ትኩረት በአፍሪካ የጥቅምት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና
Update: 2025-10-18
Description
አምስት ጊዜ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረው ባይሳካላቸውም ራይላ ኦዲንጋ የኬንያን ዴሞክራሲ እና ምርጫ የይስሙላ እንዳሆን ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል። በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኦዲንጋ በተቃዋሚነታቸው ታስረዋል፤ ተገርፈዋል፤ ተሰደዋል። ግን እስከ መጨረሻው አላፈገፈጉም። በማዳጋስካር ጦር ሠራዊት ውስጥ ካፕሳት ተብሎ የሚጠራው ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ሚካኤል ራንጄሬሪና ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። የ51 ዓመቱ የጦር መኮንን ሥልጣን የጨበጡት ለሦስት ሣምንታት ከተካሔደ የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጄሊና ከሥልጣን ተባረው ነው።
Comments
In Channel




