DiscoverDW | Amharic - Newsሶሪያ፤ አንድ ዓመት ክበሺር አላሳድ በኋላ
ሶሪያ፤ አንድ ዓመት ክበሺር አላሳድ በኋላ

ሶሪያ፤ አንድ ዓመት ክበሺር አላሳድ በኋላ

Update: 2025-12-08
Share

Description

ሶሪያ፤ አንድ አመት ክበሺር አላሳድ በኋላ



በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር በ2011 የተቀጣጠለውን የአረብ አብዮት ተክትሎ በሶሪያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ በህይል ለመደፍለቅ የተደረገው ሙከራ፤ በሶሪያ የርስ በርስ ጦርነትን ወልዶ ህዝብ ካስጨረሰና አገር ካወደመ በኋላ፤ ባለፈው አመት በዚች ዕለት እ እ ኣውሮፓውያኑ አቆጣጠር ዴሴምበር 8 ቀን ነበር በአማጽያን ተጋድሎና ትግል የአልበሺር አላሳድ የ14 መት የአገዛዝ ዘመንና የቤተስባቸው የበርካታ አስርት አመታት ስርወ መንግስት የተገርሰሰው። ብዙም ይታወቅ ያልነበረውና ከአልቃይዳ ጋር ግንኑነት አለው ይባል የነበረው ሀያት ታሂሪር አልሻም የተባለው አማጺ ቡድን በመሪው አህመድ አልሻራ እየተመራ ባሽር አላሳድን አስወግዶ ሶሪያን ማስተዳደር ከጀመረ እነሆ አንድ አመ ሆነው። የድህረ አሳድ ሶሪያ እንዴትና የለውጡ መሪዎች ፈተናዎች በዛሬው ማህደረ ዜና ዝግጅት የምናተኩርባቸው ናቸው.



የሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ጅማሮና ያስክተለው ውድመት



ሶሪያ ወደ እርስ በርስ ጦርነ ት የገባችው እ እ እ በ2011 ዓም በአረቡ አለም የተቀጣጠለውን የአረብ አብዮት ወይም አረብ ስፕሪንግን ተክትሎ በሶሪያም ከአባት ወደ ልጅ እየተላለፈ የቀጠለውን አገዛዝ በመቃወም የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ ለመድፈቅ ወታደራዊ እርምጃ በመወሰዱ ነው። በትረ ስልጣኑን በሞት ከተለዩት አባታቸው እ እ እ በ2000 አም የተረከቡት በሺር አላሳድ የዴሞክራሲና የለውጥ ጥያቄዎችን ባነሱ ሁሉ የወሰዱት የህይል እርምጃ በርካታ ሀይሎችን ወደ አመጽና የርስ በርስ ጦርነት ከቶ፤ አገሪቱን ላስራ አራት አመታት በጦርነት እንድትለበልብና ህዝቧ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለሞትና ለስደት እንዲዳረግ አድርጎታል። ጦርነቱ ባለብዙ ታሪኳዊቷን ሶሪያን እንዳልነበርች አድርጎና ፍጹም አውድሞ ነው ያለፈው። ህዝቧንም በአለም ፊት በስደት እንዲባዝን በማድረግ በታሪክ የሚጠቀስ ሁኗል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደተገለጸው በሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ያለቀው ሰላማዊ ህዝብ 600 ሺ፤ የተፈናቀሉና የተሰደዱት ደግሞ ከአስራ ሶስት ሚሊዮን በላይ ነው። ፡

በዚህም ምክንያት ዛሬ ሶሪያውያን አገራቸውን እንዳልነበር ያደረገውና ህዝባቸውን ታይቶ ለማይታወቅ ጦርነት የዳረገው ያሳድ ዘመን ያበቃበትን አንደኛ አመት የሚያከብሩት በተደበላለቀ ስሜት ነው። በደረሰው ውድመትና መተላለቅ ቁጭትና ሀዘን፤ በተገኘው ድልና አዲስ ጅማሮ ደግሞ ተስፋ። በመሆኑም እለቱ ለሶሪያውያን የቁዘማ ግን ደግሞ የደስታም ነው።፡



አህመድ አልሻራና ድርጅታቸው ተቀባይነት የማግኘቱ ሚስጥር



አህመድ አልሻራ በድል ደማስቆ ከገቡና ካሳድ ኩበለላ በኋላ፤ የሽግግር መንግስቱ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተሰየሙ የሰጧቸው መግለጫዎችና ያሰሟቸው የድርህረ አሳድ ሶሪያ ህልሞች፤ ለበርካታ በጥርጣሬ ለሚያዩዋቸው ሶሪያኖችና አለማቀፉ ማህብረሰብ አይን ገላጮች ነበሩ። ወዲያው የፒረዝዳንት አሳድን የአገዛዝ መዋቅሮች በማፈራርሰና እስረኖችን በመፍታት፣ የንግግርና የመጻፍ ነጻነትንም ባለመገደብ በዕበውነትም በሶሪያ ኣዲስ ዘመን እየመጣ መሆኑን ለማሳየት ሞከሩ።





