በኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቡርግ ተህዋሲ ያሳደረገዉ ስጋት
Update: 2023-02-14
Description
በኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቡርግ በተባለ በጣም አደገኛ እና ተዛማች ተህዋሲ የተለከፉ ሰዎች መገኘታቸዉ ተገለፀ። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስታወቀዉ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች መካከል እስካሁን ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል። ከሰሃራ በታች በምትገኘዉ የአፍሪቃዊትዋ ሃገር ኢኳቶሪያል ጊኒ መንግስት በሽታዉ በተዛመተባቸዉ አካባቢዎች ላይ «የጤና ማስጠንቀቂያ» አዋጅ ደንግጓል። የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከ4,000 የሚበልጡ ሰዎች በተገለለ ስፍራ እንዲዎቆዩ መደረጉንም ገልጿል። ማርቡርግ በተባለዉ አደገኛ ተህዋሲ የመያዝ ዋንኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳት፣ የደም ተቅማጥ፣ ድካምና ከባድ ራስ ምታት እንደሆነም ተያይዞ ተገልጿል። እንደ ዓለሙ የጤና ድርጅት ከሆነ በማርቡርግ ተህዋሲ የተያዘ ሰዉ የመሞት እጣዉ 88 በመቶ ነው። የማርቡርግ ተህዋሲ በጎርጎረሳዉያኑ 1967 ዓ.ም በጀርመንዋ ሄሰን ግዛት በማርቡርግ ከተማ የመድኃኒት ኩባንያ ቤተ ሙከራ ከዩጋንዳ በመጡ የሙከራ ጦጣዎች ላይ በመገኘቱ ተህዋሲዉ የከተማዋን ስም መያዙ ተመልክቷል።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
Comments
In Channel























