋል፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:
''ታላላቅ ሳይንቲስቶቻቸውን ብታይ ከእነ ኢቫን ፓብሎቭ ጀምሮ ሌሎቹን ጨምሮ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደረገ ሀገር ነው። ግን ምዕራቡ የሚከተለውን እሳቤ ማሳየት ስለሚፈለግ ያንን ነገር ለማሳነስ ይሞክራል'' - ሲሉ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ተማሪ  ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ መሠኗዳችን በክፍል አንድ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ እና በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎቸ መካከል በቋንቋ እና ባህል ረገድ ስለተመሰረተው ግኑኝነት በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በዩኒቨርሲቲው ስር ያለው የአለቃ ገብረሃና የባህል ጥናት እና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መሰረት ወርቁ ጋር ቆይታ ያደረግን ሲሆን፤  በክፍል ሁለት ደግሞ ሩሲያ በአፍሪካውያን ዓይን ምን ትመስላለች? የምዕራባውያን መገናኛ በዙሃን ያዛቡትን የሩሲያ ምስል እንዴት መቀየር ይቻላል በሚለው ጉዳይ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ተማሪ  ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ሃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
''የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመጠበቅ ሂደት ቅድሚያ ኃላፊነቱን ለአካባቢው ማኅበረሰብ መሥጠት ተገቢ ነው — ብዙ እንግዶች ከራሺያ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ አውቃለሁ። እንደ ክፍተት የማየው ነገር የራሺያኛ ቋንቋ የሚናገሩ አስጎብኚዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው አነስተኛ ነው  ... በእንግሊዘኛ ለማስጎብኘት እንደሚገደዱ አውቃለሁ። ምናልባቱ ይህ ትንሽ ሊያስቸግራቸው ይችላል'' ሲሉ የቱሪዝም ባለሙያ ታከሌ ኛሜ ከአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል።በዛሬው የአፍሪካ ሃይትስ ፕሮግራም ሁለት ወቅታዊና ተመጋጋቢ የቱሪዝምና የባህል ጉዳዮችን እንዳስሳለን። በክፍል አንድ፣ የኢትዮጵያን የቱሪዝም አቅም፣ በዘርፉ ያሉ እድሎች እና ሀገራችን ከዚህ ዘርፍ ሊያገኘችው የሚገባውን ጥቅም እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል እንቃኛለን። በክፍል ሁለት ደግሞ የመስከረም ወር የባህል ድምቀቶችን፣ በተለይም የመስቀል በዓልን፣ ባህላዊ እሴቱን እና ለቱሪዝም ዘርፉ ያለውን ፋይዳ እንዳስሳለን።የቱሪዝም ባለሙያዉ ታከሌ ኛሜ በሁለቱም ክፍሎች በመሳተፍ፣ በቱሪዝም ዘርፉ ያሉ እድሎችን እንዲሁም የመስቀልና የመስከረም ወር የባህል ድምቀቶችን በተመለከተ ያላቸውን ሀሳብና ዕይታ ያካፍለናል።
"ራሴን እንደ ምሁር ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ተማሪ አድርጌ ባስቀመጥኩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በቋንቋዎቻችን ውስጥ ያለውን ጥልቅ የፍልስፍና ይዘት ይበልጥ ለመረዳት ችያለሁ።[…]ሰዎች ባሉበት ሁሉ አስተሳሰብ አለ፤ አስተሳሰብ ባለበት ሁሉ እውቀት አለ፤ እውቀት ባለበት ሁሉ ደግሞ ፍልስፍና አለ፡፡” ሲሉ ደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር ሻባላኒ ኖኩቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ መሠኗዳችን በክፍል አንድ አፍሪካ የዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነቷን የተቀናጀ እና የጋራ በማድረግ የውጪ ጣልቃ ገብነትን እንዴት መመከት ይቻላል በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የዓለም አቀፍ ቢዝነስ አማካሪ ከሆኑት ዙበሪ ሊጂያና የተወያየን ሲሆን፤  በክፍል ሁለት ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መምህርት ፕ/ር ሻባናኒ ኖኩቱላ ጋር አፍሪካ የፖለቲካ ነፃነት ብታገኝም፣ ብዙ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም የአፍሪካን ታሪክ፣ ቋንቋዎች እና የእውቀት ሥርዓቶች ወደ ጎን በሚገፉ የቅኝ ግዛት ዘመን መዋቅሮች ውስጥ እየሰሩ ስለሚገኙበት ምክንያት፣ እነዚህ ውርሶች እንዴት እንደቀጠሉ እና መቀየር ስለሚቻልባቸው መንገዶች እንወያያለን፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:
''ከጥሬ እቃ በተያያዘ፣ ጥሬን ወደውጭ ልኮ መልሶ በውድ ዋጋ መቀበሕ ጤነኛ ዓዕምሮ የሚቀበለው ነገር አይደለም። የአፍሪካ ባለሃብቶች ባህሪያታቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል። አነስተኛ ቢዝነስ ላይ ስለሆነ በብዛት ትኩረት የሚያደርጉት እሱ ራሱ መሻሻል ይኖርበታል። በማዕድን ዘርፍ አፍሪካ ያላትን የመደራደር አቅም ባለሃብቶቹ በራሳቸው ማየት ይኖርባቸል - ሲሉ ዶ/ር መሀመድ ኢብራሂም፣ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር እና የማህበረ-ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ ለስፑትኒክ አፍራካ ተናግረዋል።''ሁለት ወሳኝ አፍሪካዊ ጉዳዮችን በሚዳስሰው የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ አፍሪካ ያላትን ወሳኝ ማዕድናት ሀብት እና ማዕድናቱን በአገር ውስጥ እሴት ጨምሮ የማቀናበር እድሎችና ተግዳሮቶችን እንቃኛለን።በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር እና የማህበረ-ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ  ዶ/ር መሀመድ ኢብራሂም  በዚህ ዙሪያ ያላቸውን ዕይታና ትንታኔ ያካፍሉናል። በክፍል ሁለት ደግሞ የጤና ሉዓላዊነትን፣ በጤና ዘርፉ የሚካሄደውን ሽግግር እና ይህ ለአፍሪካ በአህጉራዊ ደረጃ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ እንዳስሳለን። በቂሊንጦ ስፔሻል ኢኮኖሚክ ዞን የኢንቨስተሮች ማኅበር ፕሬዝዳንት ተሾመ በየነ ስለጉዳዩ ያላቸውን ሀሳብና ልምድ ያካፍሉናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ 
loading
Comments