DiscoverDW | Amharic - Newsናማታይ ክዌክዌዛ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ
ናማታይ ክዌክዌዛ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ

ናማታይ ክዌክዌዛ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ

Update: 2025-11-18
Share

Description

ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው የጎርጎሮሳዊው 2025 የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ለዴሞክራሲ አራማጇ ለዚምባብዊያዊቷ ናማቲ ክዌክዌዛ ይበረከታል። ሽልማቱን የሚሰጠው የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን በተለይ ለዶቼቬቬለ እንደተናገረው፣ የ26 ዓመቷ ወጣት ክዌክዌዛ በትውልድ አገሯ ለሕግ የበላይነት እና ለዲሞክራሲ ላላት ጽኑ አቋም ዕውቅና በመስጠቱ ነው። ዶቼቬለም የሽልማቱ የመገናኛ ቡዘኃን አንድ አጋር ነው።



20 አባላት ያሉት ገልለልተኛ የዳኞች ቡድን ፣ሴቶችና ወጣት አንቂዎች «አስደናቂ በራስ የመተማመን እና የዴሞክራሲያዊ ማሻሻያ ከፍተኛ መልዕክት"ያስተላልፋሉ ብሏል። ክዌክዌዛን ለዚህ ሽልማት የመረጠውም ከበርካታ ሀገራት ተወዳዳሪዎች መካከል በመጨረሻ ዙር ባካሄደው ምርጫ ላይ ነው። ናማታኒ ክዌክዌዛ በ18 ዓመቷ ነበር WELEAD TRUST የተባለ ወጣት መሪዎችን የሚያሰለጥንና በፖለቲካ ውሳኔዎች ሂደቶች ላይ እንዲሳተፉ የሚሠራ ድርጅት የመሠረተችው። እጅግ እየጨመረ በሄደው የዚምባብዌ ጨቋኝ ድባብ ክዌክዌዛ ለሕግ የበላይነት እና ለፖለቲካዊ ተሳትፎ ትታገላለች።



በተለያዩ ጊዜያት ታስራለች፤በወቅቱም ቁም ስቅልና የማስፈራሪት ሙከራዎች ደርሰውባታል።ክዌክዌዛ ማናቸውም ስኬት ዋጋ ያስከፍላል ትላለች።

«በስተመጨረሻ ለኛ ከባድ የሆነውን መምረጥ ይኖርብናል። ለእውነትን ቆመህ በመናገርህ ምክንያት ከተጠለፍክ፣ ስለ እውነትንበመናገርህ ምክንያት ታስረህ ከሆነ፣ከባድ ነው። ነገር ግን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ሕይወትህ በእድልና በአጋጣሚ የተገደበ የሕይወት ቅርፊት፣ከሆነ ያም ከባድ ነው።»



የአዲሱ ትውልድ ተወካይ



ወጣቷ አንቂ፣ የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ይሰጠኛል ብላ አልጠበቀችም ነበር። ተሸላሚ ስትሆን ግን የሽልማቱን ታሪክ፣ ማለትም እነማን ለዚህ ሽልማት እንደበቁ ወደ ኋላ መለስ ብላ መርምራለች። ከጎርጎሮሳዊው 1990ዎቹ አንስቶ መሰጠት የጀመረው ይህ ሽልማት ለርስዋም መበርከቱ እአስገርሞኛል ትላለች ክዌክዌዛ።

ይህ የተሳካውም በርስዋ ማኅበረሰብና በድርጅቷ WELEAD Africa ሠራተኞች ስለሆነ ለነርሱ ምስጋና አቅርባለች ።እንደ ወጣቱ ትውልድ ተወካይ ይህን ሽልማት በማግኘቷ ጥልቅ አድናቆቷንም ገልጻለች።« ሽልማቱ በራሱ በምንሰራው ስራ ላይ ፣ የበለጠ ትኩረት እንዲኖረን ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታልም ብላለች።



