DiscoverDW | Amharic - Newsለንደን፤ ዜሌንስኪ፤ ከሜርስ፤ ማክሮን እና ስታርመር ጋር ለንደን ላይ ተገናኙ
ለንደን፤ ዜሌንስኪ፤ ከሜርስ፤ ማክሮን እና ስታርመር ጋር ለንደን ላይ ተገናኙ

ለንደን፤ ዜሌንስኪ፤ ከሜርስ፤ ማክሮን እና ስታርመር ጋር ለንደን ላይ ተገናኙ

Update: 2025-12-08
Share

Description

በዩክሬን የሚካሄደዉን ጦርነት ለማስቆም ዛሬ ለንደን ላይ ስብሰባ እየተካሄደ ነዉ። በፍሎሪዳ የዩክሬን እና የዩናይትድ ስቴትስ ተደራዳሪዎች ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ፤ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ዛሬ ሰኞ ከአውሮጳ አጋሮቻቸው ጋር ለንደን ላይ እየመከሩ ነዉ። ዛሬ ለንድን ላይ እየተካሄደ ባለዉ ዉይይት የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ከጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሪድሪክ ሜርስ፣ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከብሪታኒያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር ጋር በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ላይ እየተወያዩ ነዉ። ከዉይይቱ ቀደም ሲል የብሪታኒያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር፤ ለዩክሬይን ሰላም ለማስገኘት የምናደርገዉ ጥረት እድገት እያሳየ ነዉ ብለዋል። የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ፤ የአዉሮጳ ሃገራቱ መሪዎች ከዜሌንስኪ ጋር ለመወያየት የተቀመጡት የዩኤስ የዩክሬን እቅድን በተመለከተ ነዉ። ከዉይይቱ ቀደም ሲል የብሪታኒያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በበኩላቸዉ ለዩክሬይንሰላም ለማስገኘት የምናደርገዉ ጥረት እድገት እያሳየ ነዉ ብለዋል።



«ፕሬዝደንት ዘሌንስኪ ዛሬ ስለ ሰላም እቅዱ የግል ውይይት ለማድረግ እዚህ በመምጣታቸው በጣም ተደስቻለሁ። ሁላችንም ወደ ሰላም ማግኘት እንፈልጋለን፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአራት አመት በፊት ጀምሮ የተወረሩት ዩክሬናውያን ሰላምን ይፈልጋሉ። እጅግ ከፍተኛ ችግር ዉስጥ ናቸዉ፤ ብዙ ነገር ጠፍቷል። እርግጥ ነዉ ጥቃት የምታደርሰዉ ሩሲያ ናት። እና የትኛውም የተኩስ አቁም ፍትሃዊ እና ዘላቂ መሆን አለበት። ይህ ዛሬ ከሰአት በኋላ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። የሆነ ነጥብ ላይ እንደርሳለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ትኩረት የምናደርገዉ እዚህ ላይ ብቻ ነዉ።»



የሃገራቱ መሪዎች ለንደን ላይ ለዉይይት ከመቀመጣቸዉ በፊት፤ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬይኑፕሬዚዳንት ዜለንስኪን የአሜሪካን የዩክሬን እቅድን አላወቀዉም ሲሉ ከሰዋል። ዋሽንግተን ላይ በተካሄደ አንድ የሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት ትራምፕ በሰጡት አጭር መግለጫ «ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ሀሳቡን እስካሁን አለማንበባቸው ትንሽ ቅር ብሎኛል ብዬ መናገር አለብኝ።» ብለዋል።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ለንደን፤ ዜሌንስኪ፤ ከሜርስ፤ ማክሮን እና ስታርመር ጋር ለንደን ላይ ተገናኙ

ለንደን፤ ዜሌንስኪ፤ ከሜርስ፤ ማክሮን እና ስታርመር ጋር ለንደን ላይ ተገናኙ