DiscoverDW | Amharic - News«የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው»
«የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው»

«የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው»

Update: 2025-11-07
Share

Description

የትግራይ ሙሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር በትግራይ ያንዣበበው የጦርነት ዳመና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ። ማሕበሩ ትላንት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ «የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው» ብሏል።



«የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው»





ከጫፍ እስከጫፍ ያለው የትግራይ ህዝብ ጦርነትና የጦርነት ወሬ መስማት አይፈልግም ያለው መግለጫው «ህወሓትና አንዳን የጦር ጀነራሎች የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ትግራይን ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለማስገባት እየፎከሩና የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ነው» ብሏል። ሕዝብን የሚመራ አካል ጦርነት ለማስቀረት ይጥራል እንጂ ወደ ጦርነት የሚያመሩ ንግግሮችና ተግባራትን መፈጸም የለበትም በማለትም የክልሉን ጊዚያዊ አስተዳደርም ወቅሷል።

ጀርመን በሚገኘው የአኸን ዩኒቨርሲቲ የሚሰሩና የትግራይ አለምአቀፍ ሙሁራንና ባለሙያዎች ማሕበር (GSTS) የአመራር አባል የሆኑት ዶክተር ገብረኪዳን ገብረስላሴ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተውናል።

«ትላንት ያወጣነው አስቸኳይ ብረስ ርሊዙ አንድ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ሰላም መሆኑን ለማሳወቅ ነው። በሁለተኛ ጦርነት እንዳይመጣ እንጸልያለን፤ ሆኖም ግን እንደዛ አይነት ጥሪ የሚያደርጉ በሁሉም ወገን ካሉ ወጣቱ የዚህ ሰለባ እንዳይሆን፤ ሕዝባችንም በሰራዊት ያሉም አንዱ ሀራ መሬት የሚባል አለ፤ ሌላው ቲ ዲ ኤ ፍ ትግራይ ውስጥ ያለው በመካከላቸው ምንም ወደ ግጭት የሚወስዳቸው ነገር ስለሌለ ወደዛ እንዳይሄዱ፤ እና ወጣቱ የጦርነት ሰለባ እንዳይሆን ጥሪ ለማድረግ ነበር።»



ለጦርነት እምቢ ማለት አለበት



አሁን በአካባቢው እያንዣበበ ያለውን የጦርነት ድባብን ለማስቀረት ሕዝቡ፣ በትግራይ ሐይሎችና በዓፋር ያሉ የታጠቁ ሐይሎች እንዲሁም የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ለሰላም መቆም እንዳለባቸው የትግራይ ዓለም አቀፍ የሙሁራንና የባለሙያዎች ማሕበር በአስቸኳይ መግለጫው አሳስቧል። ዶክተር ገብረኪዳንም ይህንሉ ያጠናክራሉ፤ ሕዝቡ «እምቢ ለጦርነት» ማለት እንዳለበት በማሳሰብ።

« ያለው ልዩነት የፖለቲካ ልዩነት ነው። በፖለቲካ ውይይት እንዲፈቱት ነው የምንጠይቀው። ከዚህ በተጨማሪ ግን ህብረተሰቡ እራሱ ሕብረተሰቡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ግጭት ወደ ጦርነት እንዳይገቡ የራሱ ተፅዕኖ ማድረግ አለበት። ለጦርነት እምቢ ማለት አለበት።»

ዓለም አቀፍ የሙሁራንና የባለሙያዎች ማሕበር ያወጣው አስቸኳይ መግለጫ በአወንታዊ ጎኑ እንደሚመለከቱት የገለጹልን ደግሞ በጀርመን ሐገር በፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩት የምጣኔ ሐብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ካሳ ገብረመስቀል ናቸው። ሕዝቡ ለሰላም መቆም እንዳለበት በማሳሰብ ጭምር።

በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ የትግራይ ማሕበረሰብ አደረጃጀቶችም በህወሀትና በፌደራል መንግስት ያሉ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ እያደረጉ ነው።



ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር



እሸቴ በቀለ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

«የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው»

«የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው»

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር Yohannes G/Egziabher