DiscoverDW | Amharic - Newsየሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈው የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውና የአውሮጳውያን ሚና
የሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈው የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውና የአውሮጳውያን ሚና

የሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈው የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውና የአውሮጳውያን ሚና

Update: 2025-12-01
Share

Description

የዩክሬን ሩስያ ጦርነት አራት ዓመት ሊደፍን ከሦስት ወር ያነሰ ጊዜ ነው የቀረው። ጦርነቱ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ሩስያበዩክሬንዋና ከተማ በኪቭ የአየር ድብደባ አካሂዳለች። ቀደም ሲልም ዩክሬን ጥቁር ባህር የሚገኙ የሩስያ ነዳጅ ዘይት ማጠራቀሚያዎችን መታለች። ጦርነቱ እየጠነከረ በሄደበት በዚህ ወቅት ላይ ከጎርጎሮሳዊው ህዳር አጋማሽ በኋላ ይፋ በሆነው፣ ጦርነቱን ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስ በነደፈችው እቅድ ላይ ከዩክሬን ጋር ተከታታይ ንግግሮችንና ውይይቶችን እያካሄደች ነው።



ትናንትም የዋሽንግተንና የዩክሬን ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚሁ የሰላም እቅድ ላይ ፍሎሪዳ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተነጋግረዋል። ዩክሬን ከግዛቷ የተወሰነውን አላባቢ ለሩስያ እንድትለቅ የቀረበ ጥያቄን በሚያካትተው በባለ 28 ነጥቡ የሰላም እቅድ ላይ ትናንት እሁድ ፍሎሪዳ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተነጋገሩት የሁለቱም ሀገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውይይት በጣም ውጤታማ እንደነበር አስታውቀዋል።



የአሜሪካን ፕሬዝዳት የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በእቅድ ላይ የሩስያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ነገ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዋሽንግተን ሰላም ሊያወርድ ይችላል ስትል በነደፈችው እቅድ በገፋችበት በዚህ ወቅት ላይ የዩክሬንፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ዛሬ ፓሬስ ውስጥ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ጋር ተነጋግረዋል። ዩክሬን ጦርነቱን እንድታሸንፍ የሚፈልጉትአውሮጳውያን ባለፈው ሰሞን ጄኔቫ ውስጥ ተሰብስበው ለሰላም እቅዱ የበኩላቸውን ማሻሻያ ከማቅረብ ውጭ የትናንቱን የፍሎሪዳው ንግግር ጨምሮ በአሜሪካን የሰላም እቅዱ ሂደት አልተሳተፉም። ንግግሩ የቀጠለው አውሮጳውያኖች በሌሉበት ነው።





የአሜሪካን የሰለም ጥረት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮደግፍ እንደሚባለው በሙስና ይጠረጠሩ የነበሩት የዜሌንስኪ ቀኝ እጅ የሚባሉት የዩክሬን ዋነኛ ተደራዳሪና የካቢኔያቸው ሃላፊ ስራቸውን ለቀዋል። በትናንቱ የፍሎሪዳው ድርድር ንግግር ላይ የተገኙት አዲስ የዩክሬን ተደራዳሪ ናቸው።



የትናንቱ የፍሎሪዳ ንግግር ለቀጣይ ውይይቶች ምን ያህል ጠቃሚ ይሆናል ? ተስፋስ የሚጣልበት ይሆን?ዩክሬን አጣብቂኝ ውስጥ ባለችበት በአሁኑ ጊዜ ዋነኛ ተደራዳሪዋ በሙስና ተጠርጥረው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸው በሰላም እቅዱ ላይ ምን ተጽእኖ ያሳድር ይሆን? ስየሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈውን የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውንና የአውሮጳውያንን ሚና የቃኘው ከብራሰልሱ ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴ ጋር የተካሄደውን ቃለ መጠይቅ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ



ገበያው ንጉሴ



ኂሩት መለሰ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈው የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውና የአውሮጳውያን ሚና

የሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈው የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውና የአውሮጳውያን ሚና