Discoverባህልና ወጣቶች | Deutsche Welle
ባህልና ወጣቶች  | Deutsche Welle
Claim Ownership

ባህልና ወጣቶች | Deutsche Welle

Author: DW

Subscribed: 12Played: 1,396
Share

Description

ከወጣቶች ዓለም
2753 Episodes
Reverse
ዶክተር ያብባል የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ብቻ አይደሉም፤ካኅንም ጭምር እንጂ። በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ደብረ ታቦር ከተማ ተወልደው ያደጉትና የ1ኛና የ2ተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን የተከታተሉት ያብባል 2ተኛ ደረጃን እስኪጨርሱ ድረስ ትኩረታቸው በቀለም ትምሕርት ላይ ብቻ ነበር። ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ ግን የቤተ ክኅነት ትምሕርትም ቀልባቸውን ሳበ።
ትግራይ ለጋዜጠኞች አደገኛ መሆኗ ቀጥሏል ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ አስታውቋል።CPJ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ አለ ያለውን የፕሬስ ነጻነት ገደብም ሲያወግዝ ቆይቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሌላ ግጭት በመግባት ተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
በተፈረደባቸው የ5 ዓመት የእስር ቆይታ በሙሉ ሳርኮዚ ከታሰሩበት ክፍል አጠገብ ሆነው በቋሚነት ሁለት ፖሊሶች እንደሚጠብቋቸው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረን ኑኔስ ዛሬ ተናግረዋል። የሳርኮዚ የእስር ጊዜ እንዲያጥር ይግባኝ ያሉት ጠበቆቻቸው በአንድ ወር ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወምበራ ወረዳ፣ ቡሌን እና ድባጢ የተባሉ ወረዳዎች እና ሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ በመበላሸቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁለት ሳምንት ያህል መስተጓጉሉ ተገለጸ።
ከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።በምትኩ በሳተላይት እና የዘመኑ ቴክኖሎጂ በወለዳቸው እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች ስርጭቱን ይቀጥላል።ያም ሆኖ በይነመረብ ይጎዳል ተብሏል።
ባሳለፍነው ሰኞ ሌሊት በድሬደዋ ደወሌ የባቡር መጓጓዣ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 15 መሆኑን የድሬደዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት አስታወቀ።
«ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ እሁድ ጥቅምት 09 ቀን 2018 ዓ.ም. ማምሻውን አገር ሰላም ብለው እንደወትሮው ወደ ቤታቸው በገቡ ንጹሃን የኖኖ ወረዳ ሃሎዲንቂ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ነው» የአካባቢው ነዋሪ አስተያየት
እንደወረዳው ነዋሪዎች ገለፃ የትናንቱ ተቃውሞ ከሰዓታት በኋላ የተቋረጠው መንገደኞች ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለመቀነስ እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ መግባባት ቢሆንም ጥያቄው ካልተፈታ ከቀናት በኋላ በድጋሚ አደባባይ እንወጣለን ይላሉ፡፡
ሲምፖዝየሙ ሲጠናቀቅ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ተመራማሪዎችን እና ዲጂታል አበልጻጊወችን በማገናኘት በዳታ የሚመሩ መሳሪያዎችን ተቀባይነት ከማፋጠኑም በላይ በውኃ አስተዳደር ውስጥ ለዲጂታል ለውጥ የሚረዳ አህጉራዊ ፍኖተ ካርታ ይቀርጻል ተብሎ ይጠበቃል ።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከመከላከያና ደህንነት ባለስልጣናት ጋር ከመከሩ በኋላ ሐማስ ትንኮሳውን የማያቆም ከሆነ ጦሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ይህን ተከትሎ በካባቢው ለአጭር ቆይታም ቢሆን ሰፍኖ የነበረው ሰላም እንዳይደፈረስ ስጋትን አጭሯል።
