DiscoverDW | Amharic - Newsየ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት
የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

Update: 2025-10-27
Share

Description

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 ዓምን ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። ዶቸቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰጡት አስተያየት በበኩላቸው በሀገሪቱ በአሁን ሰዓት ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ ይናገራሉ። ለማሳያነትም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ፣ የተመጣጣኝ ድምፅ የምርጫ ሥርአት በምክርቤት አለመጽደቅ፤ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞች እስርና ወከባን ጠቅሰዋል።



የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 ዓ.ም የምርጫ የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በዝግ መክሯል። ቦርዱ በቴሌግራም ገጹ ባሰራጨው መግለጫ መጪውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ በተያዘው ዓመት ለማካሄድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አመልክቷል። ረቂቅ የጊዜ ሰለዳው የምርጫ ጽሕፈት ቤቶችን ከማደራጀት እስከ ይፋዊ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ድረስ መሆኑን ያሳያል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ግን በሐገሪቱ አለ ያሉትን የጸጥታ ችግርና ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ ያስረዳሉ።



« ከምርጫው እራሳችንን እናገላለን» (የገዳ ቢሊሱማ ኦሮሞ ፓርቲ)



የገዳ ቢሉስማ ኦሮሞ ፓርቲ ባሰራጨው መግለጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የተስማሙበትን ባገኙት ድምፅ የሚወከሉበት የተመጣጣኝ ድምፅ የምርጫ ሕግ በምክርቤት ጸድቆ ሥራ ላይ ካልዋለና በፓርቲው ላይ የሚደርሰው ተፅዕኖ ካልቆመ ከምርጫው እራሱን ለማግለል እንደሚገደድ አስታውቋል። የድርጅቱ የበላይ ሀላፊ አቶ ሮበሌ ታደሰ ለዶቸቨቬ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል።



የታገደ ፓርቲ አድራጊ ፈጣሪ በሆነበት ሁኔታ አስቻይ ሁኔታ እንዴት ይኖራል?



አቶ ከበደ አሰፋ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የሰብዓ እንደርታ ፖርቲ ሊቀመንበር ናቸው። በትግራይ ያለው ውስብስብ የፖለቲካ ችግር ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ አደለም ባይ ናቸው። በተለይም በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የታገደውህወሐት የጸጥታና የመንግሥት መዋቅሩን ተቆጣጥሮ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ፓርቲዎችና ግለሰቦች በሚያሳድድበት ክልል ውጤታማ ምርጫ ይካሄዳል የሚል እምነት እንደሌላቸው ያስረዳሉ።





«ቀጣዩ ምርጫ የመሠራት ወይም የመሰበር አድርገን ነው የምንወስደው»



«አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ለማካሄድ አይደለም ስለምርጫ ለመወያየትም ቅንጦት ነው» በማለት ሐሳባቸውን የጀመሩት የእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ጌትነት ወርቁ፤ ነገር ግን መንግሥት በሐገሪቱ ሰላም ካስከበረ፤ ጦርነቶች ቆመው፣ የታሰሩት ተፈትተው፣ ያኮረፉት ኃይሎች ጋር የውይይትና የድርድር ሁኔታዎች ከተካሄዱ ምርጫው ሊካሄድ እንደሚችል ተስፋቸውን ይገልጻሉ። ለዚህም ፓርቲያቸው በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን በማከል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢህአፓ/ ዋና ጸሐፊና አሁን የፓርቲው አባል የሆኑት ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ወይዘሮ ደስታ ጥላሁን ፓርቲያቸው በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ይገልጻሉ። ይሁንና ስጋት አለን ይላሉ ወይዘሮ ደስታ።

ድምጽ 4



ፓርቲዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ተአማኒ፣ ፍትሀዊና ቅቡልነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ ከተፈለገ በቅድሚያ በመላ ሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግና «ያኮረፉ» ያሏቸውን ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም አክለው ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ





Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር Yohannes G/Egziabher