ቃለ-መጠይቅ ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ጋር
Update: 2023-02-14
Description
የኢትዮጵያ ኦርቶዶ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሲኖዶሱ ቀኖና እና ዶግማ ውጪ መፈጸሙን ያወገዘችው በሦስት ሊቃነ ጳጳሳት የተመሠረተ የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ ጉዳይ ማወዛገቡን ቀጥሏል። የቤተክርስቲያኒቱ መሪ አባቶች ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ካደረጉበት ካለፈው ዓርብ ዕለት ወዲህም አዲስ አበባ ላይ ሳይቀር የቤተክርስቲያኒቱ ሰባኪያን እና ምዕመናን የመታሰራቸው ዜናም እየተሰማው ነው። መንግሥት በውስጥ አሠራሬ አይግባ ሲል የቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ አቤቱታውን ካሰማ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ከሊቃነጳጳሳት ጋር ተወያይተው፤ ውጤቱም አዎንታዊ እንደሆነ በቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ተገልጾ ነበር። አሁንም ግን የረገበ ነገር አይታይም። በጉዳዩ ላይ ሸዋዬ ለገሠ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዎርክና አካባቢው ሊቀጳጳስ የሆኑትን አቡነ ጴጥሮስ አነጋግራለች።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
Comments
In Channel























