DiscoverDW | Amharic - Newsየኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግስትና የኤም 23 የሰላም ውል
የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግስትና የኤም 23 የሰላም ውል

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግስትና የኤም 23 የሰላም ውል

Update: 2025-11-18
Share

Description

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክና ኤም23 የተሰኜው ዋናው በምስራቃዊ ጎንጎ የሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን ጦርነት ለማቆምና ሰላም ለመፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ስነድ ባለፈው ቅዳሜ ቃጣር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ የተፈራረሙ መሆኑ ተገልጿል። የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክና የአማጺው ቡድን ኤም 23 ተወካዮች የመግባቢያ ስነድ የፊርማ ስነስራት የተካሄደው የአሜሪካና ያስተናጋጇ አገር ቃጣር ከፍተኛ ባለስልጣኖች በተገኙበት ነው። ይህ ባለፈው ቅዳሜ የተፈረመው የዶሀው የሰላም ስምምነት ላለፉት ወራት በምስራቃዊው ጎንጎ በሰሜንና ደቡብ ኪቩ ሲካሄድ የቆየውን ጦርነት ለመግታትና ለበርክታ አስርት መታት በዴሞክራቲክ ኮንጎ እየተከሂደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። ስምምነቱ ስምንት በቀጣይ ድርድር የሚደረግባቸው ውሎች ወይም ፕሮቶኮሎች ያሉት ሲሆን፤ ሁለቱ ወገኖች በተከታታይ ተደራድረው ተግባራዊ ያደርጓቸዋል ተበሎ ነው የሚጠበቀው።



በስምምነቱ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችና የተላለፉ ጥሪዎች



የስምምነቱ ፈራሚዎችና፤ ሸምጋይ አሸማጋዮቹ ሁሉም፤ ስምምነቱን የአስክሰፊው ጦርነት ማብቂያ እንድ እርምጃ ነው ብለውታል። ያስተንጋጇ አገር የቀጠር የውጭ ጉድያ ሚኒስተርና ዋና አደራዳሪ ዶክተር ሞሃመድ አብዱላዚ አል ክሁላይፊ፤ ሁለቱ ወገኖች የፈረሙትን ስምምነት ሲያበስሩ፤ ስምምነቱ ወሳኝ የሰላም ጉዞ ጅማሮ መሆኑን አስታውቀዋል፤ ““ የቀጠር መንግስት የኮንጎን ጦርነት ሊያስቆምና ሰላም ሊፈጥር ይችላል ተብሎ የታመነበት የዶሀው የሰላም ውል የተፈረመ መሆኑን እያረጋገጠ፤ ስምምነቱ ግን የስላም ግንባታው ጅማሮ እንጂ መጨርሻ አለመሆኑን ያስገነዝባል” በማለት ሰላም ከውጭ የሚጫን ሳይሆን ከውስጥ በሚፈጠር መተማመንና መከባበር የሚገነባ መሆኑን ገልጸዋል።



የአሜሪካ የምስራቅ አፍርካ አማካሪና የፊርማ ስነስራቱ ዋና ታዛቢ ሚስተር ማሳድ ቦውሎስ በበኩላቸው ስምምነቱን አድንቀው ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን እንዲያከብሩና እንዲተረጎሙ ጥሪ አቅርበዋል።



ያሁኑ የሰላም ውል ከበፊቶቹ የሚለይበትና አተገባበሩ



የኮንጎ ዴሞክራቲክ መንግስትና ኤም23 ባለፈው ሀምሌም ከሰላም ምምነት ደርሰው የነበር ቢሆንም ሁለቱም ስምምነቱን ሳያከብሩ ነበር የቆዩት። ያሁኑ ስምምነት በቀጣይ ሊሚደረጉ ድርድሮች መነሻ በመሆን እንድሚያገልግል የታመነ ሲሆን፤ ከበፊቱ ስምምነት የየለየ እንደሆነና ለተግብራዊነቱ የሚሰሩና የሚቆጣጠሩ አካላትም እንደተመስረቱለት ጉዳዩን የሚከታተሉ ባላሙያዎች ተናግረዋል። የዲደብሊው የምስራቅ አፍርካ ዘጋቢ ኤዲት ኪማኒ የዶሀው ስምምነት ሌሎች ግብረሀይሎችን የሚያቋቁም መሆኑን ስትገልጽ፡” ስምምነቱ አንድ አካል ወይም ተቋም እንዲቁቁም ያዛል። ይህ አካል ወደፊት የሚደረጉ ስምምነቶችን ይክታተላል ግን ደግሞ ስምምነቶችን የሚጥሱ አካልትንም ይቆጣጠራል” በማለት በቡድኑ ውስጥ የኪንሻሳ፤ የኤም 23ና የ 12 የአካባቢ አገሮች ተወካዮች የሚካተቱ መሆኑን አስታውቃለች።



ስምምነቱ ተግባራዊ ከሆነ የሚኖረው ፋይዳ



ኪማኒ ስምምነቱ እድል ቀንቶ በስራ ላይከዋለ ለአካባቢው የሚያመጣውን ጠቀሜታ ስትገልጽም “ በቅድሚያ በዴሞክራቲክ ረፑብሊክ ኮንጎ በተለይም በጦርነት እየታመሰ ላለው ምስራቃዊው ክፍል ሰላም ያስገኛል። 6.9 ሚሊዮን የሚሆኑ ተፈንቃዮችም ወደቤታቸው ይመለሳሉ፣ በኢኮኖምም አካባቢው የከበሩ ማዕድናቱ ተጠቃሚ ይሆናል፡ የኪንሻሳ መንግስትም በአካባቢው ላይ ቁጥጥር ይኖረዋል” በማለት ስምምነቱ ሰላም መፍጠር ከቻለ፤ ጎንጎ ብቻ ሳይሆን አካባቢው ባጠቃላይ ተጠቃሚ የሚሆን ስለመሆኑ አብራርታለች፡ ሆኖም ግን ዴሞክራቲክ ሊፑብሊክ ኮንጎ በዋናነት በውስጡ በያዛቸው የክበሩ ማዕድናትና የተፈጥሮ ሀብት ምክኒያት ባለቤቶቹ ብዙ በመሆናቸው ሰላም በቀላሉ እውን ሊሆን እንደማይችል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።



ገበያው ንጉሴ



ማንተጋፍቶት ስለሺ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግስትና የኤም 23 የሰላም ውል

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግስትና የኤም 23 የሰላም ውል

ገበያው ንጉሤ