DiscoverDW | Amharic - Newsበጅንካ ከተማ የተከሰተው በሽታ ምንድን ነው?
በጅንካ ከተማ የተከሰተው በሽታ ምንድን ነው?

በጅንካ ከተማ የተከሰተው በሽታ ምንድን ነው?

Update: 2025-11-13
Share

Description

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጅንካ ከተማ የተከሰተውን በሽታ መንስኤ ለማጣራት እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው መላኩን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ትናንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ አክሎ እንደገለፀውም ጅንካ ከተማ የተከሰተው « ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ » የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ እንደሆነ ጠቁሟል። ዶክተር ቢንያም አስራት የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳሬክተር ሲሆኑ ተመሳሳይ ምልክት ያሳዩ አራት ህሙማን ከሳምንት በፊት ወደ ሚሰሩበት ሆስፒታል ለመታከም እንደመጡ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

«ትኩሳት ፣ ራስ ምታት ፣ብርድ ብርድ ማለት፣ የማያቋርጥ ማስመለስ እና ማስቀመጥ አጋጥሟቸው መጥተው ነበር። እነዚህ ግለሰቦች ተመሳሳይ ምልክት ካለው አንድ ግለሰብ ጋር ንኪኪ እንዳላቸው በዛን ወቅት ተነግሮ ነበር። የጤና ሁኔታቸው ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ነበር የመጣው። »





በጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ከታከሙት አራቱ ግለሰቦች አንዱ ብቻ በአሁኑ ሰዓት በህይወት እንዳለ እና የተሻለ የሚባል የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለፁልን ዶክተር ቢንያም ሁለት የሆስፒታላቸው የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ እስካሁን ስድስት ሰዎች ተመሳሳይ ምልዕክቶችን በማሳየት ህይወታቸው ማለፉን ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል። «ከአራቱ አንዱ ግለሰብ እዛው ጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ሌሎቹ ለተሻለ ህክምና ወደ ሌላ ቦታ ተልከው ነበር። እነዚህ ግለሰቦች ሪፈር የተደረጉበት ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሳሉ አንዱ ግለሰብ ኩላሊት እጥበት ስለሚያስፈልገው ወደ ግል የጤና ተቋም ተልኮ የኩላሊት እጥበት እያደረገ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። አንደኛውም ግለሰብ እንዲሁ በተመሳሳይ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ንኪኪ ያላቸው ግለሰብ የመጀመሪያው ግለሰው በጣም በጠና ታመው መጥተው ሆስፒታል ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። እነሱ ታመው ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት ማለት ነው። የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አንድ ጠቅላላ ሀኪም እና አንድ ነርስ በተመሳሳይ ህመም ተይዘው ነበር። እነሱም ወደ ተሻለ ህክምና ሪፈር ተደርገው በተደረጉበት ሆስፒታል ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።»



የጤና ሚኒስቴር ባወጣው የትናንቱ መግለጫ ምንም አይነት ህይወቱ ስላለፈ ታካሚ የተገለፀ ነገር የለም። ነገር ግን ስምንት ሰዎች በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ጋር የደወልን ቢሆንም ከግማሽ ሰዓት በኋላ መልሰን እንድንደውል ቢገልፁልንም ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ መልሰን ልናገኛቸው አልቻልንም። የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳሬክተር ዶክተር ቢንያም ስለግለሰቦቹ ሁኔታ ለክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢኒንስቲትዩት እና የዞኑ ጤና መምሪያ ሆስፒታሉ እንዳስታወቀ እና ለህብረተሰብ ጤና ኢኒንስቲትዩት ናሙና መላኩን ገልፀውልናል።«እስካሁን ባለው የጤና ሚኒስቴር ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር በውስጡ ብዙ በሽታዎች ይኖራሉ። ከእነሱ አንዱ ሊሆን እንደሚችል እንዲሁም በምርመራ እና በማጣራት ላይ እንዳለ ነግሮናል። እሱን እንጠብቃለን። ስለዚህ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ያለውን ኬዝ ማኔጅመንት እየተመራ ወይም እየተሰራ ነው የሚገኘው።»



ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር ምንድን ነው? እንዴትስ ይተላለፋል?



« ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር የተለያዩ ቫይረሶች ምክንያት የሚመጣ ኢንፌክሽን ነው። በዋናነት የደም ስሮችን የሚያጠቃ እና ደም መፍሰስ እንዲመጣ የሚያደርግ በሽታ ነው። ያንን ተከትሎ የተለያዩ የሰውነት አካላቶቻችን በቀላሉ የሚጠቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። የሚተላለፉበት መንገድም እንደ በሽታው ቤተሰብ አይነት የተለያየ ነው። ከእነዛ መካከል ደገጊ ፊቨር፣ የሎ ፊቨር የሚባል አለ። እነዚህ በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፉ ናቸው። ሌላው ደግሞ ከህመሙ ባህሪ አንፃር ከሰው ወደ ሰው (በንክኪ) የሚተላለፍበት መንገድ አለ። » ሲሉ ዶክተር ቢኒያም ያስረዳሉ። ስለሆነም ህብረተሰቡ ንኪኪን ማስወገድ እና ርቀትን መጠበቅ እንዳለበት ፤ እንደዚህ አይነት ምልዕክቶች ሲኖሩም ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንደሚያስፈልግ ዶክተር ቢኒያም እና የጤና ሚኒስቴር ይመክራሉ።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በጅንካ ከተማ የተከሰተው በሽታ ምንድን ነው?

በጅንካ ከተማ የተከሰተው በሽታ ምንድን ነው?

ልደት አበበ/ Lidet Abebe