DiscoverDW | Amharic - Newsየኅዳር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የኅዳር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የኅዳር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

Update: 2025-12-01
Share

Description

ቸልሲ በለንደን ደርቢ አርሰናልን ትናንት ነጥብ አስጥሎ ግስጋሴውን ገትቷል ። ሊቨርፑል፣ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በተጋጣሚ ሜዳ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ በኤቲሐድ ስታዲየሙ ድል ቀንቷቸዋል ። በቡንደስሊጋው ላይፕትሲሽ እና ዶርትሙንድ አንገት ለአንገት ተናንቀዋል ። ከበላያቸው ባዬርን ሙይንሽን እንደለተለመደው ፈቅ ብሎ ተኮፍሷል ። በፎርሙላ አንድ የመኪና ሽቅድምድም የሬድ ቡል አሽከርካሪ ማክስ ፈርሽታፐን ዳግም አሸንፏል ። እድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾች ከ22 ዓመታት ወዲህ ለአፍሪቃ ዋንጫ ለማለፍ ነገ የመጨረሺያ ግጥሚያቸውን ያከናውናሉ ።



እድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪቃ ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሺያ ግጥሚያቸውን ማክሰኞ ኅዳር 23 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ያከናውናሉ ። ትናንት በዩጋንዳ አቻቸው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ውስጥ የ3 ለ0 ሽንፈት አስተናግደዋል ። ቡድኑ ከ22 ዓመታት በኋላ በመጨረሺያ ግጥሚያው ለዋንጫ ለማለፍ እድሉ ምን ያህል ነው? በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮ ስፖርት መርኃ ግብር ዋና አዘጋጅ ምስጋናው ታደሰ ውድድሮጹን ተከታትሏል ። በቀጣይ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡድን ካሸነf በሦስተናነት የማለፍ እድል አለው ብሏል።



ፕሬሚየር ሊግ



ባለፈው ሳምንት ብርቱ ጥንካሬውን ያሳየው አርሰናል ግስጋሴ ትናንት ምሽት በ10 ተጨዋች በተወሰነው ቸልሲ ተገትቷል ። ትናንት ስታምፎርደ ብሪጅ ውስጥ አቻ ለወጣው ቸልሲ ውጤቱ እንደማሸነፍ ነው የሚቆጠርለት ። 38ኛው ደቂቃ ላይ ሞይሰስ ካይሴዶ በፈፀመው ብርቱ ጥፋት በቀይ ካርድ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ ሰማያውዮቹ ከመድፈኞቹ በአንድ ተጨዋች ባነሰ ነው የተፋለሙት ። ሞይሰስ ካይሴዶ በቀይ የተሰናበተው ኳስ ለማጨናገፍ የሰነዘረው እግሩ የሚኬል ሜሪኖ ቅልጥምን ብዙም ባይጎዳውም ለስብራት ሊዳርግ በሚችል መልኩ ግን መርገጡ ነው ። ለአርሰናል ይበልጥ የሚያበሳጨው ደግሞ በ10 ተጨዋች የተወሰነው ቸልሲ በ48ኛው ደቂቃ ላይ ቀዳሚውን ግብ አስቆጥሮ እስከ 59ኛው ደቂቃ ድረስ ሲመራ መቆየቱ ነው ። ለመድፈኞቹ ግብ ያስቆጠረው ቸልሲ በ10 ተጨዋቾች እንዲወሰን ሰበብ የሆነው ሚኬል ሜሪኖ ነው ።



በብርቱ ሁኔታ በመከላከል ባገኘው አጋጣሚ የመልሶ ማጥቃት ለመፈፀም የጣረው ቸልሲ ተሳክቶለት ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል ። በ30 ነጥብ ፕሬሚየር ሊጉን ለሚመራው አርሰናል ደጋፊዎች እጅግ የሚያስቆጭ የለንደን ከተማ ተጋጣሚው ለሆነው ቸልሲ ደጋፊዎች የሚያስቦርቅ አጋጣሚ ነው ። በ10 ተጨዋች ተወስነው የደርቢ ግጥሚያውን ሳይሸነፉ መውጣታቸው የቸልሲ ተጨዋቾችን ጥንካሬ እና ቆራጥነት የሚያሳይ ነው ። በአንፃሩ እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ በእልህ በመጫወት የሚታወቀው የሚኬል አርቴታ አርሰናል በትናንቱ ግጥሚያ ያ ቁርጠኝነቱ ያን ያህል አልተስተዋለም ።



