የፀሀይ ድምቀት የእውነት ሀይል እና የውበት ስበት ልንማርባቸው የሚገቡ ድንቅ ነገሮች ናቸው::
Update: 2020-04-03
Description
ፀሀይ.
ፀሀይ አስፈሪውን ጨለማ ፈርታ ሳትወጣ አትቀርም
ጨልማውን እየገፈፈች እየገፈፈች ስፍራውን ትሞላዋለች እንጂ
ዛሬ ጨለማ ነው ብላ ጎጆዋ ውስጥ አትደበቅም
ምድር እንኳን ጀርባዋን ብትሰጣት ፀሀይ በራሷ እና በሌሎች አለማት ፊት እየበራች ነው
ፀሀይ የዝናብ ናዳ አያጨልማትም
በኛ ሰማይ ሲዳምን ፀሀይ በራሷ አለም መውጣቷ አይቀርም
ፀሀይ ምድርን ታበራታለች እንጂ ምድር እንዳዘዘቻት አትሆንም
ለራሷ ደምቃ ውበቷንና ብርሃኗን ታንበሸብሸናለች እንጂ እርሷ አይበርዳትም
ፀሀይ ሁልጊዜ ከደመናው በላይ ናት
በተራሮች ከፍታ አትሰወርም
ምድር ብትዳምን ፀሀይ ጨልማ ጠፍታ አይደለም
የምድር ፊት በዳመና ተሸፍኖ እንጂ
ፀሀይ ስትወጣ የፍጥረት ፊት ይደምቃል
ውበት አብቦ ይፈካል በድፍረት ይወገዳል
ሃዘን በደስታ ይተካል
ፀሀይ ስትወጣ አይን ይከፈታል
ተስፋ ይታደሳል::
ፀሀይ አስፈሪውን ጨለማ ፈርታ ሳትወጣ አትቀርም
ጨልማውን እየገፈፈች እየገፈፈች ስፍራውን ትሞላዋለች እንጂ
ዛሬ ጨለማ ነው ብላ ጎጆዋ ውስጥ አትደበቅም
ምድር እንኳን ጀርባዋን ብትሰጣት ፀሀይ በራሷ እና በሌሎች አለማት ፊት እየበራች ነው
ፀሀይ የዝናብ ናዳ አያጨልማትም
በኛ ሰማይ ሲዳምን ፀሀይ በራሷ አለም መውጣቷ አይቀርም
ፀሀይ ምድርን ታበራታለች እንጂ ምድር እንዳዘዘቻት አትሆንም
ለራሷ ደምቃ ውበቷንና ብርሃኗን ታንበሸብሸናለች እንጂ እርሷ አይበርዳትም
ፀሀይ ሁልጊዜ ከደመናው በላይ ናት
በተራሮች ከፍታ አትሰወርም
ምድር ብትዳምን ፀሀይ ጨልማ ጠፍታ አይደለም
የምድር ፊት በዳመና ተሸፍኖ እንጂ
ፀሀይ ስትወጣ የፍጥረት ፊት ይደምቃል
ውበት አብቦ ይፈካል በድፍረት ይወገዳል
ሃዘን በደስታ ይተካል
ፀሀይ ስትወጣ አይን ይከፈታል
ተስፋ ይታደሳል::
Comments
In Channel