DiscoverDW | Amharic - Newsየኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?

Update: 2025-11-09
Share

Description

የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ በጎርጎሮሳዊው 2025 ደካማ የአፍሪካ መገበያያ ገንዘቦች መሆናቸውን የዓለም ባንክ ሪፖርት አሳይቷል። አፍሪካስ ፐልስ በተባለው ሪፖርት መሠረት ሁለቱ መገበያያ ገንዘቦች በዓመት ውስጥ ከ10 በመቶ በላይ ዋጋቸውን አጥተዋል።



በኢትዮጵያ ቢዝነሶች በገበያ ብቃት ማነስ እና በገደቦች ምክንያት ከባንኮች ዶላር ማግኘት ሲቸገሩ የውጭ ምንዛሪ ግብይት በአቅርቦት እና በፍላጎት እንዲወሰን የሚደረገው ጥረት በትይዩ ገበያው የተመን ዕድገት እየተፈተነ እንደሚገኝ የዓለም ባንክ ሪፖርት ይጠቁማል።



የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ በሐምሌ 2016 ከተደረገ በኋላ ብር ዶላርን ከመሳሰሉ የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን እየተዳከመ ቢሔድም ሀገሪቱ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ እና ከሐዋላ የምታገኘው ገቢ ማሻሻል አሳይቷል። የሥርዓት ለውጡ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና በዓለም ባንክ ብድር እና እርዳታ የሚደጎመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ቁልፍ አላባዎች አንዱ ነው።



በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ኢትዮጵያ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘች የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ ሪፖርት አድርገዋል። ሀገሪቱ ከወጪ ንግድ ካገኘችው ገቢ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት በዓለም ገበያ የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ የታየባቸው ወርቅ እና ቡና ናቸው። በሦስት ወራት በሀገሪቱ 11.47 ቶን ወርቅ የተመረተ ሲሆን ከወርቅ 1.2 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች።



የወርቅ ኤክስፖርት ሲጨምር የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ክምችት በማሳደግ የብር የምንዛሪ ተመን እንዲረጋጋ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ ለብሎምበርግ ተናግረዋል። ይሁንና አሁንም በመደበኛ እና ትይዩ ገበያዎች መካከል ያለው የተመን ልዩነት መቀራረብ ባለመቻሉ የብር አቅም እየተዳከመ በመሔድ ላይ ይገኛል።



ይህ ውይይት የብርን የመግዛት አቅም እያደከመ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ግብይት ይፈትሻል። በውይይቱ የፕራግማ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መርዕድ ብሥራት፣ የፋይናንስ ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ ተሳትፈዋል።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?

Eshete Bekele