DiscoverDW | Amharic - Newsበኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ ኮንግረስ የተካሄደ ውይይት
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ ኮንግረስ የተካሄደ ውይይት

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ ኮንግረስ የተካሄደ ውይይት

Update: 2025-12-22
Share

Description

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ ኮንግረስ የተካሄደ ውይይት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ ያተኮረ ውይይት፣ በአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት (ኮንግረስ) ውስጥ መካሄዱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ -አሜሪካ የሲቪክ ድርጅቶች ጥምረት የጠራውን ይህንን ስብሰባ በተመለከተ፣የጥምረቱ ሊቀመንበር አቶ መስፍን መኮንን ለዶቼ ቬለ እንዳስታወቁት፣በውይይቱ ላይ በቅርቡ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በቀረበው የውሳኔ ሰነድ ላይ ከምክር ቤቱ ተጠሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።



ኢትዮጵያን በተመለከተ ለአሜሪካ ኮንግረስ የቀረበውን የውሳኔ ሰነድ ያረቀቁት፣የሪፐብሊካን ፓርቲው አባል የሆኑት፣የጆርጂያ ሃገረ ግዛት እንደራሴ በዲ ካርተር እና የደቡብ ካሮላይና ተመራጩ ጆ ዊልሰን ናቸው።



የውሳኔ ሰነድ



ይህ ሰነድ፣በዋናነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን እና ሌሎች የሃይማኖት ተቋማት አማኞች እና ሌሎች፤ ዜጎች ላይ ይደርሳል የተባለን መጠነ ሰፊ እስር በማጋለጥ፣የኢትዮጵያ መንግሥት በሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲጠየቅ የሚያደርግ ነው ተብሏል። እንደጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር ዐርብ ታኅሣሥ 19 ቀን 2025 በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ የተካሄደው ስብሰባ፣በዚሁ የውሳኔ ሰነድ ላይ ትኩረት አድርጎ መምከሩን አቶ መስፍን ተናግረዋል።



''ይሄ ውሳኔ እንግዲህ፣የኢትዮጵያ መንግሥት፣በዐማራ ክልል ጦርነት እያካሄደ ሲሆን፣በኦሮሚያ፣ዓፋር፣ትግራይ፣ኦጋዴን እና በሊሎች አካባቢዎች ውስጥ የሚቀጥል ግጭት የሕይወት መጥፋት፣ሰፊ የንብረት ውድመት፣የክልል መረጋጋት መበላሸት፣የብሔርና የሃይማኖት ግጭቶችና መባባስ እና በግጭት የተነሳ ረሃብና ሰፊ መፈናቀል መጨመር እየተፈጠረ መሆኑን ይጠቅሳል።"



የውሳኔ ሰነዱ፣ግሎባል ማግነትስኪ የተባለውን እና የሰብኣዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል በሚባሉ ባለሥልጣናት ላይ፣የጉዞና የቪዛ ክልከላ ተግባራዊ እንዲሆን ይጠይቃል።' አቶ መስፍን እንዳሉት፤በአርሲና በሌሎች አካባቢዎች፣በክርስታያኖች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያ፣ መፈናቀልና ግፍ በተመለከተ የሃይማኖት አባቶች በምክር ቤት፣ቀርበው አስረድተዋል።



የሕገ መንግሥት ማሻሻያ



ሌላው፣ውይይት የተካሄደበት አጀንዳ፣የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ ነው ይላሉ አቶ መኮንን። ''የሕገ መንግስቱ ኮንፈረንስ ነው።በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን የሚያጠናክር ወደፊት ለማቅረብ፣የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ያስፈልጋል በሚል በአስቸኳይ እንድንወያይ አድርገናል።" በቀጣይ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን በሚኖሩባቸው ግዛቶች ካሉ የሕዝብ ተመራጮች ጋር በመገናኘት፣ስለኢትዮጵያ ነባራዊ ሁሌታ የሚያስረዱበት መንገድ መመቻቸቱንም ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል።



"በየስቴቱ፣አቀነባብሮ በየኮሚቴውና ከኮንግረስና ሴኔት ተወካዮች ጋር በመደወል፣ደብዳቤ በመጻፍ፣ያንን ተከትለው፣በእዛ ላይ በየግዛቱ እያስረዱ፣የኢትዮጵያን ጉዳይ ያንን ደብዳቤ ተከታትለው ጽፈው ዘመቻ ማድረግ፡በእዛ ላይ ደግሞ ስልክ በመደወል አንዳንዴ ደግሞ ቢሯቸው እየሄዱ ከሴናተርና ከሰራተኞቻቸው መገናኘትም ያስፈልጋል።



የፖለቲካ ተንታኙ አስተያየት



በጉዳዩ ላይ አስተያየት የጠየቅናቸው፣የፖለቲካ ተንታኝ አቶ አያና ፈይሳ፣ኢትዮጵያ አሜሪካውያኑ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ፣''የተጋነነ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ያለበት ዘመቻ አካል'' አድርገው ነው የሚያዩት። "እነ በዲ ካርተርና ጆ ዊልሰንን የመሳሰሉ የአሜሪካ ተወካዮችን ይዘው ውሳኔ 937 የሚባለው፣አሁን በቅርብ ጊዜ ገብቷል፤እነሱ ደግሞ ጅምላ ግድያ የሚለውን የተጋነነውን የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ያለበትን ዘመቻ የሚያደርግ አካል አለ።መሬት ላይ በትጥቅ የሚዋጋ አለ።በተላያዩ መዋቅሮች ውስጥ በገንዘብ፣በዲፕሎማሲ፣በራሱ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያለ እና ይሄ ሰፊ ክንዶች ያሉት፣በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ተመልሰን የብሔር ማንነቶችን ህብረ ብሔራዊነትን፤ አሁን ካለንበት ሕገ መንግሥት ከሚያጎናጽፈው ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርገን አንድ ማንነት፣አንንድ ቋንቋ ላይ ያተኮረ ኢትዮጵያ መልሶ መገንባት አለባት የሚለው እሳቤ እንቅስቃሴ አካል አድርጌ ነው የማየው።"



የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት ማሻሻል የሚችሉት፣ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ማኅበረስብና መርጦ የሚያስቀምጠው አካል መሆኑን ያመለከቱት አቶ አያና፤የአሜሪካ መንግሥት ቢስማማበትም የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ህልውና ሊወስን እንደማይችል አብራርተዋል። "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ማኅበረሰብና ኢትዮጵያ ውስጥ መርጦ የሚያስቀምጠው አካል ነው የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት የሚያሻሽለው፤የፈለገውን ያህል ሁለትና አንድ የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች አይደሉም፤መላው የአሜሪካ መንግሥት ቢስማማበት የኢትዮጵያን ሕዝብና የአኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦጭን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑት፣ራሳቸው ኢትዮጵያኖች ናቸው።ያንን ዐይተው ከእዛ ጋር የተናበበ ነገር መሥራት ቢጀምሩ ያዋጣል።'' በተነሱት ጉዳዮች ላይ፣ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ አስተያየት ለማካተት ጥረት ብናደርግም ምላሽ አላገኘንም።



ታሪኩ ኃይሉ



አዜብ ታደሰ



ኂሩት መለሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ ኮንግረስ የተካሄደ ውይይት

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ ኮንግረስ የተካሄደ ውይይት

ታሪኩ ኃይሉ