DiscoverDW | Amharic - Newsኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ
ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ

ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ

Update: 2023-02-13
Share

Description

ኢትዮጵያ የውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም ላይ መድረሷን መንግሥት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ "እስከ አሁን ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ለስድስት ገዢ ሀገራት ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ የ3 ሚሊዮን ኩንታል ውል መፈረሙን" መናገራቸው ተዘግቧል። የረድኤትና ሌሎች የሀገር ውስጥ ድርጅቶችም ከውጭ የሚገዙትን በሀገር ውስጥ እንዲተኩ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነት በመፈረም ላይ ነው ተብሏል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ትልቅ ውሳኔ ነው ብሎ እየሠራበት መሆኑን ደጋግሞ ከገለፀው ጉዳይ ስንዴን አምርቶ ለውጪ ገበያ መላክ የሚለው ይገኝበታል።ማንኛውም ሀገር ትርፍ ምርት ባይኖርም አለኝ የሚለውን ምርት ለውጭ ገበያ አቅርቦ ከዚህ ገበያ በሚያገኘው ገንዘብ የበለጠ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ ምርት ያስገባ ከሆነ በመርህ ደረጃ ምርትን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ከጉዳት በላይ ጥቅም ያለው መሆኑን የምጣኔ ኃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ገልፀዋል። ግን ይህ የሚሠራው የተሸጠው ምርት በሚያስገኘው ገንዘብ የሚገዛው እቃ የሚሸጠውን ምርት የላቀ ማሳደግ የሚችል ከሆነ ነው።

የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት እንደ ማሳያ የገለፁት ባለሙያው ሩሲያ ነጃጅ ለመሸጥ በጦርነቱ ጉዳይ የሀገሮችን አቋም እና ዝንባሌ ግምት ውስጥ ታስገባ ነበር። ይህም ማለት ምርቶች ከፖለቲካ አላማም ጭምር ለግብይት መቅረባቸው የገበያ ልማድ ነው ብለዋል። መንግሥት እስከ አሁን ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ለስድስት ገዢ ሀገራት ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ የ3 ሚሊዮን ኩንታል ውል መፈረሙን አስታውቋል። አቶ ዋሲሁን በላይ ይህ ምርት ሳይተርፍህ ለገበያ የሚቀርብበት ገፊ ምክንያት እንደሆነ በምሳሌ ጭምር አስረድተዋል።ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ኢትዮጵያ በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ ዜጎቿ ከወራት በፊት ከዩክሬን ስንዴ በእርዳታ ቀርቦላታል። ዩክሬን ለኢትዮጵያ የለገሰችውን ስንዴ ጨምሮ ሌሎች ሀገሮች የለገሱት የእርዳታ እህል የተከማቸበትን አዳማ የሚገኘውን የአለም የምግብ ፕሮግራም ( WFP ) መጋዘንን የፈረንሳይ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጎብኝተውት ነበር። የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ስንዴ ለውጭ ገበያ ሲቀርብ ለጉዳት የተጋለጠ ሕዝብ ከተዘነጋ አደጋ መሆኑን ጠቁመዋል። ሆኖም ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎቿ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ችግር እያለባቸውና አብዛኛው ሕዝብ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ ሆኖም ቢሆን ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት የምትሸጥ መሆኑ ምርት ሲተርፍ እና ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በላይ ሲኖር ብቻ የሚደረግ ላለመሆኑ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።



ሰሎሞን ሙጬ



ኂሩት መለሰ



ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ

ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