DiscoverDW | Amharic - Newsሞስኮ፤ የዩክሬን ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ አሜሪካ፤ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው
ሞስኮ፤ የዩክሬን ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ አሜሪካ፤ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው

ሞስኮ፤ የዩክሬን ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ አሜሪካ፤ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው

Update: 2025-12-02
Share

Description

አሜሪካ ዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው። የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች ጃሬድ ኩሸር እና ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ ሞስኮ ውስጥ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሜሪካ ያለፉትን ቀናት ከፍሎሪዳ እስከ ጄኔቫ አልፎም እስከ አቡዳቢ ባካለለው የዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ደም አፋሳሽ የሆነውን የሞስኮ ኪዬቭ ጦርነት ለማስቆም «ትልቅ ተስፋ መሰነቋን » አስታውቃለች።ነገር ግን ኪየቭ እና የአውሮጳ አጋሮቿ ዊትኮፍ ከክሬምሊን ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመተቸት ልዩ ልዑኩ የተተቹት አሁንም የዩክሬንን መሬት ለሞስኮ አሳልፈው ይሰጣሉ የሚል ስጋት ገብቷቸዋል። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ሞስኮ በዩክሬን ሰላም ከማስፈን ይልቅ የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለማቃለል ከአሜሪካ ጋር በሚደረግ ድርድር ተጠቅማለች በማለት ከሰዋል።

የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተሰማው ሞስኮ የምስራቃዊ የዩክሬኗን የፖክሮቭስክ ከተማን መቆጣጠሯን ባሳወቀችበት ወቅት ነው። ምንም እንኳ ዩክሬን ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ከእጇ መውጣቱን ሳታረጋግጥ በዙሪያው ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን ብትገልጽም። ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ የራሴ ነው የምትላቸውን ጋዛቶች ኪየቭ አሳልፋ እንድትሰጥ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል።





ታምራት ዲንሳ



አዜብ ታደሰ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ሞስኮ፤ የዩክሬን ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ አሜሪካ፤ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው

ሞስኮ፤ የዩክሬን ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ አሜሪካ፤ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው