Discover
ዜና መጽሔት
ዜና መጽሔት
Author: DW
Subscribed: 4Played: 428Subscribe
Share
© 2025 DW
Description
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
596 Episodes
Reverse
የዜና መፅሔታችን መንግሥት እና በህወሓት መካከል ከምርጫ በፊት ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀመር የቀረበው ጥሪ፤ ለመጪው ሀገራዊ ምርጫ አስቻይ ኹኔታዎች እንዲኖሩ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ኦነግ መጠየቁ፤ እንዲሁም ለትራምፕ ዛቻ የናይጀሪያ ምላሽ የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት
ከዕለተ ሰኞ ሳምንታዊ መሰናዶዎች ቀዳሚው ማኅደረ ዜና የሱዳንን ቀውስ ይቃኛል።
ዜና መጽሔት ዛሬ ፤
ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በየመን ስደተኞች የተገደሉበት የአሜሪካ ጥቃት “እንደ የጦር ወንጀል” እንዲመረመር መጠየቁ
የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የአምስ ት ቀናት የግብፅ ጉብኝት ፤ እና አንድምታዉ እንዲሁም
አፍሪካውያን ተማሪዎች ለምን የሩሲያን ዩንቨርስቲዎች ይመርጣሉ? የተሰኙ ርዕሶችን ያስቃኘናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተገኝተው በሰጡት ገለጻ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስተያየት ጠይቀናል።
የብሪታንያ መንግሥት በሴቶች ላይ የወሲብ ጥቃትና ትንኮሳ በመፈጸም ተከሶ በአንድ የብሪታንያ ፍርድ ቤት እስርና ወደ ሀገሩ መባረር የተበየነበትን ሀዱሽ ገብረሥላሴ ቅባቱን ወደ ኢትዮጵያ ማባረሩን ዛሬ አስታውቋል። ጀርመን ውስጥ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት ጀርመን ውስጥ በርካታ ሴቶች ከቤት ውጪ ደኅንነት እንደማይሰማቸው ማመልከቱን መነሻ ያደረገ ሌላ ዘገባ በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ተካተዋል።
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከሐገሪቱ የምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን መልስና ማብራቂያ የሚዳስሰዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ የምሥራቅ ኢትዮጵያ የፀጥታ የጋራ ግብረ-ኃይል ከ40 በላይ የአማፂ ቡድን መሪና አባላትን ገደልኩ ማለቱን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።የሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ መሸለምና የሱዳን ጦርነትንም የሚመለከቱ ዘገቦች አሉትም።
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የድርድርን ቀጠሮን አዉሮጳና አሜሪካ በሩሲያ ላይ ከጣሉት ተጨማሪ ማዕቀብ ጋር ያለዉን ተቃርኖ የሚቃኘዉን ቃለ መጠይቅ ያስቀድማል።የፓሪስ-ፈረንሳዩ እዉቅ ቤተ-መዘክር መሰረቅ ያስከተለዉ ሥጋትና ክርክርን የሚቃኝ ቃለ-መጠይቅም አለን።
የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የጦር አዛዦችና የአፋር ክልል ባለሥልጣናት ኤርትራ ድንበር አጠገብ የምትገኘዉን ሥልታዊቷን የቡሬ ከተማን መጎብኘታቸው
ሰሞኑን በትግራይ ክልል የተለያዩ ቦታዎች የትግራይ ኃይሎች ለቀናት መንገድ በመዝጋት ያሰሙት ተቃውሞ
የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የቃላት ውዝግብ ያሳደረው ስጋት ፤ የደወሌው የባቡር አደጋ ያስከተለው ጉዳት፤ የመተከል ዞን የመንገድ ብልሽት እንዲሁም ወህኒ የወረዱትን የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኒኮላስ ሳርኮዚን ጉዳይ የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የምሽቱ የዜና መጽሔት
በዜና መፅሄታችን፦ በኦሮሚያ የተባባሰው የንጹናን ሰዎች ግድያ፤ በዓፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገዋኔ አካባቢ መንገድ በመዝጋት የተሰማው የተቃውሞ ድምፅ፤ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውሃ አቸቃቀም እንዲሁም የአሚሪካው ምክትል ፕሬዚደንት የእስራኤል ጉብኝትና የተኩስ አቁም ስምምነቱ ስጋትና ተስፋs የተሰኙ ሪፖርቶች ይቀርባሉ።
በኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ኃይሎች መካከል የተባባሰው ውጊያ፤ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን በጎርፍ ከተፈናቀሉት ሰባት ሺህ የሚደርሱት ወደቀያቸው መመለሳቸው፤ እንዲሁም የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት የአዲስ አበባ ጉብኝት መጠናቀቁን የሚያስቃኙ ዘገባዎች የዓለም ዜናን በሚከተለው የዜና መጽሔት ተካተዋል።
በዜና መጽሔት
-IOM የኢትዮጵያን የ5 ዓመታት የሥራ ፍኖተ ካርታ ይፋ ማድረጉ፤
-የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ ማስተላለፋቸው፤
-የፓርቲዎች የመንቀሳቀሻ ሜዳ ጠበበ ወይስ ሠፋ? እንዲሁም
-የኦሮሚያ እና ሶማሊ አዋሳኞች ግጭት ላይ ያተኮሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት
የትግራይ ኃይሎች የተባለዉ ወታደራዊ ስብስብ ባልደረቦች የጀመሩትን ተቃዉሞና መንገድ የመዝጋት እርምጃ፣
በኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የደረሰ ጥቃት
ተፅዕኖ ፈጣሪ የተባሉ ኢትዮጵያዉያን መሸለማቸዉ
በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ፣-በሕዳሴ ግድብ ምክንያት ውዝግብ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያ እና ግብጽ ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላም መካሰሳቸው መቀጠሉ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ብሪታኒያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ጋር ያካሄደው ውይይት ፣ የደሴ ከተማን ህዝብ ያስቆጣው የወጣቷ ተማሪ ግድያ ፣ የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ፣ ኃይል መቋረጥ የፈተናቸው የኮሬ ዞን ነዋሪዎች በተሰኙ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ
በሰሜን ሸዋ ዞን፤ ወራጃርሶ ወረዳ ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፤ በአማራ ክልል የልጅነት ልምሻ መከሰትን ተከትሎ የተጀመረዉ ክትባት፤ እንዲሁም ጋና ከዩናይትድ ስቴትስ የሚባረሩ ተገን ጠያቂዎችን ለመቀበል መስማማትዋ እና ያስነሳዉ ተቃዉሞ የዛሬዉ ዜና መጽሔት የሚዳስሳቸዉ ዘገቦቻችን ናቸው።
የዜና መጽሔት ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፥
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመድ ለየፃፈው ደብዳቤ ሕወሓት ምላሽ ሰጠ፤ ለአሽከርካሪዎች ፈተና እየሆነ መጥቷል የተባለው የጊቤ መንገድ የፀጥታ ይዞታ፤ የኢትዮጵያ ምንዛሪ በአፍሪካ ደካማ ከሆኑት 21 ገንዘቦች መካከል አንዱ ነው ተባለ፤ እንዲሁም “የአፍሪካ ቲንከታንክ” ጉባኤ የሚሉት ናቸው ።
ኤርትራና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጦርነት ለመክፈት በጋራ እየሰሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሰ። መስሪያ ቤቱ ሁለቱ ወገኖች የአማራ ፋኖን እያገዙም ነው በማለት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ በላከው ይፋ ደብዳቤ አስታውቋል። የደብዳቤው ይዘትና ስለክሱ የተሰጡ አስተያየቶች በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ተሰናድተዋል።






















