DiscoverDW | Amharic - Newsበባቲ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የደረሰው ሽምግልና ግጭቱን «እንዳይመለስ» አድርጎ ሸኝቷል
በባቲ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የደረሰው ሽምግልና ግጭቱን «እንዳይመለስ» አድርጎ ሸኝቷል

በባቲ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የደረሰው ሽምግልና ግጭቱን «እንዳይመለስ» አድርጎ ሸኝቷል

Update: 2025-12-01
Share

Description

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወረዳ ከሁለት ዓመታት በላይ ለበቀል ይፈላለግ የነበረ ማህበረሰብ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት በቆየ የሽምግልና ስረዓት ዕርቅ አወረዱ ። በግጭቱ ምክንያት ይፈላለጉ ከነበሩት እና እርቅ ማውረዳቸውን ለዶቼ ቬለ የገለጹ የማህበረሰቡ ተወካዮች እንዳሉት በህግ ያልቻልነውን በቆየ የሽምግልና እሴታችን ሰላም አውርደናል ብለዋል። በግለሰቦች መካከል ተቀስቅሶ ወደ አጎራባች ወረዳዎች ተስፋፍቶ የነበረው ግጭት እና መፈላለግ በእርቅ መቋጨቱ ሌሎች ችግሮችን በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት እንደሚያነሳሳ የባቲ ወረዳ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ተናግረዋል።



አቶ ጀማል አብዱ ሰኢድ በባቲ ወረዳ የ023 ቡርቃ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው ። ለወትሮም የንጽህ መጠጥ ውሃ ችግርን ጨምሮ ለበርካታ ማህበራዊ እና ኤኬኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጣ በነበረችው ቀበሌያቸው ነብስ እስከ ማጥፋት የደረሰው የርስ በርሱ ግጭት ያለፉትንሁለት ዓመታት ፈታኝ አድርጎባቸው ነበር። በወቅቱ ግጭቱ የተቀሰቀሰበትን አጋጣሚም እንዲህ ያስታውሳሉ ።



«ከዚያ ቀበሌ እኛ ቀበሌን በመውረር ከዚያም በሽማግሌም ፣ በእርቅም ታግለን ታግለን መላው ሲጠፋን ወደ ህግ እንሄዳለን ስንል የሆነች ረብሻ ተከሰተች በዚያ ተገጫጨን የችግሩ መነሻ ያው ንብረታችን ላይ እና ቀሌአችን ላይ ነው በሚል ነው። »

በዚያው የባቲ ወረዳ የቦፋ ከሚሴ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሙሔ በሽር እንደሙሉት ለሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያትየነበረው እና ከሚጎራበታቸው የቡርቃ ቀበሌ ጋር በበቀል እና መፈላለግ ላይ የተመሰረተው የሁለት ዓመታት ግጭት በእርቅ ተፈቷል።

«በቡርቃ ቀበሌ እና በቦፋ ከሚሴ ቀበሌ የሁለት ዓመታት የግድያ መከሰት ነበር ።በዚህ አማካኝነት በሁለት ዓመቱ አሁን በወረዳ እና በቀበሌ አማካኝነት ተሰባስበን አሁን ለታ ጁመዓ ተገናኝተን በአ,ዋሳኝ ቀበሌ ላይ ፍርድ ተሰጥቶ ፣ ለሞተውም ካሳ ፣ጉማ ፤ ለቆሰለውም ካሳ ፣አስታርቀን በሰላም ተለያይተናል። »





ችግሩ በዚህ ቢቀጥል ኖሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት ግጭት ሊያስከትል ከጫፍ ደርሶ እንደነበር የገለጹት የቡርቃ ቀበሌ ነዋሪው የወረዳው አስተዳደር ባህላዊ የእርቅ መንገድ መሻቱ መፍትሄ አስገኝቶልናል ፤ ይላሉ ።





«ጎፋ የሚባል ከወዲያ አምስት መቶ በላይ የሆነ ሰው ፤ ከቡርቃ ከአምስት መቶ በላይ የሆነ ሰው ሊጋጠም ነበር ፣ ባቲ ላይ ጠንካራ አስተዳደር ስላለ ከበላይ ያለ አበጋር አንስቶ ጥሩ እርቅ መሰረቱ ፣ 1,326,000 ብር ለሶስቱ ተፈረደ።»

የባቲ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በማሕበራዊ መገናኛ ገጹ ባጋራው መረጃ 2ቱ ቀበሌ አዋሳኝ ላይ በመሬት ይገባኛል ግጭት ተነስቶ በሰው ሂወትና በአካል ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በቀበሌዎቹ ጎሳዎች መካከል ወደ በቀል ጥል ያደገውን ግጭት በባህላዊ የሽምግልና ስርአት በዳይን በመቅጣትና ተበዳይን በመካስ የእርቅ ስርአት እንዲፈፀም መደረጉን አትቷል።

በግለሰቦች መካከል ተቀስቅሶ የማህበረሰብ ወደ መሆን እያደገ የነበረውን ግጭት በመፍታት ሂደት አስተባባሪ እንደነበሩ የነገሩን የባቲ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈድሉ አብዱ ግጭቱ ከቁጥጥር ውች መሆን የሚችልበት ዕድል ነበረው።





«ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት የቆየ ግጭት ነበር መነሻው የእርሻ መሬት ይገባኛል በሚል ምክንያት ከግለሰቦች የተነሳ ነው። ከዚያ ወደ አርጎባ አጎራባች ወረዳ ሰው ሞቶባቸዋል፤ ከእኛም እንደዚሁ የሞተ አለ። እያለ እያለ ጠቡ እየተስፋፋ ወደ አራት ወደ አምስት ቀበሌ እያደገ የነበረ ግጭት ነው።»

በባቲ ለመሰል ችግሮች የቆየ ባህላዊ መዳኛ እና የሽምግልና እሴት አሁንም ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን የጠቆሙት የስራ ኃላፊው ፈታኝ ለነበረው የማህበረሰብ ግጭት መፍትሄ አምጥቷል ባይ ናቸው።

«ሽማግሌዎች አሉን ባህል አለን ። የኃይማኖት አባቶች አሉን ፤ በዚያ መንገድ መፈታት እንዳለበት ስለምናምን አሁን የምልህ ቀጣና ላይ ደግሞ የትናንቱን ውሎ አደር ባህሉን እሴቱን ያልተወ ማህበረሰብ ከመሆኑ አኳያ በዚህ መልክ እንደ ግብአት ተጠቅመንበታል። »





ለወትሮም በበርካታ የታጣቂ ቡድኖች እና በኢትዮጵያመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ከሁለት ዓመታት የዘለቀ ደም አፋሳሽ ግጭት እየተደረገበት ላለው የአማራ ክልል ማህበረሰብን ከማህበረሰብ ሊያጋጩ የሚችሉ መሰል ሁነቶች የሚያስከትሉት መዘዝ ከባድ ሊሆን ይችል ነበር ። ነገር ግን ጉዳዩን ቆም ብሎ ማመልከት ለመፍትሄው መምከር ሊመጣ ያለውን ጥፋት ከሩቁ ሊያስቀር ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን በእርቁ ላይ ተሳታፊ የነበሩቱ ይናገራሉ ።

አቶ ሙሄ እንደነገሩን ፤ ስንታረቅ ላንመለስበት ነው በማለት ነበር።

«አንመለስበትም ። በጣም ደስ ይላልኮ ከወዲያም ከወዲህም ያለው ፤ ለሞተበት ካሳ ፣የእምባ ማበሻ ካሳ ብር ተፈርዷል፤ ለቆሰለውም እንደዚያው ተሳስሞ በፍቅር ነው የተለያየው»





ታምራት ዲንሳ

ጸሐይ ጫኔ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በባቲ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የደረሰው ሽምግልና ግጭቱን «እንዳይመለስ» አድርጎ ሸኝቷል

በባቲ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የደረሰው ሽምግልና ግጭቱን «እንዳይመለስ» አድርጎ ሸኝቷል

Tamirat Dinssa Geleta ታምራት ዲንሳ ገለታ