አርሰናል የማታውን ጨዋታ ቢያሸንፍ ኖሮ ምናልባትም ዘንድሮ ዋንጫውን ለመውሰዱ ይበልጥ ማረጋገጫ ይሆንለት ነበር ። ሆኖም አሁን ታች ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል እንኳን የሚበለጠው በ9 ነጥብ ነው ። ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ2 ያሸነፈው ማንቸስተር ሲቲ በ25 ነጥብ በሁለተኛነት ይከተላል፥ ልዩነቱ የአምስት ነጥብ ብቻ ነው ፥ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቸልሲ ጋር ደግሞ ስድስት ። ዎልቭስን በአንዲት ብቸኛ ግብ ትናንት ያሸነፈው አስቶን ቪላ ከቸልሲ በግብ ክፍያ ተበልጦ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ብራይተን እና ሰንደርላን በ22 ነጥብ በግብ ክፍያ ልዩነት ብቻ ተበላልጠው አምስተኛ እና ስድተኛ ደረጃ ላይ ይገኘሉ ።



ቀደም ባለው ግጥሚያ ወደ ዌስትሀምb አቅንቶ የነበረው ሊቨርፑል 2 ለ0 ድል ቀንቶታል ። ለተጨዋቾቹ፤ ለአሰልጣኝ አርኔ ስሎት እና ለደጋፊዎቹ አንዳች እፎይታ ። ለሊቨርፑል ቀዳሚዋን ግብ በ60ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው በዘንድሮ የክረምት ወራት ከኒውካስትል ዩናይትድ የፈረመው አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳቅ ነው ። ለኤርትራዊ እና ስዊድናዊው አጥቂ በሊቨርፑል ቆይታው የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ግብ ሆኖ ተመዝግቦለታል ። መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜው ተጠናቅቆ በጭማሪው ሁለተኛ ደቂቃ ላይ ደግሞ ኮዲ ጋክፖ ሁለተኛውን ግብ ከመረብ አሳርፏል ። የኅዳር 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ



ሊቨርፑል ዋንጫ ባነሳበት ባለፈው የጨዋታ ዘመን በርካታ ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ብቃቱን ያሳየው ግብጻዊው አጥቂ ሞሐመድ ሣላኅ ዘንድሮ የበርካታ የስፖርት ተንታኞች ማፌዢያ ሁኗል ። ባሳለፍነው የውድድር ዘመን 29 ግቦችን አስቆጥሮ 18 ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማመቻቸት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን አስመስክሮ ነበር ። ሊቨርፑል ባለፈው ግጥሚያ በአንፊልድ ሜዳው ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በኖቲንግሐም ፎረስት እንዲያ 3 ለ0 ሲንኮታኮት ግብጻዊው የፈየደው ነገር አልነበረም ።



በተለይ ከዚያ ውጤት በኋላ ደግሞ፦ ታዋቂ የእግር ኳስ ተንታኞች አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ያለ ሞሐመድ ሳላኅ ቡድናቸውን ማሰለፍ እንደሚገባቸው ሲወተውቱ ነበር ። አሰልጣኙ ትናንት ያን ምክር የተቀበሉ ይመስላል ። ያለ ግብጻዊው አጥቂ ድል ተቀዳጅተዋል ። ምናልባትም ለ33 ዓመቱ አጥቂ ሞሐመድ ሣላኅ የትናንቱ የአሠልጣኙ ውሳኔ አንዳች የማስጠንቀቂያ ደወል ሳይሆን አይቀርም ። ሞሐመድ ሣላኅ በሊቨርፑል የረዥም ዘመንቆ ቆይታው ተቀያሪ ወንበር ላይ ካሳለፈ ከ18 ወራት በላይ ተቆጥሯል ። ያጋጣሚ ነገር ሁኖሞ ሞሐመድ ሣላኅ ተቀያሪ ወንበር ላይ ያሳለፈው በትናንቱ የዌስትሐም ዩናይትድ ስታዲየም ነበር ። ሁኔታው በወቅቁ ከነበሩት የሊቨርፑል አሰልጣኝ ዬርገን ክሎፕ ጋር አነስ ያለች መቃቃር ፈጥሮም ነበር ። አሰልጣኙ በወቅቱ ለ11 ደቂቃ ብቻ አሰ።ልፈውት ቢያበሳጩትም በቀጣዩ ግጥሚያ ግን 90 ደቂቃ ሙሉ ተሰልፎ ዳግም ብቃቱን ዐሳይቶ ነበር ። በወቅቱ ቶትንሀም ሆትስፐር ላይ ግብ ከማስቆጠሩም በላይ አንድ ግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ተጠራጣሪዎቹን በአጠቃላይ ፀጥ አሰኝቶ ነበር ።



