Discoverየዓለም ዜና
የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Author: DW

Subscribed: 7Played: 362
Share

Description

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
704 Episodes
Reverse
-የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ባለፈዉ ሚዚያ የመን እስር ቤት ዉስጥ የነበሩ ስደተኞችን መግደሉ የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ።በጥቃቱ የተገደሉት አብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተነግሯል።---የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ኤል ፋሻር በተባለችዉ ከተማ የሚኖሩ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉ ዓለም አቀፍ ተቃዉሞና ዉግዘት አስከትሏል።----ሩሲያ በሁለት ቀናት ልዩነት ዉስጥ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችሉ አዳዲስ ሚሳዬልና የዉሐ ዉስጥ ሰዉ አዉልባ አዉሮፕላን ሞከረች።የመሳሪያዎቹን ሙከ,ራ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተቃዉመዉታል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ተኛው የሥራ ዘመን 2ኛው መደበኛ ስብሰባው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያቀረቡትን የ2018 ዓ.ም የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። በኬንያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን በመስከሱ ቢያንስ 11 ሰዎች መሞታቸውን የሐገሪቱ የስቢል አቭዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ። የሕዝብ ዓመፅ ተገን አድርገው የሐገሪቱን ፕሬዝደንት ያስወገዱት የማዳጋስካር ወታደራዊ ሁንታ በዛሬው ዕለት በአብዛኛው ስቪሎችን ያካተተ የካቢኔ አባላት መሰየማቸውን አስታወቁ።
• በምዕራብ ዳርፉር ኤልፋሽር ቀውሱ ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት እንደገባው የመንግሥታቱ ድርጅት አስጠነቀቀ። • ሁለቱ ምዕራብ አፍሪቃዉያን አዛውንቶች ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸነፉ ። • የማሊ ፍርድ ቤት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ላይ እስራት ፈረደ። • የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ምስራቅ አፍሪቃዊቷን ሀገር ኬንያን ሊጎበኙ ነው። • በሊባኖስ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል «ከእስራኤል ሳይቃጣብኝ አይቀርም» ያለውን የሰው አልባ አውሮፕላን ማለትም ድሮን መትቶ መጣሉን አስታወቀ።
የጅቡቲ ምክር ቤት በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ላይ የተጣለው የዕድሜ ገደብ እንዲነሳ የቀረበ የውሳኔ-ሐሳብ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የአል-ፋሺር ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ። ቀይ መስቀል እና የግብጽ ባለሙያዎች በጋዛ ሠርጥ የታጋቾችን አስከሬኖች የእስራኤል ጦር ከሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች አልፈው እንዲያፈላልጉ ተፈቀደላቸው። ሩሲያ “ቢሮቬስኒክ” የተባለ አዲስ ኑክሌር ተሸካሚ ተወንጫፊ ሚሳይል የመጨረሻ ሙከራ በስኬት ማጠናቀቋን አስታወቀች። የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ባለፈው ሣምንት ከሉቭ ሙዚየም ውድ ጌጣ ጌጦች ሰርቀዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ።
አይቮሪኮስታዊያን ዛሬ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። የለንደን ፖሊሶች በወሲባዊ ትንኮሳ ተፈርዶበት በእስር ላይ እያለ በስህተት የተለቀቀ የጥገኝነት ጠያቂ እያፈላለጉ ነው። የአውሮጳ ህብረት በቻይና ወሳኝ የጥሬ ዕቃዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት መግታት ያስችለኛል ያለውን ርምጃ ሊወስድ ነው። ሩስያ ሌሊቱን በዩክሬን ባደረሰችው የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት በትንሹ አራት ሰዎች ተገደሉ ፤ 20 ሰዎች ቆሰሉ። አሜሪካ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቧን ወደ ካሪቢያን ባህር ማስጠጋቷን ተከትሎ ከደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ቮንዙዌላ ጋር ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል።
የጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዶቼቬለ አርዕስተ ዜና ዶቼቬለ ከኢትዮጵያ የሚሰሩ 9 ዘጋቢዎቹ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሥልጣን መታገዳቸውን ተቃወመ፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በዘጋቢዎቹ ላይ የተጣለውን እገዳም በአስቸኳይ እንዲያነሱ ጥሪ አቀረበ። የዩናይትድ ስቴትስ፣ የሳዑዲ አረብያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና የግብጽ ተወካዮች ከሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ጋር ሰብዓዊ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ግፊት ለማድረግ ዛሬ ዋሽንግተን ውስጥ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቢያንስ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ከምሥራቅ ኮንጎው የማዕድን ማውጫ ዘርፏል ተብሎ መከሰሱን አስተባበለ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የዶቼ ቬለ ዘጋቢዎችን ለጊዜው ማገዱን በዛሬው ዕለት በደብዳቤ አስታወቀ። ከሁለት ዓመት በላይ በዘለቀው የሱዳን ጦርነት ሕዝቡ አሳሳቢ የሰብአዊ ቀውስ እየተጋፈጠ እንደሚገኝ የተመ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አመለከተ። በመላው ዓለም ከሚካሄዱት ግጭቶች 40 በመቶው አፍሪቃ ውስጥ እንደሆነ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ። የአውሮጳ ሕብረት በዛሬው ዕለት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጣለ።
-የጀርመን መራሔ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ ሥደተኞችን የሚያጥላላ መልዕክት ማስተላለፋቸዉ የቀሰቀሰዉ ቁጣና ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ።የሜርስን መግለጫ፣ ፖለቲከኞች፣ የመብት ተሟጋቾችና የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ነቅፈዉታል።--የሩሲያ ጦር ኃይል የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ ጀመረ።ልምምዱ የኑኬሌር አረር መሸከም የሚችሉ ሚሳዬሎችን፣ መርከቦችንና አዉሮፕላኖችን ያካተተ ነዉ።---የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ እስራኤል በዩናይትድ ስቴትስ ቁጥጥር ሥር የምትገኝ ሐገር አይደለችም አሉ።ኔታንያሁ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንትን ከማነጋገራቸዉ በፊት ዛሬ እንዳሉት እስራኤል የራስዋን ፀጥታ በሚመለከት የምትወስነዉ ራስዋ ናት።
አ.አ፥ በባቡር አደጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ 14 ሰዎች መሞታቸው ተገለጠ፤ ገዋኔ፥ ነዋሪዎች በተቃውሞ የኢትዮጵያ ጅቡቲን አውራ ጎዳና መንገድን ዘግተው ነበር ተባለ፤ ፓሪስ፥ የፈረንሣይ የቀድሞ ፕሬዚደንት ታሰሩ፤ ዋሽንግተን፥ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቻቸው ወደ ጋዛ ጦር ለመላክ ዝግጁ ናቸው አሉ፤ ጋዛ፥ ነዋሪዎች የተኩስ አቁሙ እንዳይጣስ ሥጋት ገብቷቸዋል ።
• የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈጸመ። • እስራኤል ትናንት እሁድ ከሐማስ ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋ ነው ካለችው ብርቱ የአየር ጥቃት በኋላ የጋዛ የተኩስ አቁም ተግባራዊነቱ እንደሚቀጥል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ ። የአውሮጳ ህብረት በበኩሉ የጋዛ የተኩስ አቁም ገቢራዊነት እስኪረጋገጥ በእስራኤል ለመጣል ያሰበውን ማዕቀብ በይደር አቆያለሁ ብሏል። • የጣልያን የባሕር ድንበር ጠባቂዎች ላምፔዱሳ ደሴት አቅራቢያ 91 ሰዎች ከመስጠም መታደጋቸውን አስታወቁ ።
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታውቀች። ኢራን ለእስራኤል ይሰልል ነበር ብላ የወነጀለችው አንድ ግለሰብ በዛሬው ዕለት በስቅላት መቅጣቷን ተሰማ። ዩክሬይን ሌሊት ለዛሬ አጥቢያ በሩስያ የሳማራ ግዛት ላይ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ማውደሟን አስታወቀች። በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በዋሽንግተን ዲሲና ሌሎች ከተሞች አደባባይ ወጥተው የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን የሚቃወም ሰልፋ አድርገዋል።
በኪሱሙ የራይላ ኦዲንጋ መታሰቢያ ዝግጅት ላይ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የኬንያ ቀይ መስቀል ባለሥልጣናት ተናገሩ። የፈረንሳዩ ቢኤንፒ ፓሪስባስ ዩናይትድ ስቴትስ ሱዳን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በመተላለፍ በሰጠው የባንክ አገልግሎት የኦማር አል-በሽር መንግሥት የዘር ማጥፋት እንዲፈጽም ረድቷል በሚል በአሜሪካ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለ። በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ68,000 በላይ መድረሱን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ አስታወቀ። ኢራን ከአስር ዓመታት በፊት በኑክሌር መርሐ-ግብሯ ላይ ከልዕለ-ኃያላኑ የተፈራረመችው ሥምምነት በማብቃቱ በውሉ በተካተቱ ገደቦች እንደማትገዛ አስታወቀች።
-ትግራይ ዉስጥ ለሁለት ዓመት በተደረገዉ ጦርነት ከ152 ሺሕ በላይ የክልሉ ሴቶች መደፈራቸዉን «የትግራይ ጄኖ ሳይድ» የተባለዉ ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በ166 ገፅ በሰነደዉ ጥናቱ በትግራይ ሴቶች ላይ ከተፈፀመዉ አጠቃላይ ፆታዊ ጥቃት 90 በመቶዉን ያደረሱት የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦር ኃይላት ባልደረቦች ናቸዉ ይላል።----ባለፈዉ ሮብ የሞቱት የኬንያ የረጅም ጊዜ ዕዉቅ ፖለቲከኛ የራይላ ኦዲንጋ አስከሬን ዛሬ በይፋ ተሸኘ።---የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያዉ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ጦርነት ሥለሚቆምበት ብልሐት በቅርቡ ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ለመነጋገር ተስማሙ።
የጥቅምት 6 ቀን 2018 ቀን አርዕስተ ዜና በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባሰራጨው ዘገባ አስታውቋል። የአፍሪቃ ሕብረት ማዳጋስካር ዉስጥ ተደረገ ያለዉን መፈንቅለ መንግሥት አወገዘ።ሕብረቱ ትናንት የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መያዙን ተቃዉሟል። በአሁኑጊዜ በዓለማችን ቁጥሩ 14 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በከባድ ረሀብ እየተሰቃዩ ነው ሲል የዓለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ።
በደቡብ ኢትዮጵያ 11 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት «የሰላም ጥምረት» የፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ድብደባና እሥር እየተፈጸመ ነው አለ። የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ አባላቱ የተያዙት በፓርቲ አባልነታቸው ሳይሆን በወንጀል በመጠርጠራቸው እንደሆነ ይገልጻል። የሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም በዛሬው ዕለት በተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተፈጸመባት። አንጋፋው የኬንያ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ራይላ ኦዲንጋ አረፉ። ጀርመን ዮሮ ተዋጊ ጀቶችን በፖላንድ ወታደራዊ የአየር ጦር ሰፈር ልታሰፍር ነው።
-የትግራይ መከላከያ ኃይል የሚባለዉ ወታደራዊ ሥብስብ አባላት የደሞዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲከበሩላቸዉ በመጠየቅ የጀመሩት ተቃዉሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ትናንት የመቀሌን ዛሬ ደግሞ ከመቀሌ-አድግራት መንገድን ዘግተዉ ዉለዋል።---የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መቆጣጠሩን አስታወቀ።ጦሩ ሥልጣን መያዙን ያስታወቀዉ የተደበቁት ፕሬዝደንት የማዳጋስካርን ፓርላማ መበተናቸዉን ካስታወቁ ከሰዓታት በኋላ ነዉ።---በእስራኤል ጦር ድብደባና በምግብ እጦት ለረሐብ ለተጋለጠ,ዉ የጋዛ ሕዝብ ሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ ሁሉም መተላለፊያዎች እንዲከፈቱ ለጋሽ ድርጅቶች ጠየቁ
በትራፊክ አደጋ የ13 ሠዎች ህይወት አለፈ፡፡የማዳጋስካር ፕረዚደንት ከሐገር ወጡ። የማዳጋስካር ፕረዚደንት ከሐገር ወጡ። የትራምፕ የእስራኤል ጉብኝት፤ 1,400 ለሳይበር ጥቃት ሲውሉ የነበሩ ድረ ገጻች መዘጋታቸውን ፤ሩስያ የኔቶ አባል ሐገራት ልታጠቃ ትችላለች መባሉን
• ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ ። የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ «ስልጣኑን በኃይል ለመቆጣጠር ሙከራ » እየተደረገብኝ ነው አሉ።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሃማስ እጅ ታግተው የሚገኙ 20 ታጋቾችን ለመቀበል መዘጋጀቷን አስታወቀች።ጀርመን ወጣት ሶሪያዉያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ዝግጅት ማድረግ መጀመሯን አስታወቀች ።• ፍልስጥኤማዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሳሄር አልግሆራ የባዩ የጦርነት ዘጋቢ ሽልማት አሸነፈ።
የሰዎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየተጣሰ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አመለከተ፡፡ እስራኤል ዛሬ በደቡብ ሊባኖስ በፈጸመችው «መጠነ ሰፊ» የተባለለት የአየር ጥቃት 1 ሰው ሲገደል 7 መቁሰላቸውን የሐገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ጓቲማላ ከዩናይትድ ስቴትስ የተባረሩ የመጀመሪያው ዙር ስደተኞች ተቀበለች። ስደተኞቹ የራሷ እና የሁንድራስ መሆናቸውን ታውቋል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ድርጊቱን አውግዘዋል።
ሶዶ፥ ከኦሮሚያ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ውስጥ ጥቃት ፈጽመው ሰዎች ገደሉ፤ አ.አ፥ የዓለም ምግብ ድርጅት ኢትዮጳያ ለተጠለሉ ስደተኞች የሚሰጠውን ርዳታ ሊያቆም ጫፍ መድረሱን ገለጠ፤ ጋዛ፥ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ተሸለላሚ ሆነ፤ ዖስሎ፥የቬኔዙኤላ ተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የሰላም ኖቤል አሸነፉ፤ ዋሽንግተን፥ ዋሕይትሐዋስ ትራምፕ ከኖቤል ሽልማት ውጪ መደረጋቸውን «ፖለቲካን ከሰላም ያስቀደመ» አለ፤ ሞስኮ፥ትራምፕ ለሰላም ብዙ መልፋታቸውን ፑቲን ተናገሩ፤ ጋዛ፥ የእሥራኤል ጦር ከተወሰኑ የጋዛ አካባቢዎች መውጣት ጀመረ
loading
Comments