እያደር የተራቆተና የተበላሸው የአካባቢ ተፈጥሮ ግለሰቦች በሚያደርጉት የየግል አስተዋጽኦ ሊለወጥ ለመቻሉ ማሳያ ይሆናል የኮምቦልቻ ከተማው የአትክልት ስፍራ። በዚህ ስፍራ በየዓመቱ የተለያዩ ችግኞችን እያፈሉ ለኅብረተሰቡ ማቅረብም ሌላው የማይታጎል ሥራ ከሆነ አስር ዓመት አለፈው።
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ንጉሴ ሞግስ በዞኑ በተለያዩ ምክንያቶች የትራፊክ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት 3 ወራት 33 አደጋዎች መድረሳቸውን የየገለፁት አዛዡ፣ በ82 ሠዎች ላይ ጉዳት ደርሶ 24ቱ ህይወታቸው ሲያልፍ በ34ቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡
“ሰው ሁኑ፤ከሃይማኖትም ከዘርም ሰው መሆን ይቀድማል” “የሰው ልጅ እኩል ነው አባቱም አደም ነው እናቱም ሀዋ ነች የተፍጠሩትም ከአፈር ነው“ እነዚህ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከሚታወሱባቸው በርካታ የሰላም መልዕክቶቻቸው ጥቂቶቹ ናቸው።
የገዳ-ሥርዓት ለኦሮሞ ነጸናት ፓርቲ ገዳ ቢሊሱማ ፕሬዝዳንት አቶ ሮቤሌ ታደሰ አገር አቀፍ ምርጫ ስኖር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚጠበቅ ነበር ግን አሁን ያን የሚመስል ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም ሲሉ መንግስት ምርጫ ለማድረግ የሚወስንም ከሆነ በአገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን ግጭትና አስቻይ ሆኑታ በማገናዘብ መሆኑ እንደሚገባው ጠይቀዋል፡፡
አምና ይኼኔ የአዲስ አበባና የሐ,ርጌሳዎች ወዳጅነት ጠንክሮ፣ የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች ጠብ ከርሮ፣ የሞቃዲሾ-ካይሮ-አሥመራ ወደጅነት ንሮ፣ የቱርክ ሸምግልና ሒደት ዉጤት በጉጉት ይጠበቅ ነበር።ዓመት አጭር ነዉ ረጅም።አጠረም የዓመቱ ዑደት ለአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ «ያቀርቶ ሌላ---መጥቶ» ያሰኝ ይዟል
አጀማመሩ ላይ ዘንድሮም የሚደርስበት የለም የተባለለት ሊቨርፑል ለቡድኑ ደጋፊዎች እጅግ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን አስተናግዷል ። አርሰናል፤ ማንቸስተር ሲቲ፤ ቸልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በድል ግስጋሴ ላይ ይገኛሉ ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደተለመደው በተለያዩ ውድድሮች ድል ቀንቷቸዋል ።
ሰሞኑን የተቃውሞ ሰልፎቹ ሲደረጉ ያልዘገቡት የትግራይ ክልል መንግስት ሚድያዎች እና የህወሓት ልሳናት ሰልፉን የሚኮንን እና የሠራዊት አባላቱ ይቅርታ ስለመጠየቃቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች ትናንት ዘግበዋል። ከትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች መካከል ጀነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ የተቃውሞ ሰልፎቹን እና መንገድ የመዝጋት እርምጃዎችን አውግዘዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ከምርጫ ውድድር ባሻገር ፤ በሀገሪቱ ግጭቶች ቆመው ዘላቂ ሰላም ሊያሰፍን የሚያስችል ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን እና የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ሲነገር ቆይቷል።
እንደ በርካታ አገራት ፍላጎት ከሆነ ሐማስ ትጥቅ መፍታት ይኖርበታል ። ሆኖም እስካሁን ድረስ ግን በጋዛ ሠርጥ የሚገኘው ሐማስ ከተቀናቃኝ ጎሳዎች እና ቡድኖች ጋር ደም አፋሳሽ የኃይል ሽኩቻ ውስጥ ነው ።
በማዳጋስካር ጦር ሠራዊት ውስጥ ካፕሳት ተብሎ የሚጠራው ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ሚካኤል ራንጄሬሪና ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። የ51 ዓመቱ የጦር መኮንን ሥልጣን የጨበጡት ለሦስት ሣምንታት ከተካሔደ የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጄሊና ከሥልጣን ተባረው ነው።
loading
Comments