የጦርነት ድባቡ በነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ሥጋት
Update: 2025-11-11
Description
«ጦርነት ሰልችቶናል» የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች
ባለፈው ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫህወሐት በክልሉ ዞን ሁለት በሚገኙ 6 መንደሮች ላይ ጥቃት እንደተፈጸመበት መግለጹን ተከተሎ በአካባቢው አንጻራዊ የሰላማዊ ሁኔታው ጥያቄ ውስጥ መግባቱን አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ይህን ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚኖሩ ነዋሪዎች የጦርነት ዳመና ማንዣበቡ ለከፍተኛ ስጋት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ።
ያነጋገርናቸው የክልሉ ነዋሪዎች እንደነገሩን ጦርነት ዳግም ያገረሻል በሚል ስጋት የሸቀጦች ዋጋ አለቅጥ ንሯል፣ ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ እየተሰደዱ ነው፣ ወደ መሐል አገር የሚጓዘውም አለቅጥ በዝቷል። ከምንም በላይ ደግሞ ሕዝቡ ተረጋግቶ መኖር እንዳልቻለ ነው የነገሩን። በመሆኑም የክልሉ መሪዎች ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ በየመድረኩና በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሞ ለሰላም ያለውን ፍላጎት እየገለጸ እንደሚገኝ አጫውተውናል። የተለያዩ ሐይማኖት ተከታዮችም ፈጣሪያቸው ሰላም ያወርድላቸው ዘንድ በየዕምነታቸው እየጸለዩ እንደሆነ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን እንድታዳምጡት እንጋብዛለን።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ
Comments
In Channel























