DiscoverDW | Amharic - Newsየመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»
የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»

የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»

Update: 2025-09-21
Share

Description

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በቅርቡ በመቐለ ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ በሰጡት አስተያየት በትግራይ ክልል የጦርነት ዳመና እያዳመነ እንደሆነ ገልጸዋል።



"ብሔራዊ አንድነት ለህልውናና ደህንነትን ለማረጋገጥ" በሚል መሪ ሐሳብ ለሁለት ቀናት በተካሄደ የህወሐት ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫም «የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ በኩል ለሚቀርቡ ሕገመንግስታዊ ጥያቄዎች ምላሹ ማስፈራራት ሆንዋል» ሲሉ ከሷል።



ከዚህ በተጨማሪ የፌደራል መንግስት በትግራይ የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር ታጣቂዎች እያደራጀ ነው ሲል ህወሓት ከሷል። ይህ አካሄድ «የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ ነው» ብሏል።



ህወሐት በአለፈው እሁድ ባሰራጨው መግለጫ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን የፕሪቶርያ ውል በመጣስ በትግራይ ግጭት ለመፍጠር በአፋር እና በምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመለ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል።



በፌደራል መንግስት በኩል ደግሞ ሕወሐት ከኤትራ መንግስት ጋር እያካሄደ ነው ያለውን ግኑኝነት ኢሕገመንግስታዊ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት ወደ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል በተደጋጋሚ አስጠንቅቋል። የትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራም በፌደራል መንግስት በኩል ዝግጁነትና ፍላጎት ቢኖርም በህወሐት በኩል ዕንቅፋት እየገጠመው እንደሆነ ይገልጻል።



የተለያዩ የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚሰጡአቸው መግለጫዎችም ለጦርነት ዝግጁና ብቁ መሆናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በትግራይ ክክል ዳግም የጦርነት ዳመና እያንዣበበ ይሁን? መፍትሔው ምንድነው? የዛሬ ውይይታችን ርዕስ ነው። ማድመጫውን በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ያዳምጡ።



ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር



ነጋሽ መሐመድ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»

የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር Yohannes G/Egziabher