የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ሥራ መዘጋትና መፍትሔዉ
Update: 2025-11-11
Description
የዩናይትድ ስቴትስን የፈደራል መንግሥት ሥራን ከ40 ቀናት በላይ የዘጋዉ የበጀት ዉዝግብ የመጀመሪያዉን መሰናክል አልፏል።ዉዝግቡ የተነሳዉ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ያረቀቀዉን በጀት የተቃዋሚዉ የዴሞክራቲክ ፓርቲ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች (ሴናተሮች) አንቀበልም በማለታቸዉ ነበር።ይሁንና ትናንት የዴሞክራቲኩ ፓርቲ ሴናተሮች በጀቱን በመቀበላቸዉ ረቂቁን በጀት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አፅድቆ ለሕግ መምሪያዉ ምክር ቤት መርቶታል።የሕግ መምሪያዉ ምክር ቤት በጀቱን ለማፅደቅ ድምፅ ይሰጣል።ሥለ በጀቱ ዉዝግብና ምክንያቱ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ
Comments
In Channel