«እንደማስበው ለኛ ይሆናል የሚሉትን እስር ቤት መምረጥ ለወጣቶች በጣም ወሳኝ ነው። ራሳችሁን ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት እስር ቤት ውስጥ ልታገኙት ትችላላችሁ፤በአንድ ወቅት እንዳደረግኩት ለሰብአዊ መብቶች መታገል ። ወይም ሕይወታችሁ ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ ሁሌም የምትኖሩበት እስር ቤት ሊሆን ይችላል። ታውቃላችሁ ቢያንስ ቢያንስ ፣ ምንም አይነት እድል፣ ምንም አይነት አማራጮች፤ ምንም አይነት ክብር የሌለው ሕይወት ባለሥልጣንን አያበሳጭም ። እናም ይህን ማዘጋጀት እና መጋፈጥንም ሌሎች ሰዎች ሁሉ መከራ ሲደርስባቸው ክብር ያለው ሕይወት ሊኖራቸው የቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ምርመራ ማድረግን መረጥኩ።»



ይህም በDW የአፍሪቃ ፕሮግራሞች ኃላፊ እና የሽልማቱ ዳኞች ሊቀመንበር ክላውስ ሽቴከር እንዳሉት በዳኞች ውሳኔ ላይ ፣አርአያ የሆነ ሚና የተጫወተም ለውጥ ነው። ሽቴከር እንዳሉት

«በክፍለ ዓለሙ ወጣቶች በውሳኔ አሰጣጥ፣ ግልጽ አሠራር እና ማኅበራዊ ለውጥ ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ ናቸው ። ይህም ወጣቱ ትውልድ ከሰሞኑ እንደ ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ታንዛኒያ እና ካሜሩን ባሉት አገሮች ውስጥ ወጣቱ ትውልድ በጄን ዚ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች የሚያሳየው ነው።"



የዚምባብዌ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሕግ ሽብርን በርግጥ እየተዋጋ ነውን?



ለዳኞቹ ናማቲ ክዌክዌዛ የተቃውሞ ብቻ ሳይሆን "አዲሱ የዴሞክራቶች ትውልድ፣ በድፍረት ኃላፊነትን በመውሰድ እና የአገራቸውን መጻኤ እድል ለመቅረጽ በመርዳት" ዋና ምሳሌ የመሆናቸው ማሳያ ናት። ሽልማቱ ለሚገባቸው አፍሪቃውያን እንደ ከፍተኛው የጀርመን ዕውቅና ይቆጠራል። ሽልማቱን የሚሰጠው በየጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን ለፖለቲካው መድረክ እና ለጀርመን ሕዝብ የአፍሪቃን ገጽታ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ በቁርጠኛነት የሚሠራ ከማንኛውም ፓርቲ ነጻ የሆነ ድርጅት ነው።



ከ1993 ጀምሮ በአፍሪቃ ዲሞክራሲ፣ ሰላም፣ የሰብአዊ መብቶች፣ ዘላቂ ልማት፣ ምርምር፣ ስነጥበብ፣ ባህል ወይም ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ግለሰቦች ክብር ሰጥቷል። ባለፈው ዓመት የሴራሊዮን ዋና ከተማ የፍሪታውን ከንቲባ ኢቮን አኪ-ሳውየር ሽልማቱን ተቀብለዋል። ከሌሎችም የሽልማቱ ተቀባዮች መካከል የኮቪድ ተመራማሪዎቹ ቱሊዮ ደ ኦሊቬራ እና ሲኩሊሌ ሞዮ፣ የቀድሞዋ የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ኬትሚሌ ማሲሬ የቀድሞ የኢትዮጵያየሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የሶማሊያ አንቂዎች ዋሪስ ዲሪ እና ኢልዋድ ኤልማን ይገኙበታል። የዘንድሮው ሽልማት ኅዳር 26 ቀን፣ በጀርመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡንደስታግ ፕሬዝዳንት በዩሊያ ክሎክነር ለክዌክዌዛ ይበረከታል።



ፊሊፕ ዛንድነር /ኂሩት መለሰ



ማንተጋፍቶት ስለሺ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ናማታይ ክዌክዌዛ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ

ናማታይ ክዌክዌዛ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