ጥርጣሬ የበዛበት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ-ሩዋንዳ የሰላም ስምምነት
Description
ጥርጣሬ የበዛበት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ-ሩዋንዳ የሰላም ስምምነት
ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው አፍሪቃ "ታሪካዊ" የሰላም ስምምነትን ስታካሂድ፣ በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከባድ ውጊያዉ እንደቀጠለ ነዉ። የዳግም ግጭቶች መቀስቀስ፣ በመሪዎች መካከል ያለ አለመተማመን እና የአሜሪካ የማዕድን ፍላጎት ማስጠንቀቂያዎች መሬት ላይ ያለውን ደካማ እውነታ ፍንትዉ የሚያሳዩ ናቸዉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩዋንዳውን ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኪዲ ባለፈዉ ሐሙስ አዲስ ወደ ተሰየመው ዶናልድ ጄ.ትራምፕ የአሜሪካ የሰላም ተቋም ዉስጥ ተፈራርመዋል። ትራምፕ የሰላም ስምምነት ያሉትን ስምምነት መፈራረማቸዉን ዋይት ሀውስ አስታዉቋል። ስምምነቱ የፀጥታ ጥበቃ ከኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ማዕድናት አጋርነት ጋር በማጣመር የቀረበ ጥቅል ነዉ። መሬት ላይ ግን ጦርነቱ ገና አልተጠናቀቀም። በኮንጎ ደቡብ ኪቩ ግዛት ባለስልጣናት ባለፈዉ ረቡዕ እንደገለፁት ሰብዓዊ አደጋዉ እየተባባሰ ነዉ።
የካጋሜ–ትሺሴኪዲ ስምምነት በዋሽንግተን ተሞገሰ፣ በጎማ ተሳለቀ
በኤም 23 ቁጥጥር ስር በምትገኘው የካዚባ ከተማ የአስተዳደር ባለስልጣን ሬኔ ቹባካ ካሌምቢሬ እንደተናገሩት “ብዙ ቤቶች በቦምብ ተደብድበዋል፣ ብዙ ሕይወት ጠፍቷል።” ብለዋል። የኤም 23 አማፂ ንቅናቄ ባለፉት ወራት ጎማ እና ቡካቩን ጨምሮ ዋና ዋና ከተሞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጅምላ መፈናቀል እና የዜጎች ሞት አስከትሏል። ይህ እንቅስቃሴ በኪንሻሳ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በገለልተኛ ተመራማሪዎች በሩዋንዳ እንደሚደገፍ ተገልጿል። ይሁን እና ኪጋሊ የሚገኘዉ የሩዋንዳ መንግሥት ውንጀላውን አጣጥሏል።
ኪንሻሳ የሩዋንዳ አላማ ጠየቀች
ረቡዕ በዋሽንግተን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የ DW ዘጋቢ ጃኔል ዱማሎን የኮንጎ ባለስልጣናት እየተባባሰ የመጣውን ግጭት እንዴት እንደሚተረጉሙት ጠይቋቸዋል። የኮንጎ ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ፓትሪክ ሙያያ ሩዋንዳ ሰላም አትፈልግም ነዉ ያሉት።
"ሩዋንዳ ሰላም እንደማትፈልግ ማረጋገጫ ነው… እና ይህ ስምምነት ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የበኩላችንን መወጣታችንን ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው።"
"ይህ ስምምነት ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የበኩላችንን መወጣታችንን ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው… ለኛ ሰላም ማለት የሩዋንዳ ወታደሮች ሃገራችን መልቀቅ ፤ ይህ ማለት ለኤም 23 ማንኛውንም አይነት ድጋፍ ማቆም ማለት ነው" ሲሉ ፓትሪክ ሙያያ ለዶቼ ቬሌ አክለዉ ተናግረዋል።
በማዕድን እና በጦርነት የተጋረደ የሰላም ስምምነት
ትራምፕ በጎርጎረሳዉያኑ ጥር ወር ወደ ነጬ ቤተመንግሥት ለሁለተኛ ዘመን ከተመለሱ በኋላ ተከታታይ የዓለም ሰላም "ድሎች" ብለው የሚጠሩትን ደጋግመው አክብረዋል። ዲሞክራቲክ ኮንጎ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቀጥሎ በቀጣይ የተሰለፈች/ የተገኘች ነች ሲሉም ተናግረዋል። ለኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች እና የላቀ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አስፈላጊ የሆኑትን ወሳኝ ማዕድናት ለአሜሪካ ለማስገኘት የሚያስችል መግቢያ በር ነዉም ብለዋል።
ኮንጎ በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የኮባልት ክምችቶች፣ እንዲሁም መዳብ፣ ታንታለም፣ ወርቅ እና ሊቲየምን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂያዊ ሃብቶች የታደለች ሃገር ናት። ባለፈዉ ሐሙስ ፀደቀ የተባለዉ ስምምነት በተለያዩ ምሶሶዎች ዙሪያ የተዋቀረ ነው፡ ግጭቱን ለማስቆም የሚያስችል የፀጥታ ስምምነት፣ የምዕራባውያንን ኢንቨስትመንት ወደ ታላቋ ሀይቆች ክልል ለመሳብ የሚያስችል የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ እና "ስትራቴጂካዊ አጋርነት" ዩኤስ በተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ እና ልማት ላይ ሚና እንዲኖራት የሚያደርግ ነው።
