DiscoverDW | Amharic - Newsቦቦረና የከፋው ድርቅ በዱር እንስሳት ላይ ያስከተለው ዕልቂት
ቦቦረና የከፋው ድርቅ በዱር እንስሳት ላይ ያስከተለው ዕልቂት

ቦቦረና የከፋው ድርቅ በዱር እንስሳት ላይ ያስከተለው ዕልቂት

Update: 2023-02-12
Share

Description

ቦቦረና የከፋው ድርቅ በዱር እንስሳት ላይ ያስከተለው ዕልቂት



በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ላለፉት አምስት የዝናብ ወቅት በዝናብ እጦት የተሰቃየው ማህበረሰብ አሁን አሁን ለህይወትም ወደ ሚያሰጋው የድርቅ ተጽእኖ ምዕራፍ መሸጋገሩ በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡



በዞኑ ከሚገኙ 7.2 የአንስሳት ሃብት 2.3 እና ከዚያ በላይ የሚገመቱ ድርቁን ባለመቋቋም ማለቃቸው ነው የሚነገረው፡፡



አሁን አሁን ደግሞ በቤት አንስሳቱ ላይ እልቂትን ሲያስከትል የነበረው የከፈፋው ድርቅ ወደ ዱር እንስሳትም መዛመቱ አሳሳቢ ነው አስብሏል፡፡ቦቦረና ከፍቶ በቀጠለው ድርቅ የተፈተነው ማህበረሰብ



“በቦረና የከፋው ድርቅ እልቂቱን ያስከተለው ሁሉም አይነት የእንስሳት ዝርያ ላይ ነው፡፡ ድርቅና በረሃን ይቋቋማሉ የሚባሉ እንደ ግመል ያሉ እንስሳትም በዚህ ድርቅ እየረገፉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የድርቁ አስከፊነት ምንያህል ከባድ መሆኑን ያስረዳል፡፡”



ይህን አስተያየት ያጋሩን በቦረና ዞን የእንስሳት ሃብት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ናቸው፡፡ ኃላፊው አክለው እንዳሉት በከፋ ሁኔታ የቀጠለው ድርቁ በዞኑ ካሉት 7.2 ሚሊየን የእንስሳት ሃብት ከቤት እንስሳት ብቻ 2.3 ሚሊየን ያህሉ እንዲያልቁ ምክኒያት ሆኗል፡፡የድርቅ መባባስ ስጋት በአፍሪቃው ቀንድ



ከ40 ዓመታት ወዲህ ተከስቶ አይታወቅም የተባለው ይህ የቦረና ድርቅ ከ800 ሺህ የላቁ ነዋሪዎችንም ለከፋ ስቃይ መዳረጉን ከዞኑ አስተዳደር የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡ ብዙ የተባለለት ክስተቱ እስካሁን ባለቁት 2.3 ሚሊየን በሚገመት የዞኑ እስሳት ሃብት 22 ቢሊየን ብር የሚገመት ሃብትን ማሳጣቱም ነው የተገለጸው፡፡



ከቤት እንስሳት በተጨማሪም አሁን አሁን የዱር እንስሳትም ድርቁን መቋቋም ተስኗቸው በስፋት እያለቁ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡ አቶ ዳውድ ሙሜ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የዱር እንስሳት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡



እንደሳቸው ገለጻ፤ ለአምስት ተከታታይ የዝናብ ወራት እየተራዘመ በመጣው በዚሁ በቦረናው ድርቅ አልቂትና ጉዳቶች አሁን አሁን ወደ የዱር እንስሳትም እየተሸገረ ነው፡፡ “አሁን አሁን በዱር እንስሳቱ ላይ እየተጋረጠ የመጣው የድርቁ አደጋ በጣም የከፋ ነው” ያሉት አቶ ዳውድ፤ በቦረና ፓርክ በጥበቃ ውስጥ የሚገኙ የዱር እንስሳትም ጭምር ለመታደግ የተሰጠው ትኩረት አናሳ በመሆኑ የተጋረጠው አደጋ የከፋ ነው ብለዋል፡፡ በድርቁ የቤት እንስሳትን ለመታደግ የተሰጠውን ትኩረት ያህል የዱር እንስሳቶቹ ትኩረት ባለማግኘታቸው በተለይም የከፋ የውሃ እጥረት አጋጥሟል ነው ያሉትም፡፡ በተለይም የቦረና ብሔራዊ ፓርክ አስተዳደር ይህንኑን ችግር ለመቋቋም ጥያቄ በማቅረቡ መስሪያ ቤታቸው ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥያቄዎችን እያሰባሰበ መሆኑንም አክለው አብራርተዋል፡፡በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የበልግ ዝናብ ተስፋ እና ስጋት



እንደ አቶ ዳውድ ማብራሪያ ከዚህ በፊት የዱር እንስሳትንም ጭምር ውሃ ሲያጠጣ የነበረው የቦረና ህዝብ አሁን ለራሱም የሚጠጣ ውሃ አጥቶ የካፋ ችግር ውስጥ መሆኑንም በመግለጽ፤ ጥሪ የሚደረግላቸው አካላት ፈጣን ምላሻቸው እንደሚጠበቅ አመልክተዋልም፡፡



ስዩም ጌቱ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ቦቦረና የከፋው ድርቅ በዱር እንስሳት ላይ ያስከተለው ዕልቂት

ቦቦረና የከፋው ድርቅ በዱር እንስሳት ላይ ያስከተለው ዕልቂት