DiscoverAfrican Heights Show
African Heights Show

African Heights Show

Author: ወሰንሰገድ አሰፋ እና ዐቢይ ሀብታሙ

Subscribed: 0Played: 0
Share

Description

ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።
26 Episodes
Reverse
በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም የአፍሪካ አትሌቲክስ ኃያልነት መሠረት በማድረግ ከዓለም ክብረወሰኖች እስከ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ድረስ፣ ከስፖርተኞች የቪዛ እገዳ እስከ ድርብ መሥፈርት (Double standard) ያሉ ጉዳዮችን እንዳስሳለን።ለዚህም እንግዳችን ታሪኩ ተመቸ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌቲክስ አሰልጣኝናተባባሪ ተመራማሪ ደግሞ ሙያዊ ዕይታቸውን ያጋሩናል።    
“የፓን-አፍሪካን የክፍያና ሴትልመንት ሥርዓት አህጉራዊ የንግድ ትስስርን ለማፋጠን የተዘረጋ ግዙፍ የፋይናንስ መሠረተ-ልማት ነው። ነገር ግን ባንኮች ጉዳዩን የቴክኖሎጂ ማገናኘት ፕሮጀክት አድርገው ብቻ የመመልከት ስህተት ይፈጽማሉ። […]ባንኮች ቀጣይነት ካለው የሳይበር ደህንነት እና የጽናት ዝግጁነት ባሻገር የታመነ የዲጂታል ባንክ ሥርዓት መገንባት አለባቸው።” ሲሉ የአይቲ ኦዲትና ዲጂታል ጎቨርናንስ ባለሙያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ማህበር (EISAA) ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እስክንድር መስፍን ቸርነት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፡ በክፍል አንድ፡ የፓን-አፍሪካን የክፍያና ሴትልመንት ሥርዓት አህጉራዊ የንግድ እና የፋይናንስ ትስስርን ለማፋጠን ያለውን ሚና፣ ባንኮች በቅጽበታዊ ክፍያዎች ዘመን ሊኖራቸው የሚገባውን የሳይበር ደህንነት፣ የመረጃ ጥበቃ እና የጽናት ዝግጁነት ከባለሙያው ከእስክንድር መስፍን ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን፤ በክፍል ሁለት፡ አፍሪካ አህጉር የተፈጥሮ ሀብት ጥገኝነትን በመቀነስ፣ ወጣቱን የሕዝብ ቁጥር ፣ ትምህርትን፣ ቴክኖሎጂንና የሰው ኃይል ልማትን እንደ መሠረት በመጠቀም እንዴት ጠንካራና ዘላቂ የምጣኔ ሐብት እድገትን መገንባት እንደምትችል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሌ (ዶ/ር ) እይታቸውን አጋርተውናል፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
''የሰው ሰራሽ አስተውህሎት አስማት አይደለም። ኃይሉ የሚወሰነው በመረጃው ጥራትና በመረጃው መገኘት ላይ ነው። ቴክኖሎጂ በቀላሉ የሚታዘዝ ነገር ብቻ መሆን የለበትም፤ የሠው ሰራሽ አሰተውህሎትም ሆነ ሌላ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ከእውነታችንና ከአካባቢያችን ጋር ማጣጣም አለብን — ሰው ሰራሽ ብዙ ሀብት የሚፈልግ ቴክኖሎጂ ነው፤ ስለዚህ በትንሹ መጀመር እና አሁን መንቀሳቀስ አለብን። የሁሉንም ሰው ሕይወት እየነካ ነው'' ሲሉ ዮናስ ገብረሚካኤል ድፈር፣ የባዮ እና አመርጂንግ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የኮምፒዩቲሽናል ሳይንስ እና የመረጃ ስርዓት ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አቀፍ የትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ አውድን ስንዳስስ ዛንዲሲዌ ራዴቤ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ዲፓርትመንት የዶክትሬት ተማሪ ሀሳቡን ያጋሩናል።በክፍል ሁለት የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ እውቀት (AI)፣ ቴክኖሎጂን እንደገና መቅረጽ እና ፈጠራን ማስፋፋት በተመለከተ ዮናስ ገብረሚካኤል ድፈር በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮምፒውቴሽናል ሳይንስ እና የኢንተለጀንስ ሲስተምስ ዳይሬክተር ደግሞ ሙያዊ ዕይታውን ያጋራናል።በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበው ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ፡
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሀይትስ ዝግጅት፡-በክፍል አንድ  ሕይወትን እንደገና መገንባት — የሴት ልጆች ግርዛት በአፍሪካ የሚያስከትለው የሕክምናና የሰብዓዊ ዋጋን እንወያያለን። ዶ/ር ቡለንት ቺሃንቲሙር፣ ዝነኛው የፕላስቲክ እና የመልሶ ህክምና ቀዶ ሐኪም ደግሞ ሙያው ትንታኔ ያጋሩናል።በክፍል ሁለት የአፍሪካ ወጣቶችን ማብቃት — የነገ መሪዎችን ስለመገንባት ዳሰሳ ስናደርግ ከናይሮቢ ኬንያ፣ የአመራር ባለሙያው ጄሚ ማክአፖሎ  ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።
ከፖለቲካዊ ነፃነት የሚሻገረው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል "ሉዓላዊነት ሁለት ዓይነት ነው፤ የውስጥና የውጭ የሚባሉ። የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችን መንገድ ብቻ ተከትለን የምንሄድ ከሆነ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ችግር ነው የሚሆነው - የፈፀሟቸውም ድርጊቶች ተገቢ አይደሉም በዚህም ታዳጊ ሀገራት ለሉዓላዊነታቸው መታገለል ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ሁለት ዐበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦ በክፍል አንድ፦ “የአፍሪካ ከቀደሙት ቅኝ ገዢዎቿ ሙሉ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገው ትግል አስፈላጊነት”  ከራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) ጋር የተወያየንበት ሲሆን፤ በክፍል ሁለት፦ “የኑክሌር ኤነርጂ ትብብር በብሪክስ ሀገራት መካከል” በሚለው አህጉራዊ አጀንዳ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ታዋቂ ተመራማሪ ጌታቸው አዳም ወርቅነህ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንቃኘዋለን።    ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
loading
Comments