ፖለቲካዊ ትችት አቅራቢዎች፣ የስምምነት መድረኩ ዋሽንግተን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ያጋልጣል፣ ይህም የማዕድን አቅርቦትን በአፋጣኝ የሰላም ፍላጎት ወይም ከዚያ በላይ በማድረግ ላይ ነው።የኮንጎ ዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች መሪ የፓሲ ሙባላማ ለDW እንደገለፁት “ለአሜሪካ ይህ የኢኮኖሚ ስምምነት ብቻ ነው…”
"ለአሜሪካ ይህ የኢኮኖሚ ስምምነት ብቻ ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ በክልሉ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ጥበቃ ከግምት ውስጥ አላስገቡም። ህጻናት አሁንም እየሞቱ ነው፣ ሴቶች አሁንም እየተደፈሩ ነው"
ሩዋንዳ 'ሰላም በሂደት ላይ ነው'
የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪየር ንዱሁንጊሬህ ለሮይተርስ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ የተካሄደውን ጦርነት አምነው ሁኔታው እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል። "ሰላም በሂደት ላይ ነው...በአንዳንድ ቦታዎች ላይ መረጋጋትም እየመጣ ነዉ። ከዚህ በኋላም የግዛት መስፋፋት የለም።" ብለዋል።
የተኩስ አቁም ጥሰት የፈጸመው የኮንጎ ጦር ነው፤ የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በኤም 23 እና በሲቪሎች ላይ “የተዋጊ ጄቶች እና በሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጥቃት ፈፅመዋል” ሲሉ ከሰዋል።
ተንታኞች የኪጋሊን አቋም ይሞግታሉ
የሩዋንዳ ተመራማሪ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሳሙኤል ቤከር ቢያንሲ፤ የኪጋሊን ትረካ አጥብቀው ይሞግታሉ። "ሩዋንዳ ወታደሮቿ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ ለመከላከል አልመዉ የተገኙ ናቸዉ ስትል እየዋሸች ነው" ሲሉ ተናግሯል።
"ሩዋንዳ ወታደሮቿ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ ለመከላከል ዓላማ ይገኛሉ ስትል እየዋሸች ነው። የካጋሜ አገዛዝ አዲስ መስምሪት ወይም ነገሮችን መባባስ በፈለገ ቁጥር ምክንያት መሆኑን ለዓመታት ታይቷል። ሁሉም ነገር በ FDR ገለልተኛነት ላይ የተመሰረተ ነው የሚለው ሀሳብ ከታማኝ የጸጥታ ክርክር በላይ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኗል"
በM23 እና በሩዋንዳ መከላከያ ሃይሎች ተጽእኖ ስር ያሉ አካባቢዎች ማስፋቱን ጠቁመዋል። "በአማፂያን በተያዙ አካባቢዎች ያለው የአካባቢ አስተዳደር በሩዋንዳ ወዳጅነት ስር የሚሰራው ነው። ማዕድናት በህገወጥ መንገድ መዉጣቱ ቀጥሏል። ተንታኙ አክለዉ እንደገለፁት፤ ታሪክ እንደሚያሳየው የኪጋሊ መንግሥት ቃል ኪዳኖችን እምብዛም አያከብርም።
"በጎርጎረሳዉያኑ 2013 የተካሄደዉ የኮንጎ ሩዋንዳ ስምምነትን መመልከት ይቻላል። ሩዋንዳ ሁልጊዜ በተለዋጭ ቡድኖች፤ በስለላ መረቦች ወይም በልዩ ሃይሎች በኩል አድርጋ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዉስጥ የመቆየት መንገድን ስታገኝ ይታያል። የኪጋሊ መንግሥት የሆነ ነገር ከፈረመ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ይጀምራል።
የተኩስ አቁም ታሪኮች ጥርጣሬን ይፈጥራሉ
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ አክቲቪስቶች እና በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሚገኙ ሲቪሎች የዋሽንግተኑ መንግሥት ከዕለታዊ እውነታ ጋር የተቆራኘ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። "አሁንም ሰዎች እየተገደሉ ነው… እዚህ ያለው ሁኔታ አሁንም በጣም አስቸጋሪ ነው" ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች መሪ ሙባላማ ተናግረዋል።
"መንግስት ለፖለቲካዊ ድል ቅድሚያ ሰጥቷል ብዬ አስባለሁ. M23 እና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሪፐብሊክ ጦር ኃይሎች (ፋርዲሲ) አሁንም እየተዋጉ ነው እና ብዙ ሰዎች እየሞቱ ነው። ስለዚህ አሁንም እዚህ ያለው ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው።"
ከሐሙስ ከሰላም ስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ከመካሄዱ ከሰዓታት በፊት በኮንጎ ደቡብ ኪቩ ግዛት ጦርነት እንደቀጠለ ነበር። ሬኔ ቹባካ ካሌምቢሬ እንዳሉት በኤም 23 ቁጥጥር ስር በምትገኘው የካዚባ ከተማ በደረሰው ጥቃት ብዙዎች ተገድለዋል። የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የምስራቅ ኮንጎ ነዋሪዎች ጦርነቱ መባባሱን ተናግረዋል።
አዜብ ታደሰ /ሚሚ ሜፎ
ፀሐይ ጫኔ