ያውሮፓ ህብረትም ፈጥኖ ለአመታት በሶሪያላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ማንሳቱን አስታወቀ። የመንግስታትና አለማቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችና ጋዤጦኞችም ወደ ደማስቆ መትመም ጀመሩ። ባለፈው አንድ አመት ወደ ሶሪያ የተጓዙት ዲፕሎማቶችና ባለሙያዎች በጠቅላላው ያአሳድ ዘመን ወደ ስፍራው ከተጓዙት ዲፕሎማችና መልክተኞች ይበልጣል ነው የሚባለው።



አልሻራና ፕሬዝዳንት ትራምፕ



ያምናው ያማጺ ቡድን መሪና ያአሁኑ የሽግግር መንግስት ፕሬዝዳንት ሚስተር አልሻራና ድርጅታቸው ቀደም ሲል ከአልቃይዳ ጋር ይሰሩ እንደነበርና እሳቸውም በግል በአሸባሪነት ተፈርጀው ያገኛቸው ወይም ያሉበትን የጠቆመ የ10 ሺ ዶላር ሺልማት እንደሚሰጠው አሜሪካ ማስታውቂያ ያውጣችባቸው እንድነበርም ይታወቃል ።። ሆኖም እሳቸውም ሆኑ ድርጅታቸው እ እ ከ2016 ጀምሮ ካአልቃይዳ ተለይተው ለሶሪያያ ነጻነትና ከአምባገነን አስተዳደር መላቀቅ ይታገሉ እንደነበር ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን፤ ደማስቆን እንደተቆጣጠሩም ቀድሞ ተቀላቅለዋችው የንበሩትን አልቃይዳንና ሌሎች አክራሪ ድርቶችን አውግዘው አስተምርህሮቶቻቸውንም እንደማይቀበሉና እንደማይከተሉ በይፋ አስታውቁ። በእነዚህና ሌሎች አቋሞቻቸውን እርምጃዎቻቸው፤ አልሻራ የብዙዎችን አውሮፓውያንን ብቻ ሳይሆን ባንድ ወቅት በተፈላጊ አሸባሪነት ፈርጃቸው የነበረችው አሜሪካ መሪ ፕሬዝዳንት ትራምፕም ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ ኋይትሀውስ በመጋበዝ አድናቆታቸውንና ድጋፋቸውን ችርዋቸዋል። በሶሪያ ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብም በግዚያዊነት እንዲነስ አዘዋል። ሶሪያአሜሪካ በምትመራው አለማቀፍ የጸረ ሽብር ግብረ ሀይል አባል እንድትሆን እይሚፈልጉም አስታውቀዋል። ሶሪያ ከእስራኤል ጋርም ግንኑነት እንድትመስርት ፍላጎታቸው መሆኑንም ገልጸዋል ፕሬዝዳንት ትራም፤ ምንም እንኳ አልሻራ በዚህ በኩል ያሰቡት ባይታወቅም።

የ43 አመቱ ጎልማሳ ሚስተር አልሻራም ሆኑ ድርጅታቸው በመእራባዉያን ዘንድ መታመን ያገኙበትና ወደ አለማቀፉ ማህብረሰብ የተቀየጡበት ግዜ ፈጣን እንደሆነ ነው በብዙዎች የሚነገረው። ። ከመካክለኛው ምስራቅ እስከ አውሮፓና አሜሪካ ሁሉም አብረዋቸው እንደሚሰሩና አገራቸውን ዳግም ለመገንባት በሚያደርጉት ጥረትም ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው እየገለጹላቸው ነው፤።



በአገር ውስጥ ያሉት ችግሮችና ፈተናዎች



ሆኖም በውጭ ግንኑነት ብኰል ብዙ የቀናቸውን ያህል ሚስተር አሻራ በአገር ውስጥ ገና ብዙ እንደሚቀራቸው ነው የሚነገረው። የመንግስት መዋቅሮችና ተቋማት ገና እንደፈራረሱና የህዝብ አግለልግሎትም በተሟላ ሁኔታ እየተሰጠ እንዳልሆነ ነው የሚታየውና የሚሰማው። የኢኮኖሚ ሚኒስትር አማክሪ ሚስተር ኦስማን ካዲ እንደሚሉት ያገሪቱ ችግሮች ገና አልተነኩም፤” በዙ ፈተናዎች ነው ያሉበን ። ብዙዎቹ ከማዕቅቡ ጋር የተያያዙ ናቸው፤ የገንዘብ እጥረትም አለብን። ኢንቭስተሮች እንዳይገቡ ምክኒያት የሆኑት የተጣሉት ማዕቀቦች ናቸው፤ ሆኖም አሁን ማዕቀቡ እየተነሳ በመሆኑን ችግሮቹ ይቃለላሉ ብለን ተስፋ እንዳደርጋለን ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