ምናልባት አሰልጣኝ አርኔ ስሎትም ያን ይሆን የሚፈልጉት? ከነገ በስትያ በረቡዕ የሠንደርላንድ ጨዋታ የሞሐመድ ሣላኅ የወደፊት እጣ ዳግም የሚወሰንበት መሆኑ አይቀርም ። ወይ እንደ ዬርገን ክሎፕ ዘመን እንደቆሰለ ነብር ይሆናል፤ አለያም በአርኔ ስሎት ዘመን ያረጀ አንበሳ ሁኖ ወደ ፍጻሜው ያመራ ይሆናል ። የሚሆነውን አብረን እንመለከታለን ።



በቅርቡ ለሊቨርፑል የፈረመው ፈረንሳዊው አጥቂ ሑጎ ኤኪቲኬም እንደ ሞሐመድ ሣላኅ ሁሉ የተቀያሪ ወንበር ሲያሞቅ ነበር ። ፈረንሣዊው አጥቂ ትናንት ቢያንስ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቢሆንም ተቀይሮ መሰለፍ ችሎ ነበር ። ተቀይሮ በሚገባባቸው ወቅቶች ሁሉ ግን ከአሌክሳንደር ኢሳቅ የተሻለ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ይስተዋላል ። እንዲያም ሆኑ ለሊቨርፑል አሰልጣኝ ቀዳሚ ምርጫቸው ሊሆን አልቻለም ።



ምናልባትም ረቡዕ ከሠንደርላንድ ጋር በሚኖራቸው ግጥሚያ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት እንደ ጎዲ ጋክፖ ቀዳሚ ተሰላፊ ካላደረጉት ሑጎ ኤኪቲኬ ይበልጥ ሊበሳጭ ይችል ይሆናል ። አሰልጣኙ ግን ይህን ድንቅ ተጨዋች ወደ ጎን ማለታቸው እያስተቻቸው ነው ። እንደውም ቡድናቸውን በዋናነት በሌክሳንደር ይሳቅ፤ ሑጎ ኤኪቲኬ እና ጀርመናዊው ፍሎሪያን ቪርትስ ቢመሰርቱ ያዋጣቸው ነበር ። የኅዳር 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ



በሌሎች ግጥሚያዎች፦ ሊቨርፑልን በአንፊልድ ሜዳው ጉድ አድርጎ የነበረው ኖቲንግሐም ፎረስት በገዛ ሜዳው ትናንት በብራይተን 2 ለ0 ጉድ ሁኗል ። ማንቸስተር ሲቲ ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ2 ድል አድርጓል፥ ነገ ከፉልሀም ጋር ይጋጠማል ።



የጀርመን ቡንደስሊጋ



በጀርመን ቡንደስሊጋ፥ 81ኛው ደቂቃ ላይ አንድ ተጨዋቹ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተበት ሐምቡርግ ሽቱትጋርትን ትናንት 2 ለ1 ድል አድርጓል ። አይንትራኅክት ፍራንክፉርት ከቮልፍስቡርግ ጋር ትናንት አንድ እኩል ተለያይቷል ። 28ኛው ደቂቃ ላይ የፓል ኔቤል በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበት መልካም አጋጣሚ የሆነለት ፍራይቡርግ ማይንትስን 4 ለ0 የግብ ጎተራ አድርጎ ሸኝቷል ። አንድ ተጨዋቹን 81ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጣው ሐምቡርግ በአስደናቂ ሁኔታ ሽቱትጋርትን 2 ለ1 አሸንፏል ። በነውጠኛ የአይንትራኅክት ደጋፊዎች ባለፈው ሳምንት ደጋፊዎቹ ከአውተቡስ እንዲወርዱ ተደርገው የተደበደቡበት ሽቱትጋርት በ22 ነጥብ ስድስተኛ፤ አይንትራኅት ፍራንክፉርት በ21 ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።



ሳንክት ፓውሊን ቅዳሜ ዕለት 3 ለ1 ያሸነፈው መሪው ባዬር ሙይንሽን በ34 ነጥብ ቡንደስሊጋውን እየመራ ነው ። ከተከታዩ ላይፕትሲሽ ጋር የስምንት ነጥብ ልዩነት አላቸው ። ቦሩስያ ዶርትሙንድ በ25 ነጥቡ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሰፍሯል ። ባዬር ሌቨርኩሰን እና ሆፈንሀይም በግብ ልዩነት ብቻ ተበላልጠው በ23 ነጥባቸው አራተኛ እና አምስተኛ ናቸው ። ሳንክት ፓውሊ እና ማይንትስ በ7 እና 6 ነጥብ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ ።



የባዬርን ሙይንሽን አጥቂ ሔሪ ኬን በ14 ከመረብ ያረፉ ኳሶች በኮከብ ግብ አግቢነት እየገሰገሰ ነው ። የአይንትራኅት ፍራንክፉርት አጥቂ ዮናታን ቡርካርድት እና የሽቱትጋርት የፊት መስመር ተሰላፊ ዴኒዝ ኡንዱብ በ8 እና 7 ግቦች ይከተላሉ ።



የመኪና ሽቅድምድም



በኳታር ግራንድ ፕሪ የመኪና ሽቅድምድም የማክላረን አሽከርካሪዎች «ብርቱ ስህተት» የሬድ ቡል አሽከርካሪው ማክስ ፈርሽታፐን ድል እንዲጎናጸፍ አስችሎታል ። የማክላረን አሽከርካሪዎች ጎማ ለመቀየር ፋታ የወሰዱት በውድድሩ ዘግይተው መሆኑ ዋጋ አስከፍሏቸዋል ። በዚህም የተነሳ፦ የማክላረን አሽከርካሪዎቹ ዖስካር ፒያስትሪ ሁለተኛ የቡድን አጋሩ ላንዶ ኖሪስ አራተኛ ደረጃ አግኝተዋል ። የመርሴዲስ አሽከርካሪው ካርሎስ ሣይንስ ደግሞ ከመሀከላቸው በመግባት ሦስተኛ ወጥቷል ። የጥቅምት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ



አሁን ማክስ ፈርሽታፐን ከመሪው ላንዶ ኖሪስ የሚበለጠው በ12 ነጥብ ብቻ ነው ። ዖስካር ፒያስትሪ ደግሞ በአራት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ392 ነጥብ ይከተለዋል ። በአንድ ውድድር አሸናፊ 25 ነጥብ ያገኛል ። ስለዚህም፦ በሚቀጥለው ሳምንት በአቡ ዳቢ በሚካሄደው የፍጻሜ ሽቅድምድም ሆላንዳዊው የሬድ ቡል አሽከርካሪ ለአምስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ሰፊ እድል አለው ።



በመርሴዲስ ተሽከርካሪው ለሰባት ጊዜያት የፎርሙላ አንድ የዓለም ዋንጫዎችን መሰብሰብ የቻለው ሌዊስ ሐሚልተን በፌራሪ ተሽከርካሪ እጅግ ደካማ ውጤቶችን አግኝቷል ። ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታም ዘንድሮ መጥፎ ውጤቶችን አስመዝግቧል ። በካታር ውድድር 6ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቅቋል፥ አጠቃላይ ነጥቡም 152 ነው ። የቡድን አጋሩ ሻርል ሌክሌርክ በ230 ነጥብ ከበላዩ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።



ማንተጋፍቶት ስለሺ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የኅዳር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የኅዳር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥዩም Mantegaftot Sileshi