በታጣቂዎች እገታ ስር የነበሩ 3 የኦሮምያ ክልል አቃቤያነ ሕግ መለቀቃቸው
Update: 2025-12-08
Description
በኦሮምያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞንውስጥ እገታ ስር ከነበሩ 3 የኦሮምያ ክልል አቃቢያነ ሕግ ባለፈው ቅዳሜ መለቀቃቸውን የኦሮምያ ክልልየአቃቤያነ ሕግ ማኅበር ዛሬ አስታወቀ ። እገታው በተፈጸመበት ወቅት ከተያዙት መካከል አንዱ መገደላቸውን ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። ቀሪዎቹም በአጋቾች እጅ እንደነበሩም በወቅቱ ተገልጿ ነበር። ከታጋቾቹ አንዱ ፅኑ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ናቸው ።
ለመሆኑ ታጋቾቹ እንዴት ተለቀቁ? ሂደቱስ እንዴት ነበር እገታውን የተመለከቱ መረጃዎቹን ሲከታተል ከነበረው ባልደረባችን ታምራት ዲንሳ ጋር ስለ አቃቤ ሕጉ ግድያና የሌሎቹ አቃቤያነ ሕግ እገታ መቼና የት እንዴት እንደተካሄደ ሂደቱም እንዴት እንደነበረ እንዴት እደተለቀቁ አጭር ቃለ ምልልስ አድርገናል።
ታምራት ዲንሳ
ኂሩትመለሰ
Comments
In Channel