በዳግም ግንባታው በኩል ከሶሪያ ዲያስፖራ ብዙ የሚጠበቅ ሲሆን ኧስካሁን አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራዎች ወዳገራቸው እንደተመለሱ እየተገለጸ ነው። ሰሞኑን በየደማስቆስ አውሮፕላን ጣቢያ መቼ እንደሚመለሱ ሳያውቁ በተለያየ መንገድ ካገር ወተው የነበሩ ሶሪያውን ሲመለሱ የሚስተዋለው ደስታና ለቅሶ ሶሪያውያን ያሳለፉትን መራራ ግዜ የሚያስታውስ ነው።





እየተፈጸሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችና ስጋቶች



ይህ በዚህ እንዳላ ሶሪያ ግን አሁንም ከችግር የጸዳችና አስተማማን ነች ማለት እንዳለሆነ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት። ከአልሻራ ስልጣን መጠናከር ጋር ለዴሞራሲስና ፍትህ ሲታገሉ የነበሩ ቡድኖች እየተገለሉ መሆናቸው አሳስቢ እንደሆነ ነው እንዚህ ታዛቢዎች የሚናገሩት ።፡ አንዳንዶች አልሻራና ጎዶቻቸው ጭራሹንም ስልጣናቸውን አጠናክረው ወደገዥነት እንዳይለወጡ ስጋት ያላቸው መሆኑንም ይናጋራሉ። የሰባዊ መብቶች ይዞታ እንደተሻሻለና የፕሬስ ነጻነትም እንዳልተገደበ ቢነገርም፤ በተጨባጭ ግን ብዙ የመብት ጥሰቶችና ግድያዎች ጭምር እነሚፈጸሙ የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ሚስተር ታሚን አል ካሲም ገለጸዋል፤ አሁንም በተለይ የአናሳ ማህበረስቦች አባላትና ከቀድሞው መንግስት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚባሉ ግለሰስቦች ላይ ኢላማ የተደረጉ ግድያዎች እየተፈጸሙ ነው።፡ የአሳድ መንግስት ከወደቀ ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጥይትና በድንጋይ ሳይቀር ተገድለዋል” በማለት ሁሉም አይነት ያለፉም ይሁን ያሁን ግዜ ግዜ የመብት ጥሰቶች ምርመራ ሊደረግባቸውና ወንጀለኞች ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።



አዲስ የአስተዳደር መዋቅር አስፈላጊነት



ሶሪያየተለያዩ ብሄሮችና ሀይማኖቶች ያሉባት አገር በመሆኗ አዲሱ መንግስት በተለይ ያናሳ የህብረተሰብ ክፍሎችን መብት ሊያስጠብቅና አመኔታቸውን ሊያገኝ የግድ መሆኑን የሶሪያን ፖለቲካና የማህበረስብ ስሪት የሚያውቁ ምሁራን እያሳሰቡ ነው። ከሶሪያ ህዝብ አምሳ ከመቶው የሱኒ ሙስሊሞች ሲሆኑ ሌሎች የክርስቲያን የአለዊት ድሩዝና ኩርድ ማህብረሰቦች በሶሪያ አናሳ የህብርተሰብ ክፍሎች ናቸው። እስካሁን በተለይ አለዊት በሚባሉት በሽር አላሳድ የወጡበት ማህበረሰብ እንዲሁም ድሩዝ የሚባል አናሳ ማህብረሰብ አባላት ላይ በአሻራ የጸጥታ ሀይሎች ጥቃት እንደተፈጸመና ስጋትም እንዳለ ነው የሚነገረው:።



በዚህ በኩል አዲሱ መንግስት ልዩ ጥንቃቄ ሊያደረግና ጦርነቱ የፈጠረውን አዲስ ስነልቦናና ማንነት ከግምት ውስጥ ያስገባ ያስተዳደር መዋቅርም ሊፈጥር የሚገባው መሆኑን በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሞክስ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሪም ቱርክማኒ አጥብቀው ያሳስባሉ፤ “ በሶሪያ ብዙ የተለያዩ ማህበርሰቦችና ሀይማኖቶች አሉ። ከበርካታ ብሄሮች፣ ልዩ ልዩ ሀይማኖቶችና ነገዶች የወጡ ህዝቦች የሚኖሩባት ናት። ባለፈው ግዜ እነዚህ ለዩነቶች ብዙም ትኩረት አይሰጣቸውም ነበር። አሁን ግን ጦርነቱ ሰዎች ወደ ማንነታቸውና ህይማኖታቸው እንዲሳባሰቡ ያደረጋቸው በመሆኑ ከእንግዱህ የሚኖረው የመንግስት መዋቅር በጂኦግራፊ ባቻ ሳይሆን ማንነትንም ያካተተ መሆን ይኖረበታል በማለት ባሁኑ ውቅት ግን ብዙዎች እንደተገለሉ እየተሰማቸው በመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበዋል



ገበያው ንጉሴ



ኂሩት መለሰ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ሶሪያ፤ አንድ ዓመት ክበሺር አላሳድ በኋላ

ሶሪያ፤ አንድ ዓመት ክበሺር አላሳድ በኋላ

ገበያው ንጉሤ