DiscoverDW | Amharic - Newsየጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብር
የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብር

የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብር

Update: 2025-11-17
Share

Description

የዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብር ተካሄደ

ዶቼ ቬለን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ያገለገለው፣የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን አንደኛ ሙት ዓመት ልዩ መታሰቢያ መርሐግብር አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄደ። ''ታላላቆቻችን እናክብር፣ ከቀደሙት ምን እንማር?''፣ በሚል መርህ ትናንት በተካሄደው በዚህ የዜናነህ መታሰቢያ መርሐ ግብር ላይ፣ የቀድሞ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል። ''ይህ ዶቼ ቬለ ነው። '' ከሚለው የጣቢያዎችን መለያ መክፈቻ አንስቶ በተለያዩ ዝግጅቶች መለያ ድምፆቹ የሚታወቀው ዜናነህ መኮንን፣በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ዘጋቢነት ለረጅም ጊዜያት ሰርቷል።





የዜናነህ የሙያ አበርክቶ

ከዚያ ቀድሞ፣በኢትዮያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በድንቅ የጋዜጠኝነት ብቃት ያገለገለው ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን፣ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ትናንት አንድ ዓመት ሆነው። የአንደኛ ሙት ዓመት መታሰቢያውን መነሻ በማድረግም፣ትላንት አዲስ አበባ ውስጥ በሐሀዱ ሬድዮ ውስጥ ፣የዜና አቅራቢዎች፣ደራሲያን፣በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያገለገሉ የቴክኒክ ባለሙያዎች የታደሙበት ልዩ መርሐ ግብር ተካሂዷል። ይህንኑ የመታሰቢያ መርሐ ግብር በተባባሪነት ያካሄደው፣የተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን መስራችና ስራ አስኪያጅ እዝራ እጅጉ፣ዝግጅቱን አስመልክቶ ተከታዩን አስተያየት ሰጥቶናል።

''ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ አካባቢ በሚገኘው የሐአዱ ቴሌቪዥን አዳራሽ ወይም የቴሌቪዥን ስቱዲዮ ውስጥ የተደረገው ልዩ መርሐ ግብር ዜናነህን ለማስታወስ የተደረገ መርሐ ግብር ነው። እንግዲህ ይህ መርሐ ግብር በዋነኛነት ዜናነህ በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ሬዲዮ ከ 15 ዓመታት በላይ ያገለግለ ከዛም በኋላ ደግሞ በስደት እስራኤል አገር በሄደበት ጊዜ፣በተለያዩ ቦታዎች ያለበት ጊዜ እውቅና ለመስጠት እንደዚሁም ደግሞ ያበረከተውን አስተዋፅኦ ለማሳየት፣አንደኛ ዓመቱን ለማሰብ በሚል ነው። አብረውት የሰሩ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የነበሩ ሰዎች፣ምን ያህል ድምጹ እንደሚመጥን እንደዚሁም ከአለባበስ አንጻር ዜናዎችን ሲያነብ የሚጠቀመመው የቃላት አጠቃቀም የሚያውቁ ሰዎች ነበሩና በእሱ የዜና አነባብ ላይ ትንታኔዎች ሲሰጡ ነበር የነበረው። ''



የመርሐ ግብሩ ዓላማ

ዋናው የፕሮግራሙ ግብ፣ከእነ ዜናነህ መኮንን አዲሱ ትውልድ ምን ይማራል?የሚለው ነው ያለው እዝራ እጅጉ፣ በፕሮግራሙ ላይ እንዲሳተፉ የተጋበዙት የመስከረም ሚዲያ የጋዜጠኝነት ተማሪዎች፣ ከመታሰቢያ መሰናዶው ትልቅ ትምህርት መቅሰም እንደቻሉ መናገራቸውን ገልጾልናል። ''ጋዜጠኝነት የሚሰለጥኑ ወጣት ልጆች ወደ ሰባት የሚሆኑ በፕሮግራም ላይ ታድመው ነበር። እነርሱም ምን ተማራችሁ የሚለውን ግብረ መልስ ጠይቀን ነበር በጣም ተደስተዋል፣ድሮ የነበረውን አሰራር፣ እና ደግሞ ታላላቆቻችንን ደግሞ ስላወቅን ጥሩነው በሚል፣ለተወዳጅ ሚዲያ አክብሮታቸውን ሰጥተዋል።''

በዕለቱ ለዜናነህ ክብር የተዘጋጁ ሁለት አጫጭር የቪድዮ ቅንብሮች መርሐ ግብሩን ለታደሙት ቀርቧል። ይህንኑ፣ዜናነህ መኮንንንለመዘከር የተካሄደውን መርሀግብር ከቤተሰቦቹ እና ከተወዳጅ ሚዲያ ጋር በመሆን የተባበረው እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ላስ ቬጋስ ነዋሪ የሆነው የሙያ አጋሩ ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ ነው። ''ብዙ ጊዜ ያው ትልቅ የሰሩ እንደ አንጋፋው ዜናነህ መኮንን ያሉ ለአገራቸውና ለህዝባቸው በሙያቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎች፣ ካለፉ በኋላ መልሶ የመታወስ ነገር በጣም ጥቂት፣ ወይ የቤተሰቦቻቸው እና በቅርብ የሚያውቋቸው ጓደኞቻቸው ካልሆኑ በስተቀር የሰሩለት ህዝብ እንዲያስባቸው፣ የሰሩት ስራ የሚደረግበት ሁኔታ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር የለም እና ዜናነህ በስራዎቹ በሙያ አስተዋጽኦው፣ዕልፈቱን አስታኮ እንዲታሰብ ለማድረግ ነበር ያ ከሚገባው በላይ የተሳካ ይመስለኛል። ''



የዜናነህ ቤተሰቦች ምስጋና



የዜናነህ መኮንን የበኸር ልጅ ቢታንያ ዜናነህ ፣የመታሰቢያ ዝግጅቱን ላስተባብሩት አካላት በቤተሰባቸው ስም ምስጋና አቅርባለች። ''ልክ አንድ ዓመት ሞላ ዜናነህ ካረፈ፤ኀዘኑ አያሳርፍም አያልቅም በጣም ይከብዳል። ግን እናንተን በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ እኔም ነፃነትም እህቴም እናንተን በጣም ከልባችን እናከብራለን። ዜኒ፣ሃገሩን በጣም በጣም የሚወድ ሰው ነው፣ ኢትዮጵያ የሆነ መጥፎ ነገር ሲሆን እርሱ ራሱ ያሳምመዋል፣ ኢትዮጵያ ደስታ ስትሆን ስትሆን፣እርሱ ራሱ ደስተኛ ይሆናል። አገሩን መቼም መቼም ያልረሳ ሰው ነው። እስከመጨረሻ ድረስ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን አትርሱ እያለን ነበር። እና በቃ እናመሰግናለን በጣም በጣም እሱን ስለምታከብሩ በጣም በጣም እናመሰግናለን። ''

አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን ከ1980 ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በኖርባትእስራኤል ነበር፣ባደረበት ህመም ምክንያት አምና ሕይወት ያለፈው። የቀብር ሥነ ስርዓቱም ቴላቪቭ ውስጥ በሚገኘው ያኮም መካነ መቃብር መፈጸሙ ይታወቃል።





ታሪኩ ኃይሉ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብር

የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብር

ታሪኩ ኃይሉ