Discoverዜና መጽሔት
ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Author: DW

Subscribed: 4Played: 428
Share

Description

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
576 Episodes
Reverse
በሰሜን ሸዋ ዞን፤ ወራጃርሶ ወረዳ ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፤ በአማራ ክልል የልጅነት ልምሻ መከሰትን ተከትሎ የተጀመረዉ ክትባት፤ እንዲሁም ጋና ከዩናይትድ ስቴትስ የሚባረሩ ተገን ጠያቂዎችን ለመቀበል መስማማትዋ እና ያስነሳዉ ተቃዉሞ የዛሬዉ ዜና መጽሔት የሚዳስሳቸዉ ዘገቦቻችን ናቸው።
የዜና መጽሔት ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፥ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመድ ለየፃፈው ደብዳቤ ሕወሓት ምላሽ ሰጠ፤ ለአሽከርካሪዎች ፈተና እየሆነ መጥቷል የተባለው የጊቤ መንገድ የፀጥታ ይዞታ፤ የኢትዮጵያ ምንዛሪ በአፍሪካ ደካማ ከሆኑት 21 ገንዘቦች መካከል አንዱ ነው ተባለ፤ እንዲሁም “የአፍሪካ ቲንከታንክ” ጉባኤ የሚሉት ናቸው ።
ኤርትራና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጦርነት ለመክፈት በጋራ እየሰሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሰ። መስሪያ ቤቱ ሁለቱ ወገኖች የአማራ ፋኖን እያገዙም ነው በማለት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ በላከው ይፋ ደብዳቤ አስታውቋል። የደብዳቤው ይዘትና ስለክሱ የተሰጡ አስተያየቶች በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ተሰናድተዋል።
የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት የመንግስትን አመታዊ እቅድ በሚቀጥለው ሰኞ ያቀርባሉ። የህዝብ ተወካዮች እና የሚንስትሮች ምክር ቤቶችም የሚከፈቱት በዚያው ቀን ነው። ለመሆኑ ሰዎች ከመንግስት ዓመታዊ ዕቅድ ምን ይጠብቃሉ?መንግሥት በዓመቱ የትኞቹን ተግባራት ቢከውን ይበጃል?
የዜና መጽሔታችን በዛሬ ጥንቅሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የከተማ ሥራችንን "ሊያጣጥሉ የሚሞክሩ" ያንሏቸውን "ሀገራት እና ቡድኖች" መንቀፋቸው፤ ከትግራይ ሐይሎች በመነጠል በዓፋር ክልል እየተደራጁ ያሉ ታጣቂዎች ትግራይ ላይ ለመፈፀም ያቀዱት ጥቃት በክልሉ ነዋሪዎች ጥረት ከሽፏል መባሉና የቡድኑ አዛዥ ምላሽ ፤ በኢትዮጵያ የንግድ ባንኮች የብድር ገደብ አለመነሳትና አንድምታው፤ በኢትዮጵያ በታላቁ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ ዘጠኝ ሀይቆች ሥነ ህይወታዊ ህልውና ፤ በኦሮሚያ ክልል የቱሪዝም ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የገበያ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ መጠየቁን የተመለከቱ ዘገባዎች ተጠናቅረዋል።
የዜና መጽሔታችን በዛሬ ጥንቅሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይመስሪያቤት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አመቺነት ኹኔታ "ፈታኝ ነው" ማለቱ ፤ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ለሄደው የጥላቻ ንግግር መፍትሔ መጠየቁ ፣ የሱዳን የናይል ወንዝ የጎርፍ ሥጋት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ፣እና በአሜሪካ የሚደገፈው የጋዛ የሰላም እቅድ እና አንድምታው በቅደም ተከተል ይተነተናሉ።
በዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉትን ውይይት የተመለከተ፣ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ እንዲሁም በጃፓን ቶኪዮ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምላሽን የተመለከቱ ሶስት ዘገባዎች ይቀርባሉ።
-ግብጽና ኢትዮጵያ ለበሶማሊያ ምድር እድል አልሰጥም ሲሉ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሰሞኑን ተናግረዋል። -በፍትህ ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮችን ማስተካከል እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በክልሉ በተካሄደው የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ ተቋማት ጥምረት ጉባዔ ላይ አሳስበዋል። እነዚህና ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚሰሩ ስምንት ሲቪል ማሕበራት ስጋትና ጥሪን እንዲሁም የተመድ ጠቅላላ ጉባኤና ፕሬዝደንት ትራምፕ ንግግር የሚያስቃኙ ቅንብሮችም በዛሬው የዜና መጽሔት ተካተዋል።
ጦርነትና ለወራት የተቋረጠ ሰብአዊ ድጋፍ የተፈናቃዮች አቤቱታ፤ በትግራይ ክልል የቀጠለው የተፈናቃዮች ችግር ፤ በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ለችግር የተጋለጡ ወገኖች፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ለምን ዝቅተኛ ሆነ? እንዲሁም በቶሮንቶ ካናዳ የተካሄደውን የቢቂላ ዕውቅናና ሽልማት የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት
ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ጥንቅራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ግጭቶች ሐገሪቱ ከቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን እንዳታገኝ ማወኩን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።የህወሓት ሊቀመንበር በድጋሚ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ያሰሙት ወቀሳ፣ ሰሜን ወሎ የሠፈሩ ተፈናቃዮች የገጠማቸዉ ችግርና የመቅደላ ዩኒቨርስቲ የመካነ ሠላም ካምፓስ ዘንድሮ ማስተማር ሊጀምር ነዉ መባሉን የሚዳስሱ ዘገቦች አሉት።
በዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤ -ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየዩ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮች መፍትሄ እያገኙ ይሆን? -በሆሮ ጉዱሩ በአቤዶንጎሮ ወረዳ የታጣቂዎቸ ጥቃት -የትግራይ ትውልድ ፓርቲ -' ውድብ ወለዶ ትግራይ' የተሰኘዉ አዲሱ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ በአዲስ አበባ ጉዳት ያደረሰው ጎርፍና መንስኤዉ የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።
የዓለም ዜና ቀዳሚው ዝግጅታችን ነው። ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት ስለኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ የዓለም አቀፍ ሕግ ምን ይላል? በሚል ርዕስ የተጠናቀረውን ዘገባ ያስቀድማል ከባድ ዝናብ በዋግኽምራ በሰብል ላይ ባለደረሰው ጉዳት ላይ የሚያተኩረው ዘገባም አለን።
የዜና መጽሔት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ መቀጠሏ፤ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በደቡባዊ ትግራይ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ማለታቸው፤ በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ ሕመም እንደጠናባቸው መገለጹ፤ ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ ያስገደደው አዲስ አበባ ላይ የተከሰው የመሬት መንሸራተት እንዲሁም የአረብ ሃገራት መንግሥታት አስቸኳይ ጉባኤ ውሳኔና አንድምታውን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰላም ሥለሚሰፍንበት ሁኔታ የሚነጋገር ጉባኤ አዲስ አበባ ዉስጥ መጀመሩን አማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የመማር-ማስተማሩን ሒደት አሁንም እያወከዉ መሆንኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ አጠገብ ሊያስገነባ ሥላቀደዉ ግዙፍ አዉሮፕላን ማረፊያ የተነጋገረ ስብሰባ
loading
Comments