DiscoverDW | Amharic - Newsኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ በአዳጊዎቿ ለአፍሪቃ ዋንጫ አለፈች
ኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ በአዳጊዎቿ ለአፍሪቃ ዋንጫ አለፈች

ኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ በአዳጊዎቿ ለአፍሪቃ ዋንጫ አለፈች

Update: 2025-12-03
Share

Description

ኢትዮጵያ ከ22 ዓመታት ቆይታ በኋላ በአዳጊ የእግር ኳስ ተጨዋቾቿ ወደ አፍሪቃ ዋንጫ ተመልሳለች ። ማክሰኞ ኅዳር 23 ቀን፣ 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ፥ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ውስጥ በነበረው ግጥሚያ የኢትዮጵያ አዳጊ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የኬንያ አቻውን 3 ለ0 ድል በማድረግ ደጋፊዎቹን አስቦርቋል ። ግቦቹን ዳዊት ካሣው፣ ቢንያም አብርሃ እና ብሩክ ዕይላቸው አስቆጥረዋል ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርሃኑ ጥላሁን ከሁለት ዐሥርተ-ዓመታት በኋላ በተገኘው ድል እሳቸውም ፌዴሬሽኑም እጅግ መደሰቱን ገልጠዋል ።



«እውነት ለመናገር ከ22 ዓመት በኋላ ነው ይህን ታሪክ መሥራት የቻልነው፥ በዚም እጅግ በጣም ደስተኖች ነን ። በአዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ላይ በደንብ ከተሠራ የተሻለ ነገር ማምጣት እንደሚቻል ያሳየንበት ውጤት ነው ማለት ይቻላል ። እና እዚህ ታሪክ ውስጥ በመኖሬ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ እንደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ሁላችንም እጅግ በጣም ደስተኞች ነን ። »



በዶይቸ ቬለ የኪስዋሂሊ ክፍል የስፖርት አዘጋጅ ኬኒያዊው ጋዜጠኛ ጆሴፋት ቻሮ በትናንቱ ግጥሚያ የኬንያ ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር የተጨዋቾቹ ብቃት ደካማ ነበር ብሏል ። በተለይ ደግሞ ተከላካዮች እና ግብ ጠባቂው የኢትዮጵያ አጥቂዎችን መቆጣጠር ተስኗቸው እንደነበር ገልጧል ። እንዲያም ሆኖ እስከ 66ኛው ደቂቃ ድረስ የኬንያ ቡድን የተረጋጋ ነበር ብሏል ። ከዚያ በኋላ ግን የትኩረት አቅጣቸውን እና ሚዛናቸውን ማጣታቸውን አክሏል ። ለኢትዮጵያ ቡድንም መልካም ምኞቹን ገልጧል ።



«ድንቅ ነው፤ ለኢትዮጵያ ቡድን ለዚያ አስደናቂ ድል እንኳን ደስ ያላችሁ ። ታላቅ ድል ነው ። እናም አሁን ማለፍ ችለዋል፣ ያም ይገባቸዋል ። አሁን ለአፍሪቃ ዋንጫ በማለፍ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳን ተቀላቅለዋል ። ይህ በጣም ደስ የሚል እና አስደናቂ ነው ። እንኳን ደስ ያላቸው ።»



የተገኘው እድል ከእጅ እንዳይወጣ ጠንክሮ መሥራት ያሻል



የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፌስቡክ ይፋዊ ገጹ ላይ ባወጣው አጠር ያለ ጽሑፍ፦ «ኢትዮጵያ ውድድሩን በስኬት እንድታስተናግድ ድጋፍ» ላደረጉ አካላት በመላ ምስጋናውን አቅርቧል ። ጀርመን አገር ነዋሪ የሆኑት የኤኮኖሚ እና አስተዳደር ባለሞያው እንዲሁም በስፖርቱ ዘርፍ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በኃላፊነት የሚያገለግሉት ዶ/ር ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ ለፌዴሬሽኑ መልእክት አላቸው ።



«ለፌዴሬሽኑ ይኼ ትልቅ ስኬት የመሆኑን ያህል ትልቅ ኃላፊነት ነው ። ይህን ስኬት ማጣት የለበትም ። እጢህ ላይ ጠንክሮ ለመሥራት እያንዳንዱን ተጨዋች በግል፣ በጨዋታ ብቃት፣ አብሮ በማጀብ እንዲሁም በሥነ-ልቦና እና ዓለም አቀፋዊ ልምድ ሊያገኙበት የሚችሉበት ላይ መሠራት አለበት ።»



መንግስት ከ17 ዓመት በታች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ10 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ ሽልማትና ውቅና መስጠቱን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ ዘግቧል ። የኢትዮጵያ ቡድን ቀድሞ ከሚታማበት የእድሜ ጉዳይ በተለየ መልኩ ዘንድሮ የተጨዋቾች ትክክለኛ እድሜ በምርመራ መረጋገጡም ተገልጧል ። በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮ ስፖርት መርኃ ግብር ዋና አዘጋጅ ምስጋናው ታደሰ ዕድሜ ላይ ጥሩ እንደተሠራ ጠቁሟል ። «በካፍም በሴካፋም ባለሞያዎች አስፈላጊውም ምርመራ ተደርጎላቸው በትክክለኛ እድሜ ላይ ይገኛሉ ተብለው የተረጋገጡ ወጣቶች ናቸው ።» በውድድሩ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ፤ ታንዛኒያ፣ ዩጋንዳ፣ ሱዳን፣ ርዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ በሁለት ምድብ ተደልድለው ተጫውተዋል ።



ቀጣዩ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ አዘጋጅ የዘንድሮ ዋንጫን የወሰደችው ሞሮኮ ናት ። ከምሥራቅ አፍሪቃ በፍጻሜው ግጥሚያ ዩጋንዳን 3 ለ2 በመርታት ዋንጫ ያነሳችው ታንዛኒያእና ሁለተኛ ደረጃ ያገኘችው ዩጋንዳ እንዲሁም በሦስተኛነት ያጠናቀቀችው ለአፍሪቃ ዋንጫ ኢትዮጵያ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።



ማንተጋፍቶት ስለሺ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ በአዳጊዎቿ ለአፍሪቃ ዋንጫ አለፈች

ኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ በአዳጊዎቿ ለአፍሪቃ ዋንጫ አለፈች

ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥዩም Mantegaftot Sileshi