የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክር ቤት የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አነሳ
Description
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክር ቤት የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አነሳ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የምክር ቤቱ አባል የሆኑትን አቶ ዩሐንስ ተሰማን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡ ምክር ቤቱ ያለ መከሰስ መብቱን ያነሳው ዛሬ ባካሄዴው አስቸኳይ ጉባኤ ነው፡፡ በጉባኤ ላይ በተሰጠው ማብራሪያ መንግስት በሀይል ለመጣል ከሚሰሩ አካላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸውና ህዝብን በህዝብ ላይ ለማስነሳት መልዕክት አሰራጭተዋል የሚል ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ አቶ ዩሐንስ ተሰማ ክልሉ ከዚህ ቀደም የጸደቀውን የህግ ማሻሻያን አዋጅን በመቃወም አቤቱታ ካቀረቡ የቦዴፓ 3 የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ ሲሆኑ ቦዴፓ ውሳኔውን «ዲሞክራሲን የሚያቀጭጭና የምርጫን አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ» ነው ብሏል፡፡
የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መብራቱ አለሙ ከዚህ ቀደም በክልል ምክር ቤት የጸደቀውን አዋጅ በመቃወማቸው ዛቻና ማስፈራሪያዎች ሲደርስባቸው መቆየቱን ገልጸው «ውሳኔው ለሰላማዊ ትግል እንቅፋት የሚሆን ነው» ብሏል፡፡ ፓርቲው የተቃወመው አዋጅ አንዱ የክልሉን ምክር ቤት አባላት ቁጥርን ከ99 ወደ 165 ያሳደገውን ውሳኔ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ለፈደራል መንግስት አቤቱ አቅርቧል ነው የተባለው፡፡
ግጭት በመቀስቀስና ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት ሰርቷል በሚል ተጠርጥረዋል
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኃላፊ የሆኑ አቶ ዩሐንስ ተሰማን ዛሬ ያለ መከሰስ መብት አንስቷል፡፡ ያለ መከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባል ጉዳይ በዝርዝር ያቀረቡት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሀሚድ «ግጭትን መቀስቀስና ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሱ መልዕክቶችን አሰራጭተዋል» የሚል ማብራርያ ሰጥቷል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ በሰጡት ማብራርያም በባለፈው ጉባኤ የጸደቀውን ጉባኤ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ የተላለፈውን ውሳኔ አንድ አንድ አካላት ግጭት ለመቀስቀስ መጠቀደሚያ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በቦዴፓ ፓርቲ የቀረበውን «የምርጫ ክልል ወስናችሃል» ተብሎ የቀረበውንም አቤቱታም በምክር ቤቱ ምርጫ ክልል አለመከለሉን አመልክተዋል፡፡ በተጨማሪም የምክር ቤቱ አባላትም በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን ሰጥተዋል፡፡
ውሳኔው ምርጫንና ሠላማዊ ትግልን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው መባሉን
የቦሮ ዴሞክራሲያ ፓርቲ በበኩሉ 3ቱ የምክር ቤት አባላት የካቲት 10-11/2017 በተካሄደው ጉባኤ የህገ መንግስት ማሻሻያ አዋጅን በመቃወም አቤቱ ማቅረባቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ወከባ እና ዛቻ እየደረሰበት እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በፓርቲው አባላት ላይ የሚደርሱ እስራትና ወከባ ሊቆም ይገባል ሲል ፓርቲው ገልጸዋል፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መብራቱ አለሙ እንደተናገሩት በክልል ደረጃ የጸደቀውን አዋጅ ላይ የፓርቲው አባላት ተቃውሞ ማቅረባቸውን ተከትሎ ጫናዎች መድረሳቸውን ገልጸው «ውሳኔውንም የምርጫን አስፈላጊነት እና ሰላማዊ ትግልን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው» ብሏል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ከየካቲት 10-11 ባካሄደው ጉባኤ የክልሉን ምክር ቤት የአባላት ብዛትና የክልሉን ህገ መንግስት ለማሻሻል የቀረበውን አዋጅ በአብላጭ ድምጽ ማጽደቁ ይታወሳል፡፡ ውሳኔውን የተቃወሙ የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 3 የምክር ቤት አባላትም ጉዳዩን ለህገ መንግስት ጉዳዎች አጣሪ ጉባኤ በማቅረብ የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቃቸውን ተዘግበዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የካት 10-11/2017 በየተካሄውን ጉባኤ የጸደቀውን የህግ ማሻሻያ አዋጅን በመቃወም የቦሮ ዴሚክራሲያዊ ፓርቲ ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤተቱታ ማቅረቡን ተከትሎ በማህበራዊ መገናኘ ዜገዴዎች አዋጁን በድጋፍም ሆነ በመቃወም የተለያዩ አስተያየቶች ተስተናግደዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር























