DiscoverDW | Amharic - Newsአፍሪቃ በዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ መድረክ ድምጿን እንዴት እያሰማች ነው
አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ መድረክ ድምጿን እንዴት እያሰማች ነው

አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ መድረክ ድምጿን እንዴት እያሰማች ነው

Update: 2025-12-06
Share

Description

አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ መድረክ ድምጿን እንዴት እያሰማች ነው



የዛሬ ዓመት በጎርጎረሳዉያኑ 2025 መባቻ የመጀመርያ ወር ጥር 20 ቀን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ የነጩን ቤተ- መንግሥት መንበር የተረከቡበት እና ትልቅ ለዉጥ የመጣበት እለት ነበር። በእለቱ ትራምፕ እግራቸዉ የዋሽንግተኑን ቤተ-መንግሥት ሲረግጥ፣ የዓለም ፖለቲካ አቅጣጫ መለወጥ ጀመረ። ዓለም አቀፉ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) መፍረስ፣ አሜሪካ እንደ ፓሪስ የአየር ንብረት ለዉጥ ስምምነት እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ካሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ራስዋን ማግለልዋ፤ ከዚህ ሌላ የአሜሪካ የቪዛ ፖሊሲ የመሳሰሉት የዋሽንግተን ዉሳኔዎች፤ ኃያላን የሚያደርጉት ተፅዕኖ በዓለም ሁሉ ላይ ምን ያህል ታላቅ ኃይል እንደሆነ ያሳየ ነዉ።



ትራምፕ እንቅስቃሴ፣ የአፍሪቃ ግዴለሽነት



የትራምፕ ፖሊሲዎች በዓለም ዙሪያ ያስነሱት አቧራ እና ሁከት በአፍሪቃ ሀገራት የእለት ተእለት ኑሮ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ውስን ነዉ ፤ይላሉ በአንድ ገለልተኛ አማካሪ ድርጅት ዉስጥ ተንታኝ የሆኑት ኦቪግግ ኢጉጉ “አህጉሪቱ አፍሪቃ ማለታቸዉ ነዉ አሁንም በትክክለኛ መስመር ላይ ትገኛለች። አፍሪቃ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለየምትልከዉ ትልቅ ምርት ገበያ የላትም። ወደ ውጭ የምትልካቸዉ እንደ ዘይት፣ ጋዝ፣ ወሳኝ ጥሬ ዕቃዎች እና ብረትን ያካትታል። እነዚህ ብዙውን ጊዜ ምንም ቀረጥ አይጣልባቸዉም።



የአሜሪካ ነፃ የንግድ ዕድል(አጎዋ)መስከረም ወር መገባደጃ ላይ የስምምነት ጊዜው እንዳበቃ፤ አሜሪካ ከአፍሪቃ ሀገራት ጋር እንደመጠርያዉ “እድገት እና ዕድል” በሚል የሚታወቀዉ የንግድ ስምምነት ተስፋዉ ውስን ሆንዋል። ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቃሚ የሽያጭ ገበያ የነበራቸው ጥቂት አገሮች ለምሳሌ ትንሽ ጂንስ አምራች የሆነችዉ ሌሶቶ አሁን 50 በመቶ ቀረጥ መክፈል ይኖርባታል። ወይም መኪና ላኪ የሆነችዉ ደቡብ አፍሪቃ፣ 30 በመቶው ቀረጥ ተጥሎታል።



አህጉሪቱ አሁንም በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰች ነው። በአጠቃላይ አፍሪቃ በአሜሪካ ውስጥ ለተመረቱ እቃዎች ትልቅ የኤክስፖርት ገበያ የላትም። ወደ ውጭ የሚላኩት በአብዛኛው እንደ ዘይት፣ ጋዝ፣ ፔትሮሊየም እና ወሳኝ ማዕድናት እና ብረቶች በ2025 ከተጣለው አዲስ ታሪፍ ነፃ ናቸው። ስለዚህ አህጉሪቱ የሚያመርቱ ምርቶችን ወደ ውጭ ከሚልኩ ጥቂት ሀገራት በስተቀር እንቅልፍ እያጣች አይደለችም። ደቡብ አፍሪቃ እና ሌሴቶ በቅደም ተከተል 30% እና 50% የቀረጥ ተገዢ ናቸው።



የደቡብ አፍሪቃ ቡድን 20 ስኬት



በትራምፕ አስተዳደር ደቡብ አፍሪቃ ከዋሽንግተን ጋር ያላት ግንኙነት የሻከረ ሆንዋል። ትራምፕ ለደቡብ አፍሪካ ነጭ ቡድን የፖለቲካ ጥገኝነት መስጠታቸዉ፤ በፕሪቶሪያዉን መንግሥት ላይ ቅሬታ አስነስቷል። ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የቡድን 20 ጉባኤ በአፍሪቃ ምድር ስታስተናግድ፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት እና አስተዳደሩ በጉባኤዉ አልተወከሉም። ትራምፕ ደቡብ አፍሪቃን በሚቀጥለው ዩናይትድ ስቴትስ ማያሚ ላይ በምታካሄደው የቡድን 20 አገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደማይጋብዙ አስታውቀዋል።



የኔልሰን ማንዴላ የህዝብ አስተዳደር ትምህርት ቤት ተመራማሪ ኖንሴዶ ቩቱላ፤ በደቡብ አፍሪቃ የተካሄደዉ ጉባኤ ስኬታማ እንደነበር ተናግረዋል። ቩቱላ ለ DW እንደተናገሩት "በጉባኤዉ ላይ የተነሱ ነጥቦች ፍሬ የታየባቸዉ እና ቀደም ሲል ክርክር አስነስተዉ የነበሩ የተለያዩ አመለካከቶችን ግምት ውስጥ ያስገባ እንነበር ገልፀዋል። በተለይም ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ መግለጫ እንዳይሰጥ ለመከላከል ከሞከረው ከዋሽንግተኑ መንግሥት ፍላጎት ውጪ የጋራ የመሪዎች መግለጫ ላይ መድረሱ ለደቡብ አፍሪቃ በጣም የሚያስደስት እንደሆነ አክለዋል።



ጉባኤዉን የተካፈሉት በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሃገራት፣ የአውሮጳ ህብረት እና የአፍሪቃ ህብረት፤ የአፍሪቃን "ኡቡንቱ" ፍልስፍና በመጥራት ለባለብዙ ወገንተኝነት እና ለዓለም አቀፍ ልማት አጋርነት ራሳቸውን ሰጥተዋል። “በኡቡንቱ መንፈስ፣ ብሔሮች/ሃገራት ተነጥለው ማደግ እንደማይችሉ እንገነዘባለን ሲሉ ገልፀዋል። በጉባኤዉ መጠናቀቅያ በወጣዉ መግለጫ "የአፍሪቃን ድምጽ በቡድን 20 እና በሁሉም ዓለም አቀፍ መድረኮች" የበለጠ ለማጠናከር ቃል በመግባት ነበር።



ጉባኤው ከብዙዎቹ የቡድን 20 አባላት ውክልና ነበረን በሚል መልኩ በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ ይመስለኛል። ግን ደግሞ፣ ውይይቶቹ እስከ ቡድን 20 ግንባታ ሂደት የጎለበቱ እና ሁሉንም የሚያጠቃልሉ የተለያዩ አመለካከቶችን ያካተተ ነበር፤ ። እና እንደ ደቡብ አፍሪቃ ለኛ ትኩረት የሚሰጠው ነገር ከዚህ በጣም ጠቃሚ ስብሰባ መግለጫውን ማግኘታችን ይመስለኛል።



ልማት በአፍሪካ ተጨማሪ እሴት ያስፈልገዋል



ለአስርት ዓመታት ከቅኝ ግዛት ጥላ ለመውጣት ለጣረች አህጉር የቡድን 20 ተምሳሌያታዊ ስልጣን በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የአፍሪቃ ህብረትን እና የአውሮጳ ህብረትን የመሪዎች ጉባኤ ያስተናገደችዉ አንጎላ በጉባኤዉ ላይ የጉባኤዉ ፕሬዚዳንት የነበሩት የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ ባሰሙት ንግግር “ዓለም በአንድ ወይም በሁለት ሀገራት ብቻ የተዋቀረች አይደለችም፤ መቀራረብ ከሚፈልጉት ጋር ሁሉ እንሰራለን” ብለዋል።



በሉዋንዳ በተካሄደው ስብሰባ የአውሮጳ አጋር ሀገራት «በግሎባል ጌትዌይ ኢኒሼቲቭ» በተሰኘዉ ማዕቀፍ አንጎላን ከምዕራብ ወደ ምስራቅ የሚያገናኘዉ የባቡር መስመር ዝርጋታ እንደ ሎቢቶ ኮሪደር የመሳሰሉ ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ድጋፋቸውን አረጋግጠዋል። በአፍሪቃ ሀገራት የእሴት ፈጠራን ለማስፋት ወሳኝ እንደሆነ ባለሙያዎች አፅንዖት ሰተዋል። “ይህን የአውሮጳ አጋሮችም ያውቁታል” ሲሉ ተንታኙ ኤጉኤጉ አጽንዖት ሰጥቷል።



ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፍሪቃ ሀገራት ከሩሲያ ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ካሉ ሃገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያሰፉ ነው። የምስራቅ አፍሪካን የባቡር የትስስር መስመር ለማስፋት ከዛምቢያ ጋር ሌላ የብዙ ቢሊየን ዶላር ስምምነት የፈፀመችዉ ቻይና ከአፍሪቃ ህብረት እና ከአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ጠቃሚ ሃገር ነች። ሆኖም፣ እንደ ተንታኙ ኢጉጉ ገለጻ፣ አውሮጳ የረዥም ጊዜ የአፍሪቃ ሀገራት ተፈላጊ አጋር ሆና ትቀጥላለች።



ጦርነቶች እና ወታደራዊ አገዛዝ እድገትን ያደናቅፋሉ



አፍሪቃ በዓለም ላይ ያላትን ሚና ለማዳከም የቀጠሉት ቀውሶች እና ግጭቶች፤ ለምሳሌ በሱዳን ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት እና የምስራቅ ኮንጎ ግጭት አሜሪካንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ሽምግልና ቢካሄድም ግጭቱ እንደቀጠለ ነዉ። በተጨማሪም ሰባት የአፍሪቃ ሀገራት በአሁኑ ወቅት በወታደራዊ አገዛዝ ስር ናቸው። ወደ ዲሞክራሲ የመመለስ ግልጽ ተስፋም የላቸውም። ማዳጋስካር እና ጊኒ ቢሳው በዚህ ሊጠናቀቅ ሳምንታት በቀረዉ የጎርጎረሳዉያን 2025 ዓመት ወታደራዊዉን አገዛዝ አመራር ተቀላቅለዋል።



ሰላም የሰፈነባት አፍሪቃ ለኢኮኖሚ እድገት የበኩሏን አስተዋፅዖ እንደምታበረክት ተመራማሪው ቩቱላ ተናግረዋል። ኢጉጉ በበኩላቸዉ አፍሪቃ እስከ ዛሬ ድረስ በውጭ ኃይሎች ተጽእኖ ስር ጥገኛ ሆና ትገኛለች ሲሉ ተናግረዋል። “ይህ የደካማ መንግስታት ፖለቲካዊ እውነታ ነው። አህጉሪቱ በደካማ መንግስታት የተሞላች ነች። ደካማ መንግስታት አቅምም ሆነ የፖለቲካ ልምድ የላቸውም። ሀገራዊ ሁኔታቸው ለውጭ ተጽእኖ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል።“



በማደግ ላይ ካሉ አገሮች ጋር መንቀሳቀስ



ሌላው ገጽታ የበርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያደናቀፈ ያለው አሁንም ከፍተኛ የብድር ጫና ነው። ይህ ጉዳይ ቡድን 20 ውስጥ እንደ ችግር ታይቷል። ኖንሴዶ ቩቱላ የአፍሪቃ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ለበለጠ ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እንደ መፍትሄ ይመለከቱታል። አብዛኞቹ አገሮች ስምምነቱን ማፅደቃቸውን፤ አበክረው ትናግረዋል። አሁንም ፈተናዎች ቢኖሩም "አፍሪቃ እርስ በርስ ለመገበያየት ተስፋን ይፈጥራል። በአፍሪቃ አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለት በመገንባት የአፍሪካን ኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ እንችላለን" ሲሉም አክለዋል።



ለአፍሪቃ እድገት የአፍሪቃ ሃገራት ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ሀገራት ጋር በተለይም ከግሎባል ደቡብ ሀገራት ጋር መቀላቀል አስፈላጊ ነው ሲሉ ቩቱላ ተናግረዋል። ለምሳሌ የአየር ንብረት ፖሊሲ ሊጠቀስ ይቻላል። በብራዚል ቤሌም የተካሄደው የCOP30 ጉባኤ የሚፈለገውን ያህል ውጤት አለማምጣቱን ቩቱላ ተናግረዋል።



አፍሪቃ አህጉር በዓለም አቀፍ የአስተዳደር ማዕቀፍ ውስጥ እየታዩ ያሉ የማይመስሉ ጉዳዮችን ለማራመድ በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር ተቀራርቦ መስራት አለበት የሚል አመለካከት አለ። ውጤቱን ለአብነት ካየህው ፤ የታዳጊ ሀገራት ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች በኮፕ 30 ውጤት ላይ በግልፅ ያልወጡ በታዳጊ ሀገራት ሊወሰዱ የሚችሉ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው ሀገራት እና የደቡብ ሀገራትን ማስተካከል ነው።



አዜብ ታደሰ / ፊሊፕ ሳንድረር



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ መድረክ ድምጿን እንዴት እያሰማች ነው

አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ መድረክ ድምጿን እንዴት እያሰማች ነው