DiscoverDW | Amharic - Newsብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ
ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ

ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ

Update: 2025-09-21
Share

Description

ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ። ርምጃውን የፍልስጤም መብት ደጋፊዎች መደበኛ እውቅና ለማግኘት የመጀመሪያው ጥረት ነው ሲሉ፤ በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ ውግዘት አስከትሏል።ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም በይፋ እውቅና በመስጠት ከዚህ ቀደም ዕውቅና የሰጡ ሀገራትን ተቀላቅለዋል።



ፖርቱጋል ፣ስፔን እና ፈረንሳይ ቀደም ሲል ለፍልስጤም ዕውቅና የሰጡ የአውሮፓ ሀገራት ናቸው።የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫርሰን አግቤኪያን ሻሂን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በዚህ ሳምንት የፍልስጤም ግዛትን እውን ለማድረግ የማይቀለበስ እርምጃ እየተወሰደ ነው።የሀገራቱ ርምጃ የሁለት-ግዛት መፍትሄን ያስጠበቀ እና የፍልስጤምን ነፃነት እና ሉዓላዊነት ቅርብ የሚያደርግ ነው ብለዋል።እስራኤል የሀገራቱ ርምጃ አግባብነት የሌለው እና መሬት ላይ ያሉ እውነታዎች. የማይለውጥ ስትል ክፉኛ ተችታለች። ።በእስራኤል የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ በበኩላቸው የሰላም ጥረቶችን የሚያደናቅፍ እና ውጤታማ ያልሆነ ሲሉ ርምጃውን ውድቅ አድርገዋል።ይህ ሊሳካ የሚችለው በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚደረግ ቀጥተኛ ድርድር ብቻ ነውም ብለዋል።



በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ፍልስጤምንበተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ እንደ ሀገር እውቅና ለመስጠት ማቀዳቸው ተሰምቷል። የፍልስጤም መብት ደጋፊዎች ርምጃው መደበኛ እውቅና ለማግኘት የመጀመሪያው እርምጃ ነው ሲሉ፤ እስራኤል እና አጋሮቿ "የፖለቲካ ቲያትር" ብለውታል።በፍልስጤም እውቅናላይ የሚመክረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ነገ ሰኞ በአሜሪካ ኒዮርክ ይካሄዳል።ለአስርት አመታት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም ብቸኛው መፍትሄ ተብሎ የቀረበው የእስራኤል እና የፍልስጤም የሁለት-ሃገራት መፍትሄ በፈረንሳይ እና በሳውዲ አረቢያ የሚመራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ነው። በሰኞው ስብሰባ በርካታ ሀገራት ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ከሰጡ ከ145 በላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላት እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል። ከነዚህም ውስጥ ፈረንሳይ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ቤልጂየም፣ አውስትራሊያ፣ ሉክሰምበርግ እና ማልታ ይገኙበታል።





ፀሀይ ጫኔ



ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ

ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