DiscoverDW | Amharic - Newsኢትዮጵያ በዓለም የሰላም መመዘኛ በ2025 ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር ተባለች
ኢትዮጵያ በዓለም የሰላም መመዘኛ በ2025 ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር ተባለች

ኢትዮጵያ በዓለም የሰላም መመዘኛ በ2025 ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር ተባለች

Update: 2025-08-29
Share

Description

ኢትዮጵያ በዓለም መዘርዝር - በ 2025 ኢትዮጵያዝቅተኛሰላም ያለባት ሀገር መባልዋ



ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት እና የሰላም ጥናት ተቋም (IEP) ባወጣው ዓመታዊ "ዓለም አቀፍ የሰላም መረጃ ጠቋሚ" ዘገባ ኢትዮጵያ ደካማ የሰላም ሁኔታ ያላት ሀገር መሆንዋን ገለፀ። ጥናቱ በዘንድርዉ የ2025 ዘገባው የሀገራትን የሰላም ሁኔታ ለማመልከት 23 የሚሆኑ የጥራት እና የመጠን አመልካቾችን ተጠቅሟል።በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት ከተመለከታቸው 163 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ 138ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ኤርትራ በ132ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ኢትዮጵያና ኤርትራ በአዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች፥ የነዳጅ እጥረት



በአፍሪካ አህጉር 44 ሀገራት በጥናቱ የተካተቱ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ 36ኛ ኤርትራ ደግሞ 32ኛ ሆናለች።ዶሞክራቲክ ኮንጎ 44ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።በሪፖርቱ መሰረት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሀገራት የሚገኙበት ቀጣና የሰላም እጦት ያለበት ቀጠና ሲሆን፤ በዚህ ቀጠና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዝቅተኛ የሰላም ያላት ሀገር ተብላለች። የዓለም አቀፍ የሰላም መረጃ ጠቋሚ የጥራት እና የመጠን የሰላም መረጃ ጠቋሚ ነጥቦችን እና አመላካቾችን በመጠቀም የሀገራትን የሰላም ሁኔታ ከ1-5 ነጥብ ሰጥቷል።ጥቃት፣ግጭት እና ግጭት ያስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት ከመስፈርቶቹ መካከል ናቸው።የግጭት ተጋላጭነት ምክንያቶችና የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ



ኢትዮጵያ በአብዛኛዎቹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አስተዳደር የትጥቅ ግጭቶችን እያስተናገደች ሲሆን፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እስኪቋጭ ድረስ ከጎርጎሪያኑ ከ2020 እስከ 2022 በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል፣ከጎርጎሪያኑ ነሀሴ 2023 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ የፌደራል መንግስቱ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ ገብቷል።በኦሮሚያ ክልልም ከስድስት ዓመታት በላይ መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሃይሎች ከክልሉ እና ከፌደራል መንግስት ጋር ሲፋለሙ ቆይተዋል። ምዕራብ እና ማዕከላዊ አውሮፓ ሰላም የሰፈነበት ክልል የተባለ ሲሆን፤ አይስላንድ በቀጠናው በጣም ሰላም የሰፈነባት ሀገር ተብላለች።





ገበያዉ ንጉሴ / አዜብ ታደሰ



ኂሩት መለሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ኢትዮጵያ በዓለም የሰላም መመዘኛ በ2025 ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር ተባለች

ኢትዮጵያ በዓለም የሰላም መመዘኛ በ2025 ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር ተባለች